ታኀሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሽብረተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው ከፍተኛው ፍርድ ቤት በነጻ ያሰናበታቸው ታዋቂዎቹ ፖለቲከኞች ሃብታሙ አያሌው፣ የሺዋስ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ዳንኤል ሽበሺ እንዲሁም አብርሃም ሰለሞን ፣ አቃቢ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ነጻ ከተባሉትበት ከነሃሴ 14 ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ። ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው ታህሳስ 29/2008 ዓ.ም ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኑ ላይ ብይን ይሰጣል ተብሎ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኢትዮጵያ የአእምሮ በሽተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው
ታኀሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከቅርብ ኣመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የአእምሮ ጤና መቃወስን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፉ መምጣታቸውን፣ መንግስትም ችግሩን ለመከላከል በቂ የሆነ ጥረት እንዳላደረገ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ አመለከተ፡፡ ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች መካከል የካንሰር ሕመም ፣ የአእምሮ ህመም፣ ከውፍረት ጋር የተያያዙ የጤና ችግሮች፣ ከአልኮልና የትምባሆ እንዲሁም ከአደገኛ ዕጾች ጋር የተያያዙ የጤና ...
Read More »ኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ያነሱት የመብት ጥያቄ ተገቢ ነው፣ የትጥቅ ትግል የጀመሩትን መደገፍ አለብን ሲሉ ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ አስታወቁ
ኢሳት (ታህሳስ 29 ፣ 2008) የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ያነሱት የመብት ጥያቄ ተገቢና የሚግደገፍ ነው ሲሉ ታዋቂው ኢትዮጵያዊ ምሁር ገለጹ። በከተሞች መስፋት ሃብታም የመሆን እድል የልተመቻቸለት አርሶ አደሮች ወደ ድህነት እየተገፉ፣ ባለጊዜ በዕርሱ መሬት እንዲበለጽግ መንገድ ሲጠርግ ተቃውሞ መጀመራቸው ትክክል ነው ያሉት ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ፣ ይህ በኦሮሞዎች ላይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ላይ ሊደርስ የሚችል በመሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሊያወግዙት እንደሚገባ ለኢሳት በሰጡት ...
Read More »የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተከትሎ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ተጠናክሮ ቀጥሏል
ኢሳት (ታህሳስ 29, 2008) የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተከትሎ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው ተቃውሞ ትናንትም በተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሎ መዋሉ ታወቀ። በትናንትናው ዕለትም በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች እና በአንዳንድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መንግስት እየወሰደ ያለውን ዕርምጃ በመቃወም የተለያዩ ህዝባዊ እምቢተኝነቶች መካሄዳቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በትናንትናው ዕለት የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ 5 ኪሎ ካምፓስ ተማሪዎች ለገና በዓል የተዘጋጀውን ምግብ ባለመመገብ ...
Read More »የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ መሮቆርዮስ ኢትዮጵያውያና በፍቅርና በሰላም ተከባብረው እንዲኖሩ፣ አገራቸውን እንዲጠብቁ ጥሪ አቀረቡ
ኢሳት (ታህሳስ 29 ፡ 2008) ኢትዮጵያውያን በፍቅርና በሰላም ተከባብረው እንዲኖሩ፣ አድነታቸውን እንዲጠብቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ መሮቆርዮስ ጥሪ አቀረቡ፥ በኦሮሚያ ክልል ለተቃውሞ አደባባይ በወጡ ኢትዮጵያውያን ላይ መንግስት በወሰደው የመግደልና የእስር እርምጃ ማዘናቸውን ገልጸው፣ ለሟች ለቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል። ፓትሪያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የኢየሱስ ክርስቶስን 2ሺ 8ኛ አመት የልደት በዓል በማስመልከት ለኢትዮጵያውያን ትናንት ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ግዛት ወደሱዳን ተላልፎ ...
Read More »በኦሮምያ የሚካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ የታሰሩት እንደፈቱ ሂውማን ራይትስ ወች ጠየቀ
ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰብአዊ መብት ድርጅቱ በምስራቅ አፍሪካ ተመራማሪው ፌሊክ ሆርን በኩል ባወጣው መግለጫ፣ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ መታሰራቸውን ተከትሎ ግጭቱ እየተባባሰ መምጣቱንና በእስካሁኑ ተቃውሞ 140 ሰዎች መገደላቸውን ጠቅሷል። አቶ በቀለ ገርባና ሌሎችም እስረኞች እንዲፈቱ የጠየቀው ሂውማን ራይትስ ወች፣ ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻነት እንዲገልጹ እንዲፈቀድላቸው፣ አርሶአደሮችን በዘፈቀደ ማፈናቀል እንዲቆምና በቂ ምክክር እንዲደረግ አሳስቧል። ...
Read More »ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት መከሰቱን ነጋዴዎች ተናገሩ
ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንግድ ድርጅት ባለቤቶች ለኢሳት እንደገለጹት በአሁኑ ሰአት የተከሰተው የዶላር እጥረት ከምርጫ 97 በሁዋላ ከፍተኛው ነው። በአስመጭነትና ላኪነት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በውጭ ምንዛሬ እጥረት ስራቸውን ለመስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ፋብሪካዎች የመለዋወጫ እቃዎችን ለመግዛት በመቸገራቸው እንቅስቃሴያቸው በእጅጉ ተዳክሟል። በተለይ የግንባታ እንቅስቃሴው በእጅጉ መዳከሙን ነጋዴዎች ይገልጻሉ። በአገሪቱ የተፈጠረውን ከፍተኛ ድርቅ ለማቋቋም መንግስት ...
Read More »በባህርዳር እስረኞች ለ2 ቀናት በቤተሰብ እንዳይጠየቁ ተደረጉ
ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው እሁድ የእስር ቤቱ ሃላፊዎች ” በእስር ቤቱ ውስጥ ቦንብ ገብቷል” የሚል መረጃ ደርሶናል በሚል እስር ቤቱን በአድማ በታኝ ፖሊሶች አጥለቅልቀውና ዋናውን መንገድ በመዝጋት ጠያቂዎች እንዳይገቡ ከልክለዋል። በዚሁ ሰበብ በእስረኞች ላይ ከፍተኛ እግልት የደረሰ ሲሆን፣ ለሁለት ቀናት ያክል እስረኞች በቤተሰቦቻቸው እንዳይጠየቁ አግደዋል። በእስር ቤቱ ውስጥም ከፍተኛ ፍተሻ ተካሂዷል። ዛሬ ታህሳስ 28 ...
Read More »በትግራይ አርሶአደሮች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ታህሳስ 22፣ 2008 ዓም በመቶዎች የሚቆጠሩ አርሶአደሮች ተቃውሞውን ያካሄዱት የበለስ ምርታችን በተሳሳተ ምርምር ወድሞብናል በሚል ምክንያት ነው። አርሶአደሮቹ ከዋጅራት ተነስተው በእግራቸው ወደ መቀሌ የገሰገሱ ሲሆን፣ አዲግዶም ላይ ፖሊሶች በሃይል በትነዋቸዋል። አርሶአደሮቹ እንደሚሉት ለምርምር በሚል የገባው በሽታ ፣ የበለስ ምርቱን በከፍተኛ ሁኔታ በመጉዳቱ በህልውናቸው ላይ አደጋ ፈጥሯል። መንግስት በሽታውን ያመጡትን ተመራማሪዎች ለፍርድ ...
Read More »በኒውዚላንድ የሚኖሩ ሴቶች ገንዘብ አሰባስበው ለአርበኞች ግንቦት7 ለገሱ
ታኀሳስ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኒዉዚላንድ ዌሊንግቶን የሚኖሩ ሴቶች ፣ በበረሃ ውስጥ ያሉ ሴቶችን ለመርዳት በሚል ተነሳስተው ለአርበኞች ግንቦት ሰባት የሴት ታጋዮች ፍጆታ የሚዉል ገንዘብ መለገሳቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል። ሴቶቹ ይህ ጅማሪ እንጂ የመጨረሻዉ እንደማይሆን፣ ለወደፊቱ ራሳቸዉን በማደራጀት ቀጣይ የሆነ እርዳታ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። በገና በዓል ቀን ሴት እሕቶቻችን በጫካ ለኛ ነፃነት ሲታገሉ እኛ የተመቻቸ ...
Read More »