ኢሳት (ጥር 2 ፥ 2008) በጎረቤት ሶማሊላንድ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያዊ ስደተኞችን ይዞ ይጓዝ የነበረ ጀልባ የመስጠም አደጋ አጋጥሞት በትንሹ 112ቱ መሞታቸውን የሶማሊላንድ ባለስልጣናት ሰኞ አስታወቁ። ራሷን ነጻ ሃገር አድርጋ ባወጀችው ሶማሊላንድ በደረሰው የጀልባ አደጋ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩንም የነብስ አድኑ ሰራተኞች ገልጸዋል። በጀልባው ላይ ከደረሰው አደጋ 75 ሰዎችን መታደግ እንደተቻለና ስደተኞቹን ይዞ ይጓዝ የነበረው ጀልባ የቴክኒክ ችግር ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኦሮምያ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ህዝባዊ ተቃውሞውን ግንባር ቀድም ሆነው እየመሩት ነው
ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወር በላይ ያስቆጠረው በኦሮምያ የሚካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደገና በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ሃይሉን ጨምሮ ሲካሄድ ሰንብቷል። መንግስት ከፍተኛ ሰራዊት በማሰማራትና ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ በመውሰድ ተቃውሞውን ለማብረድ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም በክልሉ የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በሚጫወቱት የመሪነት ሚና ተቃውሞ አድማሱን አስፍቶ ቀጥሎአል።በጀማ፣አሮማያ፣ መዳወላቡ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች በክልሉ እየተፈጸሙ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ከማወገዛቸውም በላይ፣ ተቃውሞውን ተከትሎ ...
Read More »የወልቃይትን ህዝብ ለማሳመን የተላከው ቡድን እስካሁን አልተሳካለትም
ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ያለፍለጎታቸውን ወደ ትግራይ ክልል በመጠቃለላችን ወደ አማራ ክልል እንዛወር በማለት የጠየቁ የወልቃይት ነዋሪዎችን ሲያግባባ የነበረው ከአማራ ክልል ከልዩ ልዩ መስሪያ ቤቶች የተወጣጣው ቡድን ለአንድ ወር ያክል ጊዜ በአካባቢው ተሰማርቶ የማሳመን ስራ ለመስራት ቢሞክርም እስካሁን ተልዕኮው ባለመሳካቱ ለተጨማሪ ጊዜ በወልቃይት ለመክረም ተገዷል፡፡ የክልሉ ጸጥታ ጉዳዮች፣ ፍትህ፣ፖሊስና መከላከያን ጨምሮ በርካታ የመንግስት ተሿሚዎችን ያካተተው ቡድን ...
Read More »ኢትዮጵያ በተመድ የልማት ፕሮግራም መስፈረት የ174ኛ ደረጃን ያዘች
ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት የልማት ፕሮግራም UNDP ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ ከ188 የአለም አገራት 174ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ገልጿል። ድርጅቱ የኢኮኖሚ እድገትን፣ ልማትን፣ የጸጥታ ጉዳዮችን ፣ የፖለቲካ ነጻነትንና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮችን በማጥናት የሚያወጣው ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ ካለፈው አመት ከነበረችበት ደረጃ ዘንድሮ አንድ ደረጃ ዝቅ ብላለች። በአለማ ላይ ካሉት አገራት ኢትዮጵያ መብለጥ የቻለችው 14 አገራትን ብቻ ሲሆን፣ ሁሉም ...
Read More »ወደ የመን በጀልባ ሲጓዙ ከነበሩ ስደተኞች ውስጥ 122 የሚሆኑት ሕይወታቸውን አጡ
ጥር ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መነሻቸውን በሶማሌላንድ ሳናጋ ግዛት አድርገው በተጨናነቀ ጀልባ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ባሕር አቆራርጠው ወደ የመንና የገልፍ አገራት ለመግባት ሲጓዙ ከነበሩት ኢትዮጵያዊያንና ሶማሊያዊያን ዜጎች ውስጥ አብዛኞቹ መሞታቸውንና ከሟቾቹ ውስጥ 122 የሚሆኑት አስከሬናቸው በባህር ዳርቻዎች መገኘቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል። ከአደጋው ሕይወታቸው የተረፈ 80 ኢትዮጵያዊያን መኖራቸውንና በድንበር ጠባቂዎች መያዛቸውን ዘገባው ገልፆ ፣ ከተያዙት ውስጥ አብዛኞቹ በምግብ ...
Read More »በማስተር ፕላን ሰበብ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል፥ የመማር ማስተማር ሂደትን አስተጓጉሏል
ኢሳት (ታህሳስ 29 ፥ 2008) ከቀናት በፊት ዳግም ያገረሸው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ አርብ በምዕራብ ሃረርጌ በምትገኘው የጭሮ ከተማና አካባቢዋ ቀጥሎ መዋሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በሌሎች አካባቢዎች የተወሰደው አይነት የመንግስት ታጣቂዎች እርምጃም በከተማዋ ተካሄዶ በርካታ ሰዎች ለእስር መዳረጋቸው ተገልጿል። ከቀናት በፊት በዚሁ በምዕራብ ሃረርጌ በምትገኘው የሂርና ከተማ ተቀስቅሶ የነበረው ተቃውሞ አለመብረዱንና አርብ በከተማዋና በዙሪያው ባሉ የገጠር መንደሮች ...
Read More »በኢትዮጵያ 1 ሚሊዮን የቤት እንስሳት በረሃብ መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ
ኢሳት (ታህሳት 29 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በሚገኙ ስድስት ክልሎች ጉዳትን እያደረሰ ባለው የድርቅ አደጋ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ የቤት እንስሳት በረሃብ ምክንያት መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጠ። በዚሁ የድርቅ አደጋ ወደ ሁለት ሚሊዮን የቤት እንስሳት ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በህይወት የመቆየት እድላቸውም አደጋ ውስጥ መሆኑን ድርጅቱ በድርቁ ዙሪያ ባወጣው ረፖርት አመልክቷ። ድርቁ ከፍተኛ ጉዳት ባስከተለባቸው የአማራ፣ ኦሮሚያ እና የደቡብ ክልሎች ...
Read More »በማስተር ፕላን ተቃውሞ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ140 ማለፉን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ
ኢሳት (ታህሳስ 29 ፥ 2008) በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ቀጥሎ የሚገኘው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ በመንግስት ወታደሮች የተገደሉ ሰዎች ቁጥር በትንሹ 140 መድረሱንና ተቃውሞው አለመርገቡን በርካታ አለም-አቀፍ መገናኛ ብዙሃን አርብ ዘገቡ። ዳግም አገርሽቶ የሚገኘው ይኸው ተቃውሞ አርብ በምዕራብ ሃረርጌ በሚገኙ ሂርናና ጭሮ (አሰበ ተፈሪ) ከተማ መቀስቀሱንና፣ የመንግስት ወታደሮችና ፖሊሶች እርምጃ መውሰዳቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ሁለተኛ ወሩን በያዘውና ...
Read More »በአርባምንጭ የሚገኘው የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ጣቢያ በኢትዮጵያ ጥያቄ የተዘጋ መሆኑ ታወቀ
ኢሳት (ታህሳስ 29 2008) በደቡብ ኢትዮጵያ አርባ ምንጭ ከተማ ላለፉት 5 አመታት ያህል ሲያገለግል የቆየው የአሜሪካ የሰው አልባ የስለላና የውጊያ አውሮፕላን (ድሮን) ጣቢያ መዘጋት የሃገሪቱን ግንኙነት የሚጎዳ ዕርምጃ መሆኑ ተመልክቷል። ዩ ኤስ አሜሪካ የድሮን ጣቢያው አላስፈላጊ በመሆኑ መዘጋቱን በወቅቱ ብትገልጽም፣ የኢትዮጵያ መንግስት ቃለ አቀባይ ረቡዕ በሰጡት መግለጫ የድሮን ጣቢያው በኢትዮጵያ ጥያቄ መዘጋቱን ይፋ አድርገዋል። በዓለም-አቀፍ ደረጃ በውጭ ግንኙነት ፖሊሲዎች ላይ ...
Read More »አቶ በቀለ ነገአ በቁም እስር ላይ ናቸው
ታኀሳስ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦፌዴን ሊቀመንበር አቶ በቀለ ነገአ በደህንነት ሃይሎች ታፍነው ተወስደው ድብደባ ከተፈጸመባቸው በሁዋላ፣ ከቤት ወጥተው ስራቸውን ለማከናወን ባለመቻላቸው በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ ከባልደረቦቻቸው የተገኘው መረጃ አመልክቷል። ሌላው የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ባልታወቀ ስፍራ ተወስደው የታሰሩ ሲሆን፣ አቶ በቀለ ነገአ ግን ማንኛውንም አይነት መግለጫ ለመገናኛ ብዙሃን እንዳይሰጡ እንዲሁም ከቤታቸው እንዳይወጡ ...
Read More »