ታኀሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የባንኩ ሰራተኞች እንደገለጹት ኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር እንዲዋሃድ የተደረገው ከጀርባው ያለውን የዘረፋ ወንጀል ሽፋን ለመስጠት ነው።ሰራተኞቹ በዘረፋው ወንጀል የበላይ የመንግስት አካላት እንዳሉበት ይገልጻሉ። ባንኩ በ2008 ዓም 12 ሚሊዮን ብር መክሰሩን የሚገልጹት ሰራተኞች ለኪሳራው ምክንያት ናቸው ያሉዋቸውን በርካታ የሙስና ወንጀሎች ዘርዝረው አቅርበዋል። ባንኩ አገልግሎትን እንዲያቀላጥፍ በሚል ቲ 24 ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በመሬት አስተዳደር ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ለመሬት ዝርፊያ ከፍተኛ አመራሮችን ተጠያቂ አደረጉ
ታኀሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአማራ ክልል የሚገኙት ከፍተኛ የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎችና የስራ ሂደት መሪዎች ለኢሳት እንደተናገሩት ‹‹ በእኛ ዘመን መሬት በየትኛውም አቅጣጫ በሙሰኞች እጅ መውደቁ ቁጭት ፈጥሮብናል፡፡ ››ይላሉ ፡፡ ትልቁን ሚና የሚጫወቱት የስርአቱ አመራሮች ናቸው ሲሉ ይወቅሳሉ። ከአደርባይነት የተላቀቀ አመራር ማግኘት ከፍተኛ የወቅቱ ችግር መሆኑን የሚናገሩት የስራ ሃላፊዎች በተለይ መሬት በከተሞች ላይ ትልቅና ፈታኝ ...
Read More »ከማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ 5ሺ በላይ የሚሆኑ ዜጎች እንደታሰሩ ታወቀ
ኢሳት ዜና (ታህሳስ 18 ፣ 2008) በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ለእስር የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ቀጥሎ በመንግስት ታጣቂ ሃይሎች የተያዙ ሰዎች ቁጥር አራት ሺ አካባቢ መድረሱን የኦሮሚያ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሰኞ አስታወቀ። ለእስር ከተዳረጉት መካከልም 500 ያህሉ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች፣ ወረዳዎችና ቀበሎዎች የሚገኙ አባላት መሆናቸዉን የኦፌኮ ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ በቀለ ነገአ ለሀገር ዉስጥ መገናኛ ገልጸዋል። በሳምንቱ መገባደጃ ሁለት የስራ ...
Read More »በድርቁ ምክንያት 400ሺ ህጻናት አሳሳቢ ሁኔታ ላይ መሆናቸው፣ አንድ ሚሊዮን ትምህርት ማቋረጣቸው ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 18 ፣ 2008) በኢትዮጵያ ስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ ከ 400ሺ የሚበልጡ ህጻናትን ለአሳሳቢ የጤናና የአካል ችግር አጋልጦ እንደሚገኝና ጉዳት የሚደርስባቸው ህጻናት ቁጥር እያሻቀበ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታወቀ። ለተረጂዎች የሚያስፈልገው ድጋፍ በበቂ ሁኔታ በመቅረብ ላይ አለመሆኑ ችግሩን እያባባሰው እንደሆነም ድርጅቱ ገልጿል። ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ከ10 ሚሊዮን ሰዎች መካከል ወደ ግማሽ የሚጠጉት ህጻናት ...
Read More »ሲፒጄ በጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደው ያለው የእስር ዘመቻ እንዳሳሰበዉ ገለጸ
ኢሳት ዜና (ታህሳት 18 ፣ 2008) ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል ተቀስቀሶ የነበረዉን ተቃዉሞ ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ መዉሰድ የጀመረዉ የእስረ ዘመቻ እንዳሳሰበዉ መቀመጫዉን በዚህ በአሜሪካ ያደረገዉ CPJ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሰኞ አስታወቀ። በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ለእስር የተዳረገዉ ጋዜጠኛ ጌታቸዉ ሽፈራው በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቅ ተቋሙ ጥሪዉን አቅርቧል። በአንድ ሳምንት ዉስጥ ለእስር ሲዳረግ ሁለተኛ ጋዜጠኛ የሆነዉ ...
Read More »በማስተር ፕላን ላይ የተነሳት ተቃውሞ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ ማገርሸቱ ታወቀ
ኢሳት ዜና (ታህሳስ 18 ፣ 2008) ከአንድ ወር በላይ የዘለቀውና፣ ለአንድ ሳምንት ጋብ ብሎ የሰነበተው ተቃውሞ፣ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ዳግም መቀስቀሱ ተገለጸ። በመላው ኦሮሚያ ክልል የተነሳው ተቃውሞ፣ ለተወሰነ ጊዜ ጋብ ያለ ቢመስልም፣ በምዕራብ ወለጋ፣ በምዕራብና ሰሜን ሸዋ በተለያዩ ከተሞች ዩንቨርስቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተቀጣጥሎ መቀጠሉ ታውቋል። ባለፈው ዓርብ ማለትም በወለጋ ዩንቨርስቲ፣ በሰሜን ሸዋ ወረዳዎች፣ ቱሉ ሚልኪ እንዲሁም ...
Read More »መንግስት በሃይል ሊያዳፍነው የሞከረው ተቃውሞ እንደገና አገረሸ
ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ መንግስት አጋዚ የሚባለውን ጦሩን በማሰማራት ሊጨፈልቀው ያሰበው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደገና አገርሽቶ በርካታ ተማሪዎች ታስረዋል። በወለጋ ዩኒቨርስቲ የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ የአጋዚ ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ በርካታ ተማሪዎች ተደብድበው ታስረዋል። ተማሪዎቹ ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል ወደ ጫካዎችና አጎራባች ከተሞች ቢያመልጡም ወታደሮቹ እግር በእግር እየተከታተሉ በመደብደብ አስረዋቸዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ወታደሮቹ ከትናንት በስቲያ በአምቦ ዩኒቨርስቲ ...
Read More »የኢትዮጵያና የሱዳን ድንበርን ለማካለል የተጀመረ ስራ እንደሌለ የኮምኒኬሽንና ሚዲያ ባለሙያዎች ደጋግመው እንዲሰሩ የአቶ ጌታቸው ረዳ ጽ/ቤት አሳሰበ፡፡
ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመንግስት ኮምንኬሽን ጽ/ቤት ለኮምኒኬሽን ባለሙያዎችና ለጋዜጠኞች ባሰራጨው የመንግስት የሳምንቱ አቋም መግለጫ በኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ የተጀመረ ስራ እንደሌለ እንዲናገሩ አቅጣጫ አስቀምጧል። “መንግስት ሁሉም የኢትዮጵያ ድንበሮችን የማካለል ስራ ጠቃሚ መሆኑን ይረዳል”ያለው ፣ የአቋም መግለጫው፣ ሆኖም የኢትዮ-ሱዳንን ድንበር ለማካለል አሁን ምንም የተደረገ ስምምነት የለም።» በማለት በሱዳን ሚዲያዎች በተደጋጋሚ እየተዘገበ ያለውን ጉዳይ ለማስተባበል ...
Read More »የካራቶሪው ባለቤት መሬቴን ትነኩና የህንድን ሃያልነት ታያላችሁ ሲሉ የመንግስት ባለስልጣናትን አስጠነቀቁ
ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጋምቤላ 300 ሺ ሄክታር መሬት ተሰጥቷቸው ለማልማት ባለመቻላቸው ከፍተኛ ትችት የሚቀርብባቸው የካሩቱሪ አግሮ ፕሮዳክትስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ መሥራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳይ ራማክሪሽና ከሪፖርትር ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ የጋምቤላ ክልል መንግስት በግድ ሳይፈልጉ በፈለጉት ዋጋ ከፍለው 300 ሺ ሄክታር መሬት እንደሰጧቸው ተናግረዋል። እኔ የጠየቁት 10 ሺ ሄክታር ብቻ ነው ያሉት ባለሃብቱ፣ ...
Read More »ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን ማሰር መቀጠሉ እያሳሰበው እንደመጣ አሳወቀ።
ታኀሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የነገረ ኢትዮጵያ ዘጋቢ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እለተ ዐርብ በጸጥታ ኃይሎች ከመንገድ ላይ ተይዞ የታሰረ ሲሆን፣የኦሮሚያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ጋዜጠኛ ፍቃዱ ሚርካናም በደኅንነት ኃይሎች ተይዞ ያለበት ቦታ እንደማይታወቅ ጂፒጄ አስታውቋል። በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔት እየከፋ መምጣቱንና በአፍሪካ ውስጥ ካሉ አገራት ጋዜጠኞችን በማሰር የኢትዮጵያ መንግስት ከቀዳሚዎቹ ተርታ መቀመጡን ሲፒጄ በሪፖርቱ አስታውቋል። ...
Read More »