ኀዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሳሙኤል ጋዲሳ ገለታ የተባለው የደህንነት አባል ጥቅምት 03/2008 ዓ.ም ፣ በመኪና አከራይነት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙትን አቶ ተክሉ ቀጄላን የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባል እንደሆንክ ደርሸብሃለሁ በማለት አስፈራርተው 30 ሺ ብር ጽዮን ሆቴል ውስጥ ሲቀበሉ፣ ግለሰቡ አስቀድመው ለፖሊስ አመልክተው ስለነበር፣ የደህንነት አባሉ ገንዘቡን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ ተይዟል። ፖሊስ በገንዘቡ ላይ ማህተም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአፍሪካ የሰላምና የደህንነት ጉባኤ በድርቅ የተጎዱ አገሮች እንዲረዱ ጠየቀ
ኀዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ የአፍሪካ አገራት በቦትስዋና፣ ሌሶቶ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ሞዛምቢክ፣ ደቡብ አፍሪካና ዝምባብዌ ከምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ሶማሊያን እንዲሁም በምዕራብ አፍሪካ አገራት የአየር መዛባቱ በሚፈጥረው ድርቅ ሳቢያ የምግብ እጥረትና የሰብዓዊ ቀውስና ግጭቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ምክር ቤቱ ጠቅሷል። ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ እነዚህ አገራት አስከፊ ቀውስ ውስጥ ከመግባታቸው አስቀድሞ አፋጣኝ የሆነ የሰብዓዊ እርዳታውን መለገስ እንዳለበት በአጽኖት ...
Read More »በኦሮምያ አዲሱን ማስተር ፕላን በመቃወም ተቃውሞ ተነሳ
ኀዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አወዛጋቢው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን በመቃወም ከአመት በፊት አደባባይ የወጡ የኦሮምያ ክልል ወጣቶችና ተማሪዎች ህይወታቸው በመንግስት ታጣቂዎች ከተቀጠፈ በሁዋላ፣ ኢህአዴግ እቅዱን በድጋሜ ተግባራዊ ለማድረግ መንቀሳቀሱን ተከትሎ በአምቦ፣ በማንዲና በዙሪያ ከተሞችና ቀበሌዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ተቃውሞአቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። ለኢሳት ደረሱት መረጃዎች እንደማለከቱት አካባቢው ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሁሉ በፌደራልና በኦሮምያ ፖሊሶች የተወረ ሲሆን፣ ...
Read More »በአዲስ አበባ ህዝቡ የመሬት ፖሊሲውን ሲቃወም የጸጥታ ጉዳይም አሳሳቢ እየሆነ መሆኑን ገለጸ
ኀዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ሁለተኛውን የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ከህዝብ ጋር ለመወያየት የጠራው ስብሰባ ህዝቡ ብሶቱን አሰምቶ በተቃውሞና ባለመግባባት ተጠናቋል። የካራ ቆሬ ነዋሪዎች በመጀመሪያ የተደረገላቸውን ጥሪ ባለመቀበል በስብሰባው ባለመገኘታቸው፣ በድጋሜ 50 ብር እንደሚሰጥ ከተገለጸ በሁዋላ በ አዳራሹ ተገኝተዋል። ይሁን እንጅ ውይይቱ በእቅዱ ላይ መሆኑ ቀርቶ ህዝቡ ብሶቱን ሲያሰማ ውሎአል። አንድ እናት ” የሰቆቃ ኑሮ ...
Read More »በደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ አንድ የመንግስት ወኪል መገደሉን ተከትሎ 4 ሰዎች በተገኙበት እንዲገደሉ ተወሰነባቸው
ኀዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፎገራ ወረዳ፣ ወረታ ከተማ በቁሃር ሚካኤል ቀበሌ ነዋሪ የሆነው መንግስቴ ቢምር የተባለ የአካባቢ ሹም የህብረተሰቡን መሳሪያ በማስፈታት ከኢህአዴግ ጋር ሲሰራ ነበር በሚል መገደሉን ተከትሎ፣ እስካሁን በቁጥጥር ስር ያልዋሉት ገዳዮች በተገኙበት እንዲገደሉ መወሰኑን ምንጮች ገልጸዋል። ከሹሙ ግድያ ጋር በተያያዘ እየተፈለጉ ያሉትና ባለቡት ይገደሉ የተባሉት አርሶ አደር መንጋው አላምር ፣ አርሶአደር በላቸው ውዱ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል በምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ በአርሲ ዞኖች የተረጂዎች ቁጥር አሻቀበ
ኀዳር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የተከሰተው አስከፊ ድርቅ አድማሱን እያሰፋ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብና ምስራቅ ሃረርጌ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ አፋጣኝ የምግብ ዕርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር በአሁኑ ወቅት 50 በመቶ በላይ ማሻቀቡን የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሃረን አልዪ ለሪፖርተር ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ ከ549 ሽህ ተረጂዎች ተለይተው ዕርዳታ ሲሰጣቸው የቆየ ቢሆንም ድርቁ ...
Read More »ዜጎች እርዳታ እንዲደረግላቸው እየጠየቁ ቢሆንም እስካሁን በቂ ምላሽ ሊሰጣቸው አልቻለም
ኀዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተለያዩ ክልሎች ለኢሳት የሚላኩ መረጃዎች እንደሚያሳዩት እርዳታ የሚጠይቁ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ በቂ የሆነ እርዳታ እየተከፋፈለ አይደለም። በአማራ፣ በትግራይ ፣ በሶማሊ፣ በደቡብና በአፋር የእለት ደራሽ ምግብ የሚጠይቁ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ህጻናት በአልሚ ምግብ እጥረት የተነሳ ለበሽታ እየተዳረጉ በመሞት ላይ ናቸው፡፡የረሃቡ ሁኔታ አስከፊ እየሆነ ቢመጣም በመንግስት ባለስልጣናት ...
Read More »በደቡብ ክልል በርካታ ከተሞች አርበኞች ግንቦት7 የድጋፍ ወረቀቶች ተበተኑ
ኀዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው ወጣቶች እንደገለጹት፣ በወላይታ ሶዶ ከ1 ሺ የማያንሱ በራሪ ወረቀቶች ተበትነዋል። ራሳቸውን ያደራጁት ወጣቶች በፖሊስ፣ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና የገበያ ማእከላት የአርበኞች ግንቦት7 ሊ/መንበር የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ን ፎቶ እንዲሁም የቅስቀሳ መልእክቶችን የያዙ ወረቀቶችን በግድግዳዎች ላይ ለጥፈዋል። ፖሊሶች ወረቀቶችን በመቅደድ ተጠምደው ማርፈዳቸውን፣ በከተማው ውስጥ ትልቅ የመነጋገሪያ ርእስ መፍጠሩንም ወጣቶች ለኢሳት ...
Read More »የመንግስት ደህንነቶች የኢሳትን ዌብሳይት ሰብረው ለመግባት ያደረጉት ሙከራ ከሸፈ
ኀዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመረጃ ደህንነት ባለሙያዎች በማስረጃ አስደግፈው እንደገለጹት የኢህአዴግ የመረጃ ደህንነት ሰራተኞች መብራቱ በሚል ስም ኢሳት በኢንተርኔት የሚያሰራጨውን ዌብሳይት ሰብረው በመግባት፣ ጉዳት ለማድረስ በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል። የኮምፒዩት መለያ ቁጥሩ 197. 156. 86. 162 የሆነ አዲስ አበባ የሚገኝ ኮምፒዩተር መብራቱ በሚል የመግቢያ ስም ወደ ወደ ኢሳት ዌብሳይት ለመግባት ቢሞክርም አልተሳካለትም። መንግስት በሚሊዮን ...
Read More »በቴፒ ከተማ ውጥረት ነግሷል
ኢሳት (ህዳር 14 ፣ 2008) በደቡብ ምዕራብ ቴፒ ከተማ የተቀሰቀሰውን አስተዳደራዊ አለመግባባት ተከትሎ ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት አባላት በአካባቢው መስፈሩ ተገለጠ። በከተማዋ ላይ የተነሳው የይገባኛል አስተዳደራዊ ጥያቄ ስምምነት ባለማግኘቱ በርካታ ሰዎች በተቃውሞ ጫካ መግባታቸውንና ድርጊቱ በከተማዋ ውጥረት ማንገሱን በሃገር ውስጥ ያሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ከሚዛን ተፈሪ ወደ ቴፒ፣ ከሸሸንዳ ከተማ ወደ ቴፒ፣ ከሚሻ ከተማ ...
Read More »