ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በባህርዳር ማረሚያ ቤት ለሚገኙ እስረኞች ያበረከተውን ፍራሽ ማረሚያ ቤቱ ለፖሊሶች ማከፋፈሉን ምንጮች ገለጹ፡፡ዩኒቨርሲቲው ለተማሪዎቹ አዲስ ፍራሽ በመግዛቱ ያገለገሉትን ፍራሾች እስረኞች የፍራሽ ችግር እንዳለባቸው በማወቁ እንዳበረከተ የታወቀ ሲሆን ፣ እስር ቤቱ ግን ለፖሊሶች እንዳከፋፈለ ዩኒቨርስቲው በማወቁ ቅር እንደተሰኘ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁንና ምንም አይነት እርምጃ ሳይወስድ ቀርቷል ተብሏል፡፡ በባህርዳር እስር ቤቶች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የድርቁ ሁኔታ በእጅጉ እንዳሳሰበው ተመድ ገለጸ
ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ መጽሄት ይዞት በወጣ ዘገባ፣ ከ80 እስከ 85 በመቶ የሚሆነውን የአገሪቱን የቆዳ ስፋት የሸፈነው የዝናብ መዛባት፣ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል ብሎአል። ሁኔታዎች እየባሱ ቢሄዱም ፣ በመንግስት በኩል የቀረበው የእርዳታ ጥሪ በቂ መልስ አላገኘም የሚለው መጽሄቱ፣ ከጥር በሁዋላ ያለውን የምግብ አቅርቦት ለመሸፈን አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፍልግ ገልጿል። መንግስት ለገባያ ማረጋጋያ ...
Read More »በመተማ መሳሪያ ለመቀማት በተደረገ ሙከራ አንድ ሰው በጥይት ተመታ
ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መሻ ላስታ በሚባል አካባቢ ሰሞኑን መሳሪያ ለመቀማት በተደረገው ጥረት ታደለ ነሽሃ የተባለ ሰው በጥይት መመታቱን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል። ብዙ ነዋሪዎች መሳሪያ አናስረክብም በማለታቸው እና የሌሊት ጥበቃ ላይ አንሳተፍም በማለታቸው የሌሎች ድርጅቶች አባሎች ናቸው በሚል ንብረታቸው መዘረፉን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
Read More »አልሸባብ 15 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ
ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ እንደሚለው ሁዱር አቅራቢያ በሚገኝ ሙራ ገቢይ እና ጋርስዌይኒ በተባለ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ ባደረሰው ድንገተኛ ጥቃት 25 ወታደሮችን ሲገድል ከእነዚህ ውስጥ 15ቱ የኢትዮጵያ ወታደሮች ናቸው ብሎአል። የክልሉ ባለስልጣን የሆኑት አዳን አብዲ በበኩላቸው በተኩሱ ልውውጥ 50 የአልሸባብ ወታደሮች ተገድለዋል ብለዋል። በሁለተኛው ቀን ታጣቂ ሚሊሺያው ሞቃዲሹ በሚገኘው ሳሃፊ ሆቴል ላይ ባደረሰው ጥቃት 13 ...
Read More »ኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር ሁከት ተቀስቅሶ ከአስር ሰዎች በላይ ተገደሉ
ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያዋ የድንበር ከተማ ሜሩ ኢዞሎ አቅራቢያ በቦረና እና ሜሩ ጎሳዎች መሃከል በተቀሰቀሰ ግጭት አስር የአካባቢው ነዋሪዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ ከ2 ሺ በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። የከተማው አሽከርካሪዎች ግጭቱ እጅግ አስፈሪ እንደነበርና ሁኔታዎቹ አሳሳቢ መሆናቸውን ገልጸው የሜሩ ብሔር አባላት ወደ ከተማቸው የሸሹ ሲሆን የቦረና ጎሳ አባላትም ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ ታግደዋል። በግጭቱ ...
Read More »በሶማሊ ክልል ዜጎች በረሃብ መፈናቀላቸውን የአለም የምግብ ድርጅት አስታወቀ
ጥቅምት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአለም የምግብ ድርጅት በእንግሊዝኛው ( FAO) ተወካዮች በዚህ ሳምንት በድሬዳዋ ከተማ አቅራቢያ የሚገኝን አንድ የመጠለያ ካምፕ ከጎበኙ በሁዋላ ባወጡት መግለጫ፣ በአንዳንድ ወረዳዎች 95 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በረሃቡ ምክንያት አካባቢውን ለቆ ተሰዷል። እጅግ በርካታ የቤት እንስሳት መሞታቸውን ይፋ ያደረገው ድርጅቱ፣ አሁንም ከፍተኛ የምግብ እጥረት በማጋጠሙ በተለይ ህጻናት በከፍተኛ ሁኔታ እየተጎዱ ነው። በመጠለያ ...
Read More »በኮንሶ በርካታ ወጣቶች ታሰሩ
ጥቅምት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናት ጀምሮ የአርበኞች ግንቦት7 አባሎች በሰገን ዞን ኮንሶ ወረዳ ውስጥ ገብተዋል በሚል የፖሊስ አባላት በከተማው የሚገኙ ወጣቶችን ሲያድኑ ከዋሉ በሁዋላ ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶችን ይዘው አስረዋል። በአካባቢው ሰሞኑን በፖሊስ አባላት ላይ የተፈጸመ የተባለ ጥቃትና ወጣቱን የሚያነሳሱ በራሪ ወረቀቶች መበተናቸው ለአሰሳው ተጨማሪ ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ነዋሪዎች ገልጸዋል። በሌላ በኩል ከዞን ምስረታ ...
Read More »ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ምክርቤት አባል መመረጧ ተወገዘ
ጥቅምት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከሚፈጽሙት አገራት ውስጥ ጋዜጠኞችን በማሰር፣ ሰላማዊ የዴሞክራሲ ሽግግር እንዳይፈጠር ከሚያደርጉ በቀዳሚነት ተርታ የምትገኘው ኢትዮጵያን ጨምሮ ቡሩንዲ፣ቬንዚዌላ፣አረብ ኤምሬትስ፣ቶጎ፣ ታጃኪስታን ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት አባል ሆነው መመረጣቸው የስብዓዊ መብት ተሟጓቾችን ጨምሮ የእስራኤል መንግስት ማውገዛቸውን ዴሊ ኒውስ ዘግቧል። ኢትዮጵያ በተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶች በየአመቱ በሰብአዊ መብት ጥሰት ትወነጀላለች።
Read More »በደቡብ አፍሪካ ስደተኞች ላይ ያነጣጠረው ጥቃት ተፈጸመ
ጥቅምት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሚኖሩ ስደተኞች ላይ ኢላማውን ያደረገው ባለፈው ዓመት ተፈፅሞ የነበረው ዘግናኝ ግድያና ዘረፋ በግርሃምስቶን ከተማ ውስጥ ማገርሸቱ ተገልጿል። የራሳቸውን አነስተኛ ሱቆች ከፍተው የሚተዳደሩና በተቀጣሪነት የሚሰሩ ስደተኛ ኢትዮጵያዊያን፣ሶማሊያዊያን፣ ባንግላዴሻዊያን፣የፓኪስታናዊያን ከ500 በላይ የሚሆኑ ቤተሰቦች ከዕለተ ሰኞ ጀምሮ ከስራ ቦታቸው ላይ ንብረታቸው እየተዘረፉ አካላዊ ጥቃቶች እንደተፈጸሙባቸውና በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል። የስራአጦች ...
Read More »16 ዜጎቼ በኢትዮጵያውያን ታጣቂዎች ተገደሉብኝ ስትል ሱዳን አስታወቀች
ጥቅምት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ገዳሪፍ አቅራቢያ በተቀሰቀሰ ውጊያ 16 ሱዳናዊያን መገደላቸውን፣ 12 መቁሰላቸውን እንዲሁም 7ቱ ታግተው መወሰዳቸውንና የደረሱበት እንደማይታወቅ ከ300 በላይ የቁም ከብቶችም መዘረፉን የቀድሞው የአገሪቱ ጦር አዛዥና የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ለፓርላማ ሪፖርት አቅርበዋል። ኢስማት አብዱረሕማን ” ሽፍቶች” ያሉዋቸው መሬታችንን አሳልፈን አንሰጥም ያሉ የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ...
Read More »