ኢሳት (ህዳር 9 ፣ 2008) የአለም ምግብ ፕሮግራም (FAO) በድርቁ ለተጎዱ ኢትዮጵያውያን የሚያቀርበው የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ ከሁለት ሳምንት በኋላ ሊያልቅበት እንደሚችል ትናንት ረቡዕ አሳሰበ። የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት የሚያደርገው የእርዳታ አቅርቦት ከፍተኛ እጥረት አጋጥሞት እንደሚገኝ የገለጸው ድርጅቱ፣ የምግብ አቅርቦቱ በተያዘው የፈረንጆች ወር መጨረሻ ላይ ሊቋረጥ እንደሚችል ይፋ አድርጓል። የአለም የምግብ ፕሮግራም እስከፊታችን ሰኔ ድረስ ከሚያስፈልገው የ228 ሚሊዮን ዶላር ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በቤንሻንጉል ጉሙዝ 12 የአማራ ተወላጆች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ተገኙ
ኀዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጊቱ የተፈጸመው ባለፈው መስከረም ወር ሲሆን የቀብሩ ስነስርዓት የተፈጸመው ግን ባሳለፍነው ሳንምት ነው። በመተከል ዞን በዳንጉር ወረዳ 12 የአማራ ተወላጆች ለቀን ስራ ተብለው ከተወሰዱ በሁዋላ በወረዳው አስተዳደሪ ትእዛዝ ኮከል ቀበሌ ላይ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተረሽነዋል።አስከሬናቸው ተቆራርጦ በጆንያ ተጠቅሎ መገኘቱንና የቀብር ስነስርዓታቸውም መፈጸሙን ምንጮች ገልጸዋል። የተገደሉት ነዋሪዎች 20 የሚደርሱ ሲሆን፣ እስካሁን አስከሬናቸው ...
Read More »በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ 2 መምህራን ታሰሩ
ኀዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህር ወንድማገኝ አንጆሎ እና መምህር መስፍን በላይ የታሰሩት ባለፈው ሳምንት ሲሆን፣ ወደ አዲስ አበባ ማእከላዊ እስር ቤት ተወስደዋል። ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር በተያያዘ መታሰራቸውን ምንቾች ገልጸዋል። መምህራሩ ከሰው ጋር እንዳይገናኙ ተደርጎ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። መምህር ወንድማገኝ ከመታሰራቸው በፊት ዩኒቨርስቲው የስራ እና የእግድ ደብዳቤ ጽፎላቸው ነበር። በመምህር ወንድማገኝ ላይ የቀረበውን ክስ መነሻ፣ የየኑቨርስቲ ...
Read More »አለማቀፍ የአፋር ዲያስፖራ በአፋሮች ላይ የሚደረሰውን ጥቃት በተመለከተ ለጅቡቲው ፕሬዚዳንት ደብዳቤ ጻፈ
ኀዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእንግሊዝኛ አጭር አጠራሩ ፊዳ የተባለው የአፋር ድርጅት ለጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጉሌህ በጻፈው ደብዳቤ በአፋር ህዝብ ላይ የዘር ማጽዳት በመፈጸም፣ የራስዎን ዘሮች በቦታው ላይ እያስቀመጡ ነው ሲል ከሷል። ድርጅቱ እንዳለው የአፋር ተፈጥሮአዊ መኖሪያ በሆነው ድክሂል ፣ አርታ፣ በታጁራ ከተማና በኦቦክ በሚገኙ አፋሮች ላይ የጸታ ሃይሎች እስር ግድያ፣ አፈና አስገድዶ መድፈርና ሌሎችንም ...
Read More »ብአዴን ህዝቡን በግዳጅ ሰልፍ እያስወጣ በአሉን እያከበረ ነው
ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-35ኛ አመት በአሉን በማክበር ላይ ያለው ብአዴን ፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ ተማሪዎች፣ ነጋዴዎችና በተለያዩ ሙያ የተሰመራዩት ሁሉ ስራቸውን አቁመውና ድርጅታቸውን ዘግተው በአሉን እንዲያከብሩ ተገደዋል። በበአሉ ላይ ባልተገኙት ላይ የተለያዩ ደረጃ ያላቸው ቀጣቶች እንደሚተላለፍባቸው የድርጅቱ ካድሬዎች ሲቀሰቅሱ መሰንበታቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በኮምቦልቻ፣ ደሴ ጎንደርና ሌሎችም ቦታዎች ህዝቡ ለብአዴን ሰልፍ እንዲወጡ ተገደዋል። በተለይ ተማሪዎች በበአሉ ...
Read More »የህወሃት ድጋፍ ያለው ቡድን በአፋር ስልጣኑን ተቆጣጠረ
ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር ክልል ራሳቸውን ከህወሃት ተጽኖ ለማላቀቅ በሚፈልጉ የአቶ ጣሃ አህመድ ቡድኖችና ህወሃት ከጀርባ ሆኖ በሚመራቸው በአቶ ስዩም አወል መካከል ሲካሄድ የነበረው የስልጣን ሽኩቻ ፣ በህወሃት የሚደገፉት አቶ ስዩም የአፋር ብሄራዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ሆነው በመመረጥ አሸንፈዋል። ከጥቅምት 30 / 2008 ዓ.ም እስከ ሕዳር 03/ 2008 ዓ.ም ድረስ ከቀመሌ ወደ 40 ኪሜ ርቀት ...
Read More »የአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የቅርብ ቤተሰብ በበርካታ ዜጎች ላይ የፈጸሙት ማጭበርበር ተጋለጠ
ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ባለቤት አባት የሆኑት አቶ አሰፋ ሩዎ ሂወራ በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ ነዋሪዎችን የቤት ካርታ በመቀበል በአመት ከ25 ሺ እስከ 30 ሺ ብር እንደሚከፍሉ አስታውቀው የባንክ ብድር ከወሰዱ በሁዋላ፣ ብድሩን ለመመለስ ሳይችሉ በመቅረታቸው የቤታቸውን ካርታ ያስያዙ ሰዎች ቤታቸው በሃራጅ ሊሸጥባቸው መሆኑን ተናግረዋል። ነዋሪዎች እንደተናገሩት፣ ሚኒስትሩን ከለላ በማድረግ አቶ ...
Read More »የዓለም የጤና ድርጅት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የጤና ቀውሶች ተጋላጭ ትሆናለች በማለት አስጠነቀቀ
ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዓለም ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠነ ሰፊ የሆኑ የጤና ችግሮች እንደሚከሰቱ የዓለም የጤና ድርጅት የአየር ንብረትና የጤና እክሎችን በሚተነትነው ሪፖርቱ አስጠንቅቋል። በሙቀት መጨመር ሳቢያ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ማዕበል፣ጎርፍና የመሬት መንሸራተት፣ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብን ተከትሎ በሚፈጠሩ በሽታዎች ሳቢያ የምግብ እጥረትና የጤና መቃወሶች እንደሚያጋጥሙና አስቀድሞ አደጋዎችን ለመከላከል ካልተሞከረ የችግሩ ተጋላጮች ቁጥር እንደሚጨምር ...
Read More »የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ለሶማሊያ ከወታደራዊ ይልቅ ፖለቲካዊ መፍትሔ ያስፈልጋታል አሉ
ኀዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ማህሙድ በአገራቸው ላለፉት አስር ዓመታት ለተንሰራፋው የአልቃይዳና የአልሸባብ ጥቃቶች እልባት ሊገኝለት የሚችለው ፖለቲካዊ መግባባቶችን በመፍጠር ካልሆነ በስተቀር በወታደራዊ የኃይል ጥቃቶች ብቻ ዘላቂና አስተማማኝ የሆነ ሰላም ማስፈን እንደማይቻል አበክረው ተናግረዋል። በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ ፣በበርሜል እየሞላን ጥይቶችን እና መሳሪያዎችን ስላዘነብን ብቻ አልሸባብን አናጠፋውም።የእርቅና የምህረት መንገዱን ሁሌም መፈለግ ያሻናል።አሁንም በሽምግልና ...
Read More »መንግስት ረሀቡ የደቀነውን አደጋ ለማቃለል እየሞከረ ነው
ኀዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መንግስት በአንድ በኩል የውጭ እርዳታ እየጠየቀ በሌላ በኩል ረሃቡን ብቻውን እንደሚቋቋመው መግለጹ ግራ እያጋባ ነው። የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ችግሩ ከመንግስት አቅም በላይ አይደለም ብለዋል። በሌላ በኩል ግን መንግስት ላቀረበው የእርዳታ ጥሪ አለማቀፉ ማህበረሰብ በበቂ ሁኔታ መልስ አልሰጠም በሚል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቅሬታ እያቀረበ ...
Read More »