.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ችግር በከፋ ሁኔታ ተባባሰ።

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ ባል ድፍን አዲስ አበባ ጭለማ ውጧታል። ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ የሃይል መቆራረጡ እየተባባሰ የመጣ ሲሆን የመንግስት ሹማምንት አንዴ ችግሩ የመልካም አስተዳደር ብልሽት ውጤት ነው፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ የመስመር እርጅና ነው እያሉ ፣ እርስበርሱ የተምታታ መግለጫ ከመስጠት ባለፈ ሁነኛ መፍትሄ ሳያበጁለት ቀርተዋል። ችግሩ በተባባሰበት ባለፉት ሁለት ቀናት ዳቦ ...

Read More »

223 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከማላዊ ወደ አገራቸው ተመለሱ

ኀዳር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOM ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ ማላዊ ላይ ተይዘው በእስር ቤት ውስጥ ሲንገላቱ የነበሩትን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን አሜሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች በሰጡት 9 ሺ የአሜሪካ ዶላር ቁጥራቸው 223 የሚሆኑትን በቻርተር አውሮፕላን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከመስከረም ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ድርጅቱ ወደ ትውልድ አገራቸው እንዲመለሱ ያደረገ ሲሆን ...

Read More »

ከአንድ ሺ ያላነሱ የአዲስ አበባ ፖሊሶች የሥራ መልቀቂያ አስገብተው በመጠባባቅ ላይ ናቸው

የፖሊስ ምንጮች እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ስራቸውን ለመልቀቅ ማመልከቻ ያስገቡ ፖሊሶች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል።7 አመት ያላገለገሉ ፖሊሶች ያገለገሉበት ዘመን ታስቦ ገንዘብ ከፍለው የሚሰናበቱ ሲሆን፣ ይህንን ክፈተት በመጠቀም ብዙዎች ስራውን እየለቀቁ ሄደዋል። ከፖሊስ የሰው ሃይል ክፍል የደረሰን አስተማማኝ መረጃ እንደሚያሳያው መልቀቂያ አስገብተው ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ፖሊሶች 1 ሺ ይደርሳሉ። ብዙዎች ለመልቀቃቸው የሚሰጡት ምክንያት ከስራ ጫና፣ ከአስተዳደር፣ ዘረኝነትና ...

Read More »

የአዲስ አበባ የተለያዩ ወረዳዎች ተወካዮች የተባሉ መንግስት አይሰማንም አሉ

ኀዳር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሁለተኛውን የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አስመልከቶ የህዝብ ተወካዮች ናቸው ከተባሉ ሰዎች ጋር የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በውይይቱ ተወካዮች በየአካባቢው የሚታዩ ችግሮችን ተናግረዋል። የህዝብ ተወካዮቹ ” ብንናገርም የሚሰማን መንግስት” የለንም ብለዋል። ምንም እንኳ ብዙዎቹ ተወካዮች ለገዢው ፓርቲ ካላቸው ቀረቤታ እና በድርጅት አባልነት ተመርጠው የመጡ ቢሆንም ፣ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ በነበረው ...

Read More »

የተባበሩት መንግስታት የረድኤት ክፍል በኢትዮጵያ የሚታየውን ድርቅ የተመለከተ ፎቶግራፍ ይፋ አደረገ

ኀዳር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ድርቁ እያስከተለ ያለውን ጉዳትና የደቀነውን ፈተና ወደ ተለያዩ ቦታዎች በመዟዟር በፎቶ ግራፍ በማስደገፍ አቅርቧል። በሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ የሚኖሩት አርሶአደርን፣ የስንዴ ማሳቸው በዝናብ እጥረት የተነሳ ደርቆባቸው ሃሳብ ገብቷቸው ይታያሉ በጊዳን፣ ዳውንት፣ አበርጌሌ ወረዳዎች የጤፍ፣ የስንዴ፣ የዳጉሳና የማሽላ ማሳዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት ደርቀው መሬቱም ተሰነጣጥቆ ይታያል። በአፋር ፋንቲ ዞን ያሎ ወረዳ ...

Read More »

105 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ታንዛኒያ ውስጥ ተያዙ

ኀዳር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሕገወጥ መንገድ ወደ ታንዛኒያ ግዛት ገብተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዋና ከተማዋ ዳሬሰላም ውስጥ መያዛቸውን የከተማዋ የፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ሱሌይማን ኮቫ ገልጸዋል። አዛዡ ቁጥራቸው 105 የሚሆኑ ያሉዋቸውን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዳሬሰላም በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቀው መያቻውን ገልጸዋል። ስደተኞቹን ጨምሮ ሕገወጥ የሰው ዝውውር ሥራ ይሰራል የተባለው የ25 ዓመቱ ሩዋንዳዊ ዜጋም ተይዟል። በስደተኞች ...

Read More »

ኢትዮጵያዊቷ ሯጭ ገንዘቤ ዲባባ በረዥምና መሃከለኛ ርቀት ሩጫ የዓመቱ ኮከብ ተብላ ተመረጠች

ኀዳር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ማኅበር እንደ አውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር የ2015 ዓ.ም የዓመቱ ኮከብ ሯጮች በማለት ኢትዮጵያዊቷ ትንሿ ልዕልት ገንዘቤ ዲባባ እና አሜሪካዊው አሽተን ኤተንን መርጧል። የ24 ዓመቷ ወጣት የበቆጂ ፍሬ ገንዘቤ ዲባባ በዓመቱ ውስጥ በ1 ሽህ 500 ሜትር የሩጫ ውድድር በፈረንሳይ ሞናኮ እርቀቱን በ3 ደቂቃ 50.07 ሰከንድ ክብረወሰን ከመስበሯም በተጨማሪ በቻይና ቤጅንግ የአለም ...

Read More »

የህንዱ ካራቱሪ ኩባንያ ንብረት ጨረታ ወጣበት

ኀዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጋምቤላ ብሔራዊ ክልል በኑኤር ዞን ጂካዎ እና ኢታንግ ወረዳ የሚገኘውን የህንዱ ካራቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ ኃ/ተ/የግ/ማ ንብረት የሆነውን 100ሺህ ሄክታር የእርሻ መሬት ጨምሮ ሌሎች ንብረቶች ላይ የሐራጅ ጨረታ አውጥቷል። ባንኩ ህዳር 7ቀን 2008 በመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ባወጣው የሐራጅ ማስታወቂያ መሠረት ተጨራቾች እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2008 ዓ.ም ድረስ ...

Read More »

የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ገቢ በ2008 ዓ.ም መጀመሪያው ሩብ ዓመት እንደአለፉት ዓመታት ሁሉ ማሽቆልቆል ታየበት፡፡

ኀዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሐምሌ 2007 እስከ ጥቅምት 30 /2008 ባሉት ጊዜያት ብቻ 222 ሚሊየን ዶላር ከወጭ ንግድ ገቢ ለማግኘት ታቅዶ ማሳካት የተቻለው 177 ሚሊየን ዶላር ያህሉን ብቻ ነው፡፡ ሀገሪቱ ወደውጭ ከምትልካቸው የግብርና ምርቶች መካከል የቅባት እህሎች ጥራጥሬ፣ ቅመማቅመም፣ ቡና፣ ጫት የሚገኙበት ሲሆን በተለይ የቅባትና የጥራጥሬ እህሎት የዓለም ገበያ ዋጋ መውደቅ ጋር ተያይዞ ገቢው ሊያሽቆለቁል ...

Read More »

ለብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል 200 ሚሊዮን ብር ተመደበ

ኀዳር ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህገመንግስቱ የጸደቀበት በተለምዶ የብሄር ብሄረሰቦች በአል ህዳር 29 ቀን በጋምቤላ ክልል የሚከበር ሲሆን ፣ ለበአሉ ድምቀት በጋምቤላ ስታዲየም ተገንብቷል። ከ5 ሺ በላይ እንግዶችን ለማስተናገድ የማሰልጠኛ ተቁዋማት የመማሪያ ክፍሎችን ጭምር ወደ ምኝታ ክፍሎች ለመቀየር ታስቦአል። በፈዴሬሽን ም/ቤት በኩል በየአመቱ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ የሚወጣበት ይህ በአል ፣ዘንድሮ ከ15 ሚሊየን በላይ ወገኖች በድርቅ ...

Read More »