.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሃረማያ ዩንቨርስቲ የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ በአጎራባች ቀበሌዎች ተዛመተ

ኢሳት (ጥር 4 ፥ 2008) ሰኞ በሃረማያ ዩንቨርስቲ የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ በአካባቢው መዛመቱንና በአካባቢው ውጥረቱ አለመርገቡን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የዩንቨርስቲው አስተዳደር ተማሪዎች መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ ቢያቀርብም ተማሪዎቹ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በምስራቅ ሃረርጌ አካባቢ ባሉ ከተሞች ረቡዕ ተመሳሳይ ተቃውሞ ሲያካሄዱ ያረፈዱ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ከፍተኛ ተቃውሞ በመካሄድ ላይ መሆኑም ታውቋል። ተቃውሞው በአዲስ መልክ ቀጥሎ ...

Read More »

ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የጸጥታና የደህንነት ሃላፊዎች በናዝሬት ከተማ ተሰበሰቡ

ኢሳት (ጥር 4 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ በርካታ ከተሞች ዳግም የተቀሰቀሰውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ተከትሎ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ከፍተኛ የጸጥታና የደህንነት ሃላፊዎች በናዝሬት አዳማ ከተማ ሃገር አቀፍ ምክክር ጀመሩ። በዚሁ በሶስት ቀናቶች በሚቆየው ሃገር አቀፍ የጸጥታ ምክክር ከ200 በላይ የፌዴራልና የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች እንዲሁም ከፍተኛ የጸጥታ ስራ ሃላፊዎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። በአይነቱ የመጀመሪያው ነው በተባለው በዚሁ ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደው ስላለው ተቃውሞ ከዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ማብራሪያ ጠየቀ

ኢሳት (ጥር 4 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ዋነኛ የልማት አጋር የሆነው የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በህብረቱ ዋና መቀመጫ ብራሰልስ ከተማ ተገኘተው በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ስላለው ተቃውሞ ማብራሪያን እንዲሰጡ ጠየቀ። ሆኖም የተዘጋጀላቸውም ጋዜጣዊ መግለጫ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ተሰርዟል። የቀረበላቸውን ጥያቄ ተከትሎ በብራሰልስ የሚገኙት ዶ/ር ቴዎድሮስ በጉዳዩ ዙሪያ ከህብረቱ አባል ሃገራት በርካታ ጥያቄዎች ይቀርብላቸዋል ተብሎ በመጠበቅ ላይ መሆኑን ...

Read More »

ኦህዴድ ማስተር ፕላኑን ትቼዋለሁ ቢልም ተቃውሞ ግን ቀጥሎአል

ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ አንድ ክንፍ የሆነው የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መተውን ባስታወቀ ማግስት በአምቦ፣ በአርሶ ኬፈሌና በሌሎችም የኦሮምያ ክፍሎች ተቃውሞው ቀጥሎአል። በአምቦ የተካሄደው ተቃውሞ ደም አፋሳሽ የነበረ ሲሆን፣ አንድ ሰው መገደሉና በርካቶች መቁሰላቸው ታውቋል። ከቆሰሉት መካከል ህጻናትም ይገኙበታል። ከአምቦ ከተማ በተጨማሪ በ ጃርሶ ወረዳ ቀሬ ጎሓ ...

Read More »

የወልቃይትን ህዝብ ትግል የሚያስተባብሩ ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች እየተዋከቡ ነው

ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “የወልቃይት ሕዝብ አማራነቱ ይከበርለት” በማለት ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ በፌዴራልና በአማራ ክልል እየቀረቡ አቤቱታ ሲያሰሙ የነበሩ የኮሚቴ አባላት ወደአካባቢቸው በሰላም ለመመለስ መቸገራቸው ታውቋል። “የወልቃት ሕዝብ አማራ ነው፣ በትግራይ ክልል ሊተዳደር አይገባም” በማለት ጥያቄ ያነሱት ተወላጆች፣ የትግራይ ክልል አሁንም ጥያቄ የሚያቀርቡ ወገኖችን በተናጠልና በጋራ በማጥቃትና በማሳደድ ስራ በመጠመዱ ምክንያት የኮምቴ አባላቱ ያለስጋት ...

Read More »

በቀን ከ150 በላይ ኢትጵያዊያን ከአገራቸው ይሰደዳሉ ተባለ

ጥር ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከስደተኛ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ውስጥ አብዛሃኞቹ በእድሜ ወጣቶች ሲሆኑ፣ በጾታ ስብጥር ደግሞ በመቶኛ ሲሰላ 94 ከመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ተከላካይ ኮሚቴ በሂልተን ሆቴል ባካሄደው የውይይት መድረክ ላይ ለፍልሰቱ ዋናው ምክንያት ሥራ አጥነትንና ሕገወጥ ደላሎችን በምክንያትነት አቅርቧል። ወላጆች ተበድረው ለደላላ በመክፈል ልጆቻቸውን ወደ ውጭ ሀገራት እንደሚልኩ ...

Read More »

ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ 760 ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ ያስፈልጋል ተባለ

ኢሳት (ጥር 3 ፥ 2008) በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው የእርዳታ መጠን ከ760 ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ መድረሱን መንግስት ማክሰኞ ባቀረበው የእርዳታ ጥያቄ አስታወቀ። አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በበኩላቸው ለምግብ እርዳታ የተጋለጡ ሰዎች በቀጣዮቹ ሶስት ወራቶች ውስጥ ድጋፍ ካልጀመሩ ችግሩ የከፋ እንደሚሆን በድጋሚ አሳስበዋል። ከ10 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ተረጂዎች የእርዳታ ጥሪን ያቀረቡ ...

Read More »

የአክሰስ ሪል ስቴትና የዘመን ባንክ መስራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ታሰሩ

ኢሳት (ጥር 3 ፥ 2008) የአክሰስ ሪል ስቴት እንዲሁም የዘመን ባንክ መስራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ መታሰራቸውን ከአዲስ አበባ የደረስን ዜና አመለከተ። በመንግስት ዋስትና ወደሃገር ቤት ከተመለሱ ወራት ብቻ ያስቆጠሩት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ ተመልሰው የታሰሩበት ዝርዝር ምክንያት ባይገለጽም፣ ከአክሰስ ሪል ስቴት ጋር የተያያዘ መሆኑን የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሃይላንድ ውሃን በማምረት ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ በመግባት በንግዱ አለም ታዋቂ የሆኑት አቶ ...

Read More »

የግቡፁ ፕሬዚዳንት ከመከላከያና ደህንነት ሃላፊዎች ጋር በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ መከሩ

ኢሳት (ጥር 3 ፥ 2008) የግቡፁ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ከሃገራቸው የመከላከያና ደህንነት ሃላፊዎች ጋር በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ መምከራቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ማክሰኞ ዘገቡ። ሰኞ በተካሄደው በዚሁ ዝግ ውይይት ፕሬዚደንቱ በቅርቡ ተደርሰዋል በተባሉ ስምምነቶችና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በሰፊው መምከራቸውን አል-አህራም የተሰኘ ጋዜጣ አስነብቧል። ፕሬዚደንቱ ከከፍተኛ የመከላከያና የደህንነት ሃላፊዎች ጋር ምክክርን አካሄደዋል ቢባልም ውይይቱ በዚህ ደራጃ ለምን እንደተካሄደና በምን አበይት ...

Read More »

የመንግስት ባለስልጣን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤትን እንዲመሩ ተመረጡ

ኢሳት (ጥር 3 ፥ 2008) ማክሰኞ በይፋ የተቋቋመንውን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤትን እንዲመሩ አንድ የመንግስት ባለስልጣን በዋና ፀሃፊነት ተመረጡ። በሃገር ውስጥ የሚገኙ ጋዜጠኞችንና አሳታሚ ድርጅቶችን ያስተዳድራል የተባለውን ይህንን ምክር ቤት በሃላፊነት ለመምራት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ  ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ገብረመድህን ለምክር ቤቱ ዋና ጸሃፊ ሆነው ተመርጠዋል። ለጋዜጠኞች መብት መከበርና ለሙያው ድጋፍን ያደርጋል ለተባለው ለዚህ ምክር ቤት የረፖርተር ...

Read More »