ታኀሳስ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በሚገኙ ሰባት ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ፣ የሚያስተምሩ መምህራን በየጊዜው ስራቸውን በመልቀቃቸው የትምህርቱ ስራ አደጋ ላይ መሆኑን የዞኑ ትምህርት ከፍተኛ ባለስልጣናት በጎንደር ከተማ በሰጡት መግለጫ ተናገሩ፡፡ በዞኑ ባሉት 280 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ከ120 ሽህ በላይ ህጻናት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማቆም በቋፍ ላይ መሆናቸወን የተናገሩት የዞኑ አመራሮች በተለይ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢትዮጵያ ፖሊሶች ሁለት ኬንያዊያንን አግተው መውሰዳቸው ታወቀ
ታኀሳስ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቅዳሜ እለት የኢትዮጵያ የደኅንነት ኃይሎች በኢትዮ ኬንያ ድንበር ቦሪ አቅራቢያ ተሻግረው ሁለት ኬንያዊንና ሁለት የእሳት አደጋ መከላከያ መሳሪያዎችን አግተው መውሰዳቸውን የቀጠናው ፖሊስ አስታውቋል። የመርሳቤት ግዛት የፓሊስ አዛዥ የሆኑት ሞፋት ካንጋ እንዳሉት ግለሰቦቹ ምን እንዳደረጉ ያወቅነው ነገር የለም። በእርግጥ በኦሮሞ ሕዝብና በኢትዮጵያ መንግስት መሃከል ችግር እንዳለ እናውቃለን። የታገቱትን ዜጎቻችንን እንደሚለቁና የወሰዱብንን ...
Read More »በዲላ ዩንቨርስቲ ቦምብ ፈንድቶ 2 ተማሪዎች ሲሞቱ በርካታዎች ቆሰሉ
ኢሳት (ታህሳስ 23 ፣ 2008) ሐሙስ ምሽት በዲላ ዩንቨርስቲ በደረሰ የእጅ ቦንብ ፍንዳታ ሁለት ተማሪዎች የሞቱ ሲሆን፣ በርካታ ተማሪዎችም ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ላይ እየወሰዱ ያለው የእስር ዘመቻና ግድያ ተቃውሞው በድጋሚ እንዲቀሰቀስ ማድረጉን ለመርዳት ተችሏል። ግድያ ይቁም የሚል መፈክሮችን በማሰማት ላይ የሚገኙት እነዚሁ ተማሪዎች የፅጥታ ሃይሎች ከትምህርት ...
Read More »ኢትዮጵያ ከህገወጥ ገንዘብ ተቋማት ጋር በተያያዘ በአመት ሁለት ቢሊዮን ዶላር እንደምታጣ ተገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 23 ፣ 2008) በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር በየአመቱ ከፍተኛ ገንዘብ የምታወጣው ኢትዮጵያ ከህገ-ወጥ ንግድ ተቋማት ጋር በተያያዘ በየአመቱ ሁለት ቢሊዮን ዶላር እያጣች እንደሆነ አንድ አለም አቀፍ የፋይናንስ ደህንነት ተቋም ይፋ አደረገ። እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2004-2013 26 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ያጣችው ኢትዮጵያ ከዚሁ ገንዘብ መካከል 19.7 ቢሊዮን ዶላር ከህገወጥ ንግድ ጋር የተያያዘ መሆኑን ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተለጀንስ አስታውቋል። ሃገሪቷ ...
Read More »በአፋርና ሶማሌ ክልል የምግብ እጥረት አሳሳቢ ነው ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ
ኢሳት (ታህሳስ 23 ፣ 2008) በደቡብ የአፋር አካባቢና በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን በድርቅ ምክንያት የተከሰተው የምግብ እጥረት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አርብ አስታወቀ። በነዚህ አካባቢዎች የአደጋው አሳሳቢነት በደረጃ ሁለትና ሶስት ውስጥ ተመድቦ ቢቆይም፣ ይኸው አሃዝ ወደ ደረጃ አራት ከፍ ማለቱን የምግብ እጥረቱ የከፋ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። በእነዚሁ ዞኖች ውስጥ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮችና አርብቶ-አደሮች አፋጣኝ ...
Read More »የቀድሞ መከላከያ ሰራዊት አባላት ማህበር አባላቱ ከህዝቡ ጎን በመሆን እንዲታገሉ ጥሪ አቀረቡ
ኢሳት (ታህሳስ ፣ 2008) የቀድሞው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አርበኞች ማህበር በኦሮሚያ ክልል በፀጥታ ሃይሎች የተገደሉ ሰዎችን ድርጊት በማውገዝ የቀድሞ የሰራዊት አባላት ህዝቡ እያካሄደ ካለው ትግል ጎን እንዲሰልፍ ጥሪን አቀረበ። በስልጣን ላይ ያለው ገዢው የኢህአዴግ መንግስት መብታቸውን በሚጠይቁ ሰዎች ላይ የሚወስደው የግፍ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የገለጸው ማህበሩ፣ ህዝቡ ለሰላም ያለውን ተስፋም ጨልሞ እንደሚገኝ አስታውቋል። እያንዳንዱ የቀድሞ ሰራዊት አባላት በያለህበት ሆነህ በመደራጀትና ...
Read More »በአባይ ጉዳይ ላይ ያደረኩት ምንም ስምምነት የለም ሲል የኢትዮጵያ መንግስት አስተባበለ
ኢሳት (ታህሳስ 21 ፣ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ከግብፅ መንግስት ጋር የተደረሰ ምንም አይነት አዲስ ስምምነት የለም ሲል ሃሙስ አስተባበለ። የግብፅ ባለስልጣናት በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ጋር አዲስ ስምምነት መፈረሙንና የየትኛውም ሃገር በተናጥል በግዱቡ ላይ ምንም አይነት ስራ እንዳያከናውን ውሳኔ መደረጉን በመግለጽ ላይ ናቸው። ሁለት የፈረንሳይ አለም አቀፍ ተቋማት በግድቡ ላይ የሚያካሄዱት ጥናት እስኪጠናቀቅ ድረስ ግድቡን በውሃ የመሙላቱን ሂደት እንዳይካሄድ ፕሬዚደንት አልሲሲና በድርድሩ ...
Read More »በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን አፈና ተጠናክሮ እንደቀጠለ አንድ አለም አቀፍ ተቋም ገለጸ
ኢሳት (ታህሳስ 21 ፣ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት በሃገር ውስጥ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ አለም አቀፍ ትኩረትን እንዲያገኝ ለማድረግ ከውጭ ሃገር የሚሰራጩ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ የቁጥጥር ዘመቻ መክፈቱን ግሎባል ቦይስ የተሰኘ አለም አቀፍ ተቋም ይፋ አደረገ። በዚሁ የመንግስት ዘመቻም በ10 ሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ተከታታይ ያለው ኢሳት እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ስርጭት መስተጓጎሉን በሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ የሚሰራው ተቋም አስታውቋል። በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመወን ግድያ ...
Read More »የህንዱ ኩባንያ ካራቱሪ ከመንግስት ጋር የነበረው ውል ተቋርጧል ተባለ
ኢሳት (ታህሳስ 21 ፣ 2008) በጋንቤላ ክልል 100ሺ ሄክታር መሬትን በርካሽ ዋጋ ለ 50 ዓመታት ተረክቦ የነበረው የህንዱ ካራቱሪ ኩባንያ ከመንግስት ጋር የነበረው ውል ተቋረጠ። ድርጅቱ ከመንግስት የተሰጠውን ወደ 60 ሚሊዮን ብር ብድርም መክፈል ሳይችል የቀረ ሲሆን፣ ከተረከበው 100ሺ ሄክታር መሬት ውስጥ ባልፉት ስድስት አመታት 1ሺ 200 ሄክታር መሬት ብቻ ማልማቱ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ግብርና ኢንቨስትመንት መሬት አስተዳደር ኤጀንሲ የህንዱ ኩባንያ ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል ሰዎች በገፍ እየታሰሩ ነው፣ አቶ በቀለ ነገአ እንደተደበደቡ ገለጹ
ኢሳት (ታህሳስ 21 ፣ 2008) በበርካታ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ከተቀሰቀሰው ተቃውሞ ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች እየታሰሩ እንደሆነ ከሃገር ቤት የተገኘው መረጃ አመልክቷል። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራሮች ላይ እየተካሄደ ባለው በዚሁ ዘመቻ ከ4ሺ የሚበልጡ አባላት ለእስር መዳረጋቸውን ገልጸዋል። ይሁንና የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለውን የእስር ዘመቻ በመቀጠሉ ቁጥሩ በየእለቱ እየጨመረ መምጣቱንና ትክክለኛ ቁጥሩን በአንድ ጊዜ መግለጽ አስቸጋሪ ኣየሆነ መምጣቱን ...
Read More »