ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታይዋን በሚባለው አካባቢ ይሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች፣ ሆን ተብሎ በተቀሰቀሰ እሳት ድርጅታቸው እስከ ሙሉ ንብረታቸው እንደወደመባቸው ለኢሳት ተናግረዋል። ድርጊቱ ከሌሊቱ 11 ሰአት ላይ የተፈጸመ ሲሆን፣ መንግስት በአካባቢው ለሚያሰራው መንገድ ድርጅቶችን በማቃጠል ካሳ እንዳይከፍል ለማድረግ ነው በማለት ነዋሪዎች ተናግረዋል። በቃጠሎው ከ15 በላይ የንግድ ድርጅቶች የወደሙ ሲሆን፣ ፖሊሶች ህዝቡ እሳቱን እንዳያጠፋ ሲከላከሉ ታይቷል። ይህም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ እግርኳስ ቡድን በፌዴሬሽኑ ችግር ከአፍሪካ ዋንጫ ውድድሩ ውጪ ሆኑ
ጥቅምት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2016 ዓ.ም በመጪው አመት ህዳር ወር ላይ በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ የእንስቶች የእግርኳስ ዋንጫ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችለውን የእጣ ድልድል ላይ ለመሳተፍ የሚያስችለውን የተሳትፎ ማረጋገጫ ደብዳቤ የኢትዮጵያ እግርኳስ ማኅበር በወቅቱ ባለመላኩ ምክንያት የአፍሪካ እግርኳስ ማኅበር የኢትዮጵያ ሴቶች እግርኳስ ቡድን ሉሲዎችን ከምድብ ድልድል እጣ ውጪ መሆናቸውን አስታውቋል። የአፍሪካ እግርኳስ ...
Read More »በባህርዳር የተደረገውን የባጃጆች አድማ ተከትሎ ሹፈሮች እየታሰሩና የገንዘብ ቅጣት እንዲከፍሉ እየተደረገ ነው
ጥቅምት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘጋቢያችን ነዋሪዎችን በማነጋገር እንደገለጸው፣ በአድማው የተሳተፉትን ሹፌሮችን ወደ እስር ቤት የወሰዱ ሲሆን፣ ከፖሊስ የሚደርስባቸውን ጫና በመፍራት ስራ እንጀምራለን ያሉት ደግሞ 500 ብር ቅጣት ካልከፈሉ እንደማይጀምሩ ተነግሯቸዋል። ከፖሊስ የሚደርሰውን ወከባ በመፍራት ብዙ ሹፈሮች አሁንም ራሳቸውን ደብቀዋል። አንድ የባጃጅ ባለሃብት መንግስት ለምን አድማ አደረጋችሁ በሚል እየተበቀለ ነው ብለዋል።
Read More »በኢትዮጵያ ድርቁ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ
ጥቅምት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፓስፊክ ውቅያኖስ መሞቅ ሳቢያ የሚከሰተው በኤሊኖ የአየር መዛባት ተከትሎ ከሰሃራ በታች ባሉት አገራት በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሕጻናት ከፍተኛ በሆነ የምግብ እጥረት ሰለባ እንደሆኑና የዕርዳታ ለጋሽ አገሮች እርዳታውን በአፋጣኝ ካልሰጡ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ሰኞ እለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። በአስር ዓመት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ አሰቃቂ ችጋር በኢትዮጵያ ...
Read More »በአርሲ በቆጂ ከተማ አንድ ባለሃብት የተቃዋሚ ዳጋፊ ናቸው በሚል ድርጅታቸው ተዘጋ
ጥቅምት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአካባቢው ወኪሎች እንደገለጹት ባለሀብቱ አቡ ታዬ የሚባለውን ሆቴላቸውን ጨምሮ 3 ሱፐር ማርኬቶች ( የገበያ ማእከሎች)፣ 6 የእቃ ማጠራቀሚያ መጋዚኖች፣ እና ሌሎች በርካታ ድርጅቶቻቸው ታሽገውባቸዋል። ባለሀብቱ ገዢውን ፓርቲ አይደግፉም በሚል ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ግብር ሲጣልባቸው ቆይቷል። ተቃዋሚዎችን መደገፉን ትተህ ኦህዴድን ደግፍ እየተባሉ ቢዋከቡም፣ ባለሃብቱ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ችግራቸውን የሚሰማላቸው በማጣታቸው አዲስ ...
Read More »ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከዛንቢያ ወደ ኢትዮጵያ ተላኩ
ጥቅምት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዛንቢያ መንግስት በሕገወጥ መንገድ ወደ አገሬ ገብተዋል በማለት ይዞ አስሮ ያቆያቸውን ስደተኞች ወደየአገራቸው መመለሱን ያስታወቀ ሲሆን ከእነዚህ ተመላሽ ስደተኞች ውስጥ ሰባቱ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውንና ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በመሸጋገሪያነት በዛንቢያ ለማቋረጥ ሲሞክሩ በጸጥታ ኃይሎች ተይዘው መታሰራቸው ተገልጿል። የቅጣት ጊዜያቸውን አጠናቀዋል ያላቸውን 7 ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ 2 ሶማሊያዊያን፣ 3 ቡሩንዲዊያን፣ 4 ታንዛኒያዊያን እና 3 ...
Read More »አብዬ የሚገኙት የሱዳን ወታደሮች ተመድ በዶላር ካልፈላቸው የስራ ማቆም አድማ እንደሚያደርጉ አስጠነቀቁ።
ጥቅምት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-250 የሚሆኑት የሱዳን የተመድ የሰላም አስከባሪ አባላት፣ በአገሪቱ ያለው የዋጋ ንረት ህይወታቸውን ለመምራት ስላላስቻላቸው ፣ ተመድ በአገሪቱ ገንዘብ ከሚከፍላቸው በቀጥታ በዶላር እንዲከፈላቸው ጠይቀዋል። በሱዳን የሰፈሩት የተመድ የሰራዊት አባላት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ወርሃዊ ክፍያቸውን የሚያገኙት በብር ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቅሬታ ሲያቀርቡ አይሰማም። ከ10 አመት በፊት ድርጅቱ የሚከፍለን ገንዘብ በቀጥታ ...
Read More »በባህርዳር የባጃጅ አሽከርካሪዎችን አድማ ለማስቆም መስተዳድሩ በሹፌሮች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው
ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው አርብ ጀምሮየስራ ማቆም አድማ ያደረጉት የባህርዳር የባጃጅ ሹፌሮች ስራ እንዲጀምሩ ለማድረግ የከተማው ሹማምንት እርምጃ እየወሰዱ ነው። ፖሊስ የቆመ ባጃጅ መኪኖችን ሲያገኝ ታርጋ ፈቶ ከመውሰድ ጀምሮ ሹፌሮችንም እያሰረ ይገኛል። የሹፌሮች አድማ መጠናከር በከተማው ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የትራንስፖርት እጥረት የፈጠረ ሲሆን፣ መስተዳድሩ ሌሎች መኪኖችን መድቦ አገልግሎት እንዲሰጡ አስገድዷል። ስራቸውን በማይጀምሩት ሾፌሮች ላይ ...
Read More »በእስር ላይ የሚገኙት የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ
ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብር ወንጀል ተከሰው በፌደራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ የተለቀቁት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች አቶ ሃብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባል አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ የአረና አባልና ጸሃፊ መምህር አብርሃ ደስታ እንዲሁም አቶ አብራሃም ሰሎሞን አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ ሲሆን፣ ...
Read More »በቴፒ ወታደሮች ሴቶችን አስገድደው ይደፍራሉ ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ
ጥቅምት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ነዋሪዎች እንዳሉት ሰላም እና መረጋጋት እናመጣለን በማለት የሰፈሩት ወታደሮች፣ ህዝቡን አለመረጋጋት ውስጥ እየከተቱት መሆኑን ይናገራሉ። በአካባቢው የሰፈሩት ወታደሮች ሴቶችን አስገድደው ይደፍራሉ የሚሉት ነዋሪዎች፣ ሴቶች ወደ ምንጭ ወርደው ውሃ መቅዳት አልቻሉም ይላሉ። ባለትዳር ሴቶች ሳይቀር እየተደፈሩ መሆኑን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ በተለይ በቆርጫ ህብረት በሚባል ቀበሌ ወታደሮች በእናቶች ላይ ዘግናኝ ድርጊቶችን ...
Read More »