ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ ጌትነት ደርሶ ” ‹‹ሽብር ተፈፅሞብኛል እንጅ አሸባሪ አይደለሁም››፣ ‹‹ፍትህ ቢኖር ኖሮ እኔ ሳልሆን ወያኔና ግብረ አበሮቹ ነበሩ እዚህ መቆም የነበረባቸው›› ሲል፣ አቶ ዘመነ ምህረት ደግሞ ” ‹‹የተከሰስኩት ድርቡሽ እንኳ ያልደፈረውን የጎንደር ጥምቀት ላይ ፈንጅ ልታፈነዳ ነበር ተብዬ ነው፡፡ ምርመራ ላይ ግን ለምን የመኢአድ አባል ሆንክ ይሉኛል›› ማለቱን ለኢሳት የደረሰው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሙስሊሙ ማህበረሰብ በመንግስት ላይ ቅሬታውን እየገለጸ ባለበት ወቅት መጅሊሱ የጸሎት ስነስርአት አደረገ
ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሳውድ አረቢያ በጸሎት ስነስርአት ላይ በነበሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ከፍተኛ አደጋ ተከትሎ መንግስት የሃዘን መግለጫ ባለመውጣቱና ሰንደቅ አላማም ዝቅ ብሎ ባለመውለብለቡ የሃይማኖቱ አባቶች ቅሬታቸውን እየገለጹ ባለበት ወቅት፣ የእስልምና ምክር ቤቱ ሟቾቹን ለመዘከር የጸሎት ስነስርዓት አድርጓል። በአብዛኛው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው መጅሊሱ፣ ያካሄደውን የጸሎት ስነስርአት አንዳንድ የሃይማኖት አባቶች የለበጣ ...
Read More »እነ ፓስተር ኦሞት አግዋ በድጋሜ ተቀጠሩ
ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት ፓስተር ኦሞት አግዋ ፡ አሽኔ አስቲንና ጀማል ኡመር ትናንት ፍርድ ቤት ቀርበው በድጋሜ ለጥቅምት 25 ተቀጥረዋል። ቀጠሮ የተሰጠው ሁለተኛው ተከሳሽ አቶ አሽኔ አስቲን የምክር ቤት አባል በመሆናቸው፣ ያለመከሰስ መብታቸው ሳይነሳ በመታሰራቸው ፣ ጉዳዩን ለማየት ነው። እነፓስተር ኦሞት የታሰሩት የውጭ አገር የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በክልሉ ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአየር ላይ አደጋ ተረፈ
ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሶስት መቶ መንገደኞችን ጭኖ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በደብሊን አድርጎ ወደ አሜሪካ ሲጓዝ የነበረው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ድሪምላይን 787-8 አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ ላይ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር በድንገት አንድ ሞተሩ አየር ላይ ቢጠፋም በአየርላንድ ዋና ከተማ ደብሊን በሰላም ማረፍ ችሏል። መንገደኞቹ ከጀርመን ፍራንክፈርት በተላከ ተቀያሪ አውሮፕላን ወደ አሜሪካ ማቅናታቸውን ሜይል ...
Read More »ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በግብጽ ታሰሩ
ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡባዊ ግብጽ ሉዞር ላይ በባቡር አድርገው በህገወጥ መንገድ የግብጽን ድንበር ተሻግረው የገቡ አስራ አንድ ሶማሊያዊያን እና አስር ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዛቸውን የአገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች ምንጭ ጠቅሶ ዮም ሰበን ዘግቧል። በህገወጥ መንገድ በግብጽ አድርገው ወደ ሊቢያ የሚገቡ ስደተኞች በቅርብ ጊዜያት ውስጥ እየበዙ መሆናቸውንና ከ2 ሺ 215 በላይ ሕገ ወጥ ስደተኞች ባለፈው መስከረም ...
Read More »የሞያሌ ወጣቶች ለውትድርና ምዝገባ የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አደረጉት
ጥቅምት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ሞያሌ፣ የመንግስት ባለስልጣናት ወጣቶችን ለውትድርና ለመመዝገብ በድምጽ ማጉያ የታገዘ ቅስቀሳ ቢያካሂዱም፣ አንድም ለምዝገባው ፈቃደኛ ሆኖ የሄደ ወጣት አለመኖሩን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ። ወጣቶቹ የተደረገላቸውን የስብሰባ ጥሪ ባለመቀበላቸውም፣ መንግስት በሞያሌና አካባቢዋ አዳዲስ ምልምል ወታደሮችን ለመመዝገብ ያቀደው እቅድ ሳይሳካ ቀርቷል። አምና 10ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ወጣቶችን ለወትድርና ለመመዝገብ ማቀዱን የገለጸው መንግስት፣ ሂደቱ ...
Read More »ብአዴን ለበአል ማክበሪያ በሚል ህዝቡን በመዋጮ እያስጨነቀው ነው
ጥቅምት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-35ኛ አመቱን ለማክበር በዝግጅት ላይ ያለው ብአዴን ፣ በአማራ ክልል የሚኖረው ህዝብ ለበአሉ ማድመቂያ ገንዘብ እንዲያዋጣ እያስገደደ ነው። ነጋዴዎች ከብአዴን ጽ/ቤት የተጣለባቸውን ክፍያ ያለፍላጎታቸው በግድ እንዲከፍሉ ታዘዋል። ከፍተኛ የረሃብ አደጋ በክልሉ ባንዣበበት በዚህ ወቅት፣ ብአዴን እንደ ህወሃትና ኦህዴድ መቶ ሚሊዮኖችን አፍስሶ በአሉን ለማክበር መሞከሩ ፣ ከታሪክ አለመማሩን ያሳያል የሚሉት አንድ በክልሉ ...
Read More »አስራ አምስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ኬንያ ውስጥ ተያዙ
ጥቅምት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኬንያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሳምብሩ ምስራቃዊ ኢዞሎ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ሎሲሳ ውስጥ በሕገወጥ መንገድ ገቡ ያላቸውን አስራ አምስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ማሰሩን አስታውቋል። ባለፈው እሁድ ሃያአራት፣ ሰኞ ደግሞ ስድስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአካባቢው በታጣቂዎች በከበባ መያዛቸውን ገልጸዋል።ስደተኞቹ በሕገወጥ መንገድ ካለምንም ሕጋዊ ፍቃድ ድንበር አቋርጠው እንደሚገቡና አስራ አምስቱ ኢዞሎ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን የጸጥታው ሹም ...
Read More »የድርቅ አደጋው እስከ ነሃሴ 2008 ሊቀጥል እንደሚችል ተመድ አስታወቀ
ኢሳት (ጥቅምት 10 ፡ 2008) በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ እስከተያዘው አመት ማጠናቀቂያ ነሀሴ ወር ድረስ ቀጣይ ሊሆን እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዛሬ ማክሰኞ አሳሰበ ። በሀገሪቱ ተከስቶ ያለው የምግብ እርዳታ ፍላጎትም ከአራት አመት በፊት በአፍሪካ ቀንድ ተከስቶ ከነበረው አጠቃላይ መጠን ጋር ሲነጻጸር ከፍ ብሎ መገኘቱን ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። በጉዳዩ ዙሪያ ከለጋሽ ሀገራት የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ...
Read More »ኢትዮጵያ ተጨማሪ ገንዘብ ከግል ባንኮች ልትበደር ነው
ጥቅምት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ረዩተርስ እንደዘገበው የኢህአዴግ መንግስት ባለፉት 10 ወራት 1 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ20 ቢሊዮን ብር ያላነሰ ገንዘብ ከግል የውጭ አበዳሪ ባንኮች ከተበደረ በሁዋላ፣ አሁን ደግሞ 2 ቢሊዮን ዶላር ወይም 40 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመበደር በድርድር ላይ መሆኑን ረዩተርስ ዘግቧል። አዲሱ ብድር የኢትዮጵያን እዳ ከ32 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከ1 ትሪሊዮን 40 ቢሊዮን ብር ...
Read More »