ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኑዌር ዞን ዋና ከተማ ከሆነቸው ንያንግ 30 ኪሜ ራቅ ብሎ በሚገኘው የህንዱ ካራቱሪ ኩባንያ አጠገብ በሚገኘው አንዱራ የአነስተኛ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ዙሪያ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የደቡብ ዲዛይንና ግንባታ ሲፐርቪዥን ኢንተርፕራይዝ ሰራተኛ የሆኑት ኢንጂር ሙሉጌታ ደሳለኝ እና የጋምቤላ የእርሻ ቢሮ ሰራተኛ የነበሩት ወ/ሮ ሃይማኖት ተገድለዋል። የሁለቱም ሰዎች አስከሬን ማታ ወደ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አርባምንጭ በፌደራል ፖሊስ አባላት ስትታመስ ዋለች
ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአርባምንጭ ምንጮች እንደተናገሩት በቅርቡ የአርበኞች ግንቦት 7 ደጋፊዎች ኢህአዴግን የሚያወግዙና ወጣቱ ለመብቱ እንዲነሳ የሚቀሰቅሱ በራሪ ወረቀቶችን ከበተኑ በሁዋላ፣ ድርጊቱን ፈጽመዋል ብለው የጠረጠሩዋቸውን ወጣቶች በጅምላ ለማሰር ከትናንት ጀምሮ አሰሳ አካሂደዋል። አሰሳውን ተከትሎ የ70 አመት አዛውንት እናትን ጨምሮ ሴቶችና ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ተይዘዋል። ከተያዙት መካከል የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ እንደሚገኙበት ምንጮች ገልጸዋል። ...
Read More »በሰቆጣ ከፍተኛ የውሃ ችግር ተፈጥሯል
ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች እንደሚሉት ከድርቁ ጋር ተያይዞ የውሃ ችግሩ በመባባሱ ፣ ህዝቡ ውሃ ለማግኘት በእጅጉ ተቸግሯል። የውሃ ችግሩ በመባባሱና በየአካባቢው የሚታየው የውሃ ጀሪካም ብዛት ” ሳምንቱን ” ቢጫው ሳምንት” አስብሎታል በማለት ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የውሃ ችግሩ ከሰቆጣ በተጨማሪ በተለያዩ አገሪቱ ክፍሎች ይታያል። በሌላ በኩል ደግሞ ክልሉን እመራዋለሁ የሚለው ብአዴን ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ...
Read More »ቴፒ በተኩስ ስትናወጥ አመሸች
ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ፣ “የአመጹ ወጣቶችን አጋልጡ” በሚል የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግለሰቦች ቤት እየገቡ አዛውንቶችን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን እየደበደቡ ሲያስሩ ከሰነበቱ በሁዋላ ትናንት ከምሽቱ ሶስት ሰአት ጀምሮ፣ ከጫካ በመጡ ወጣቶችና በመከላከያ ፖሊስ አባላት መካከል ለሰአታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። ኢሳት ከተለያዩ ነዋሪዎች ባደረገው ማጣራት ከቴፒ 7 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቆርጫ ህብረት ...
Read More »እነ አቶ ደህናሁን ቤዛ ፍርድቤቱን በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ አስጨንቀውታል
ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ በሽብረተኝነት ወንጀል የተከሰሱት አቶ ደህናሁን ቤዛና አቶ ምንዳዬ ጥላሁን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ቀርበው እንዲመሰክሩ ፍርድ ቤቱ ለተለያዩ አካላት ደብዳቤ እንዲጽፍላቸው ለልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት በድጋሜ ደብዳቤ ጽፈዋል። ቃሊቲ እስር ቤት አቶ አንዳርጋቸው ፣ ቃሊቲ አለመታሰራቸውን ጥቅምት 12 ፣ 2008 ዓም ለፍርድ ቤቱ ጠቅሶ የነበረ ቢሆንም፣ ...
Read More »ኢህአዴግ አክራሪ የኒዮሊበራል ሀይሎች የግብርና ኢንቨስትመንቴን እየጎዱብኝ ነው አለ
ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሀገር ውስጥና የዉጪ ሀገር ባለሀብቶች በሰፋፊ እርሻዎች ላይ እንዲሰማሩ ባለፉት አምስት አመታት ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም የኒዮሊበራል ሀይሎች ባካሄዱት ፕሮፖጋንዳ ምክንያት ውጤት ማግኘት አልቻልኩም ሲል አማሯል። ከግንባሩ የተገኘ አንድ የግምገማ ሰነድ ፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ባለሀብቶች በቆላማ አካባቢዎች በኮሜርሻል እርሻዎች እንዲሳተፉ አስፈላጊው ድጋፍ ቢደረግም ፣ አንዳንዶቹ በእድሉ ተጠቅመው ጥሩ እያመረቱ ቢሆንም፣ ሌሎች ...
Read More »በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የዲሽ ተጠቃሚው ቁጥር እየጨመረ ነው
ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን በአዲስ አበባ የተለያዩ መንደሮች በመዘዋወር ባደረገው ቅኝት እጅግ ደሃ በሚባሉት መንደሮች ሳይቀር በዲሽ ከውጭ አገር የሚለቀቁ ስርጭቶችን የሚያየው ህዝብ ቁጥር ጨምሯል ብሎአል። በፎቶ ግራፍ አስደግፎ በላከው መረጃ ፣ የዲሽ ቁጥር መጨመር ህዝቡ የኢሳትን የናይል ሳት ስርጭት በብዛት እየተከታተለ መሆኑን ማሳየት ብቻ ሳይሆን፣ የመንግስቱን የቴሌቪዥን ስርጭት ለመስማት ፍላጎት እንደሌለውም የሚያመለክት ነው ...
Read More »ኢትዮጵያ የተሸከመችው 25 ቢሊዮን እዳ አሳሳቢ አይደለም ሲሉ አቶ ሃይለማሪያም ገለጹ
ኢሳት (ጥቅምት 17 ፣ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ተሸክሞ ያለው ከ25 ቢሊዮን ዶላር በላይ ብድር ለሃገሪቱ ኢኮኖሚ ጫናን አልፈጠረም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። የአለም አቀፉ ሞኒተሪ ፈንድ (አይ ኤም ኤፍ) እና በርካታ አለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ሃገሪቱ ተሸክማ ያለው ከፍተኛ ብድር ኢኮኖሚውን እየጎዳው እንደሚገኝ በመግለጽ ላይ ናቸው። በሃገሪቱ የተከማቸ ብድር መጠን ከኢትዮጵያ አጠቃላይ አመታዊ ምርት 50 በመቶውን እንደሚሸፍንና ...
Read More »131 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ኬንያ አሳልፋ እንድትሰጥ ኢትዮጵያ ጠየቀች
ኢሳት (ጥቅምት 17 ፣ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኛ ወንጀል ይፈለጋሉ በማለት ኬንያ 131 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን አሳልፋ እንድትሰጠው ጥያቄ መቅረቡን የምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ሊግ ገለጠ። የኢትዮጵያ የደህንነት እና ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ለኬንያ አቻው ያቀረበውን ይህንኑ ጥያቄ ተከትሎም በእስካሁኑ ሂደት አቶ ደበሳ ጉያ የተባለ ስደተኛ ኢትዮጵያ የገባበት ሊታወቅ አለመቻሉን የሊጉ ፕሬዚዳንት አቶ ጋሩማ በቀለ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በሽብርተኛ ...
Read More »“በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት አለ” የሚለው ተረት ተረት ነው ሲሉ ዶ/ር መረራ ጉዲና ገለጹ
ጥቅምት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮሞ ፌደራሊስት ሊቀመንበር እና የመድረክ የአመራር አባል የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ይህን ምላሽ የሰጡት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀረበውን የውይይት ግብዣ ተቃዋሚዎች ውድቅ ማድረጋቸውን ለፓርላማ አባላት መናገራቸውን ተከትሎ ነው። መንግስት በጠራው የአምስት ኣመታት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውይይት ላይ ያልተሳተፉ እንደመድረክ፣ ሰማያዊ እና መኢአድ ያሉ ፓርቲዎች ያቀረቡት ምክንያተ ውሃ ያማያነሳ ነው ...
Read More »