ኀዳር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ከተማ ነዋሪ የሆኑ ወጣት ከስደት ተመላሾች ከዓመታት በፊት ወደ ሐገራቸው እንዲመለሱ በከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተደረገ ቅስቀሳ በመታለል ለረጅም ዓመት ያፈሩትን ሐብትና ንብረት በአግባቡ ሳይዙ ከተመለሱ በኋላ በማህበር ተደራጅተው ያለምንም ድጋፍና ክትትል በመተዋቸው ከፍተኛ ችግር ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ወጣቶቹ የብድርና የመስሪያ ሸድ ተጠቃሚ ትሆናላችሁ ቢባሉም ፤ ከሁለት አመት በላይ ተሰርተው ያለ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢህአዴግ አባሎቹን ሂሳዊ ደጋፊና እና ጽንፈኛ ተቃዋሚ ሲል ከሁለት ከፈላቸው
ኀዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ግንባሩ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ሲመክር አሉኝ የሚላቸውን ደጋፊዎች በሁለት እንደሚከፍላቸውና ሁለቱም ለግንባሩ በስልጣን ለመቆየት ቀዳሚ የስጋት ምንጭ ናቸው ሲል ፈርጇቸዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪዎች አቶ በረከት ስምኦን፣ የጠ/ሚኒስትሩ ሌላው አማካሪ አቶ አለበል ደሴ፣ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ፣ የመረጃ መረብ ደህንነት የህዝብ አስተያየት ትንተና ክፍል ፣ የሁሉም የፖለቲካ ድርጅት ጽ/ቤት ሃላፊዎች በተወያዩበት መድረክ ላይ ...
Read More »መንግስት በትምህርቱ ዘርፍ ከፍተኛ እድገት ማምጣቱን ቢናገርም አገራዊ ግቡ ዝቅተኛ ነው ተባለ
ኀዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት አጠቃላይ የትምህርት ተደራሽነት ክንውን 43 ነጥብ 2 ብቻ መሆኑንና አሃዙ ከክልል ክልል እንደሚለያይ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ አንድ ሰነድ አመልክቷል። የትምህርት ተሳትፎው በአዲስአበባ 88 በመቶ፣በትግራይ 75 በመቶ እንዲሁም በቤኒሻንጉል ጉምዝ 45 በመቶ ሲሆን ፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ 3ነጥብ 6፣ አፋር 4 ነጥብ 5 እንዲሁም በጋምቤላ 17 ነጥብ8 በመቶ ብቻ ነው። በተለይ በአፋርና ...
Read More »በፌደራል ጉዳዮች ሚንስቴር ልዩ ድጋፍ በሚሹ ክልሎች ተመጣጣኝ ልማት ለማረጋገጥ የተዘጋጀ እቅድ አልተሳካም የሚል ሪፖርት ለአዲሱ ሚንስትር ካሳ ተ/ብርሐን ቀረበላቸው፡፡
ኀዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አዲሱ ሚንስትር በአዲሱ የስልጣን ወንበራቸው ተገኝተው ከሚንስትሩ መስሪያቤት ሰራተኞች ጋር ባደረጉት ትውውቅ ያለፉትን አምስት አመታት ሂደት በመገምገም እና የሰራተኛውን የመልካም አሰተዳደር ችግር እንዲያቀርቡ በውይይት ስራ ጀምረዋል፡፡ ሰራተኞች በግልፅ የሚንስትር መስሪያ ቤቱ ክንዋኔዎች እንዲገመግሙ እና ስሀተት ካለ ታርሞ እንዲቀጥል በሰጡት እድል በሚኒስቴሩ የተመጣጣኝ ልማት የማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ያስበነውን ግብ መምታት አልቻልንም ሲሉ ...
Read More »ለአባይ ግድብ በግድ መዋጮ እንዲከፍሉ የተገደዱ ሰራተኞች በፍርድ ቤት ክስ ከፈቱ
ኀዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ የግብርና ፅ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ቻላቸው ሞላ የግብርና ባለሙያ ሰራተኞችን ሳያነጋግሩና ፈቃዳቸውን ሳይጠይቁ፣ ከተወሰኑ ሀላፊዎች ጋር በመመካር የግብርና ባለሙያዎች በሙሉ ለአባይ ግድብ እንዲከፍሉ አድርገዋል። የግብርና ባለሙያዎች ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት መውሰዳቸው ታውቋል።
Read More »የብሪታንያ መንግስት የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጤንነት ያሳስበኛል አለ
ኢሳት (ጥቅምት 30 2008) የብሪታኒያ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙትን የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የጤንነት ሁኔታ አሳስቦት እንደሚገኝ በድጋሚ ገለጠ። የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ አስመልክቶ ትናንት ሰኞ በዚህ በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ከተማ በሚገኘው የብሪታኒያ ኤምባሲ ለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ምላሹን በጽሑፍ የሰጠው ኤምባሲው አቶ አንዳርጋቸው ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ ያሉበት ሁኔታ በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለውና በአጠቃላይ አሳሳቢ መሆኑን አስታውቋል። በኢትዮጵያና በብሪታኒያ መካከል የአቶ አንዳርጋቸው ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ዞን በርካታ የልዩ ሃይል አባላትና ሰላማዊ ዜጎች ተገደሉ
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅማንት ብሄረሰብ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአርሶ አደሩና በክልሉ ልዩ ሃይል መካከል ከማውራ 15 ኪሜ ርቃ በምትገኘዋ ሮቢት አካባቢ እንዲሁም በላይ አርማጭሆ ዋና ከተማ ትክል ድንጋይ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶአል። እስከትናንት ድረስ በአርሰዶ አደሩና በልዩ ሃይል መካከል በተደረገ የተኩስ ለውጥጥ ከ100 በላይ የልዩ ሃይል አባላት ሲገደሉ፣ ከ36 ያላነሱ ንጹሃን ዜጎች ደግሞ በልዩ ሃይል አባላት ...
Read More »ድርቁ ባጠቃቸው አካባቢ የሚኖሩ አርሶአደሮች ከፍተኛ ግብር ተጣለባቸው፡፡
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል ምስራቃዊ አካባቢዎች በዝናብ እጥረት ለረሃብ የተጋለጡ አርሶአደሮች በዚህ ችግር ላይ እያለን በአካባቢው አመራሮች ግብር እንድንከፍል በመገደዳችን ከፍተኛ ችግር ላይ ነን በማለት ተናገሩ፡፡ በድርቁ የተጎዱት አካባቢ የሚኖሩ የመንግስት ሠራተኞች በተለይ ለኢሳት ሲናገሩ ‹‹ የዝናቡ እጥረት እንዳለ ሆኖ መንግስት ለአርሶ አደሮች ግብአት አላቀረበም፡፡አርሶ አደሩ በዚህ ዓመት የሚቀምሰው አንዳች ነገር በእጃቸው ሳይኖር ግብር ...
Read More »በኮንሶ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ውጥረቱ ቀጥሏል
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ሰገን ዞን የኮንሶ ወረዳ ሕዝብ በዞን ደረጃ ራሱን በራሱ ለማስተዳደር መጠየቁን ተከትሎ የክልሉ መንግስት ልዩ ታጣቂ ኃይል ወደአካባቢው በማስገባት ነዋሪዎችን በማሰር፣ በመደብደብ እና በማስፈራራት ላይ ይገኛል። የዞኑ ባለስልጣናት ሕዝቡ ተሰብስቦ የዞን ይሰጠን ጥያቄ አላቀረብንም በማለት እንዲያወግዝ በማስጨነቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትየመብት ጥያቄው አንቀሳቀሾች ናቸው የተባሉ የወረዳውን ፖሊስ አዛዥ ጨምሮ የተለያዩ ...
Read More »ለ6 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከ150 ሚሊዮን ብር ባላነሰ ገንዘብ የግል መኖሪያ ቤት እየተሰራላቸው ነው
ጥቅምት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለከፍተኛ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት መኖሪያ የሚሆን ለእያንዳንዳቸው 25 ሚሊየን ብር የሚያወጡ፣ 6 ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች በአዲስ አበባ ሲኤምሲ አካባቢ ከፍተኛና ምቹ ቦታ ተመርጦ እየተገነቡላቸው መሆኑን የፌዴራል መንግሥት ቢሮዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተክለጻድቅ ተክለአረጋይን ለ ሸገር ኤፍ ኤም 102 ተናግረዋል። የሕንጻ ግንባታ ስራቸው በመጠናቅ ላይ ያሉት እነዚህ ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶች ...
Read More »