.የኢሳት አማርኛ ዜና

በዲላ ከተማ የነዳጅ እጥረት መፈጠሩን ነዋሪዎች ተናገሩ

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለመግዛት ተቸግረናል ሲሉ ፣ የነዳጅ ማደያ ባለሃብቶች በበኩላቸው መንግስት ያለንን ትንሽ መጠንም ቢሆን ከመንግስት ፈቃድ ውጭ እንዳትሸጡ ተብለናል እያሉ ነው፡፡ አንድ ሳምንት በዘለቀው ችግር የባጃጅ ባለንብረቶች ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል። የችግሩ መንስኤ በነዳጅ እጥረት ቢሳበብም በአለም ደረጃ በ12 አመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ዋጋ ከ30 ዶላር በታች በሚሸጥበት ወቅት በሃገር ውስጥም ...

Read More »

በታንዛኒያ 83 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ተያዙ

ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የታንዛኒያ ፖሊስ በሚቢያ ግዛት ማሂንቤ መንደር ውስጥ ሕገወጥ ስደተኞች ያላቸውን ተደብቀው የነበሩ ቁጥራቸው ከ83 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዙን አስታውቋል። የክልሉ የፖሊስ ኮማንደር የሆኑት ፒተር ካካምባ ስደተኞቹ በሕገወጥ መንገድ በከባድ መኪና በኮንትሮባንድ ተጭነው ወደ ማላዊ ለመሻገር ሲሞክሩ ተይዘዋል ብለዋል። ታንዛኒያዊ ሾፌርና ሕገወጥ ስደተኛ አዘዋዋሪ የሆነችው ሃና ሚካኖዮማ በአካባቢው ነዋሪዎች ጥቆማ አብረው ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

ኢሳት (ጥር 6 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል ዳግሞ ቀጥሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ አርብ በምስራቅ ሃረርጌ እንዲሁም በምዕራብ ሸዋ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲካሄድ መዋሉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎችና ተማሪዎች የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለውን እርምጃ በማውገዝ የተቃውሞ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸውን ታዉቋል። ይሁንና የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለመበተን በወሰዱት እርምጃ በርካታ ተማሪዎች ለእስር የተዳረጉ ሲሆን ተመሳሳይ ተቃውሞም በምዕራብ ወለጋ ...

Read More »

ሃሳባቸውን በነጻነት በሚገልጹት አካላት ላይ ኢትዮጵያ የምትወስደውን ሰብዓዊ መብት ረገጣ እንድታቆም አሜሪካ ጠየቀች

ኢሳት (ጥር 6 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ሃሳባቸውን በነጻነት በሚገልጹ አካላት ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆም የአሜሪካ መንግስት አሳሰበ። በወቅታዊ የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ዙሪያ በድጋሚ መግለጫን ያወጣው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በተቃዋሚ አባላትና አመራሮች እንዲሁም በጋዜጠኞች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ አሳስቦት እንደሚገኝ ገልጿል። እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችም ፖለቲካዊ ችግሮችን ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን መፍትሄን ለማፈላለግ በሚያድርጉ ጥረቶች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩ የአሜሪካ ...

Read More »

በሳምንት ውስጥ 2 ታሳሪዎች በቂሊንጦ እስርቤት ሞቱ

ኢሳት (ጥር 6 ፥ 2008) አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሙባረክ ይመር እና ጉደታ ኦላንሳ የተባሉ ኢትዮጵያውያን በቂሊንጦ እስርቤት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ መሞታቸው ተነገረ። ከድምጻችን ይሰማ የኢትዮጵያ ሙዝሊም እንቅስቃሴ እነ እንድሪስ መሃመድ መዝገብ ጋር በተያያዘ ከወሎ የታሰረው 9ኛ ተከሳሽ ሙባረክ ይመር መሞቱ ታውቋል። በአዲስ አበባ በመስራቅ አቅጣጫ ከከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቂሊንጦ እስር ቤት ከሁለት አመታት በላይ በእስር የቆየው ሙባረክ ...

Read More »

በድርቅ ምክንያት በአንዳንድ አካባቢዎች 90 በመቶ የሚሆን ሰብል ወደመ፣ የዋጋ ንረት ያስከትላል ተብሎ ተፈርቷል

ኢሳት (ጥር 6 ፥ 2008) በተያዘው አመት በኢትዮጵያ በተከሰተው የድርቅ አደጋ በአንድአንድ አካባቢዎች 90 በመቶ የሚሆን የእርሻ ሰብል መውደሙንና  የዕህል ዋጋ ንረት አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የለአም ምግብ ድርጅት ፕሮግራም (FAO) አርብ አስታወቀ። በተለይ በምስራቅ የሃገሪቱ ክፍል በተከሰተው ድርቅ የእርሻ ሰብሎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውንና የድርቁ አደጋ ገጽታውን እየቀየረ መምጣቱን ድርጅቱ ገልጿል። መቀመጫውን በጣሊያን ሮም ከተማ ያደረገው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሊያካሄድ ላሰበው ...

Read More »

የአዲስ አበባ ተቀናጀ ማስተር ፕላን  የተጠራቀሙ የጭቆናና አፈና ችግሮች እንዲፈነዱ ያደረገ ክስተት ነው ተባለ

ኢሳት (ጥር 5 ፥ 2008) የአዲስ አበባ የተቀናጀ ማስተር ፕላን የተጠራቀሙ የጭቆናና አፈና ችግሮች እንዲፈነዱ ያደረገ ክስተት ነው ሲሉ በአዲስ አበባ ዙሪያ የመሬት መፈናቀል ጥናትና ምርምር እያደረጉ ያሉት አቶ ብርሃኑ ሌንጂሶ ለኢሳት ገለጹ። መሬት ለመንግስት የስልጣን ምንጭ፣ ለገበሬው የህልውና መሰረት ነው ያሉት አቶ ብርሃኑ፣ መንግስት የህልውና መሰረት የሆነውን የገበሬውን መሬት በመንጠቅ እንደማስፈራሪያ እየተጠቀመበት እንደሆነ ለኢሳት ገልጸዋል። የመሬት ቅርምት ማለት ያልተተገበረ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ሰበብ እየሞቱ ያሉ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ ነው ተባለ

ኢሳት (ጥር 6 ፥ 2008) ሁለተኛ ወሩን በያዘው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ፣ በየዕለቱ የሚገደሉ ሰዎችና ለእስር የሚዳረጉ ተማሪዎች ቁጥር በማሻቀብ ላይ መሆኑ ሂውማን ራይትስ ዎች አርብ ጃንዋሪ 15 አስታወቀ። በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ቀጥሎ በሚገኘው በዚሁ ተቃውሞ የሟቾችንም ሆነ ለእስር የተዳረጉ ነዋሪዎችን ቁጥር በአግባቡ ማወቅ እንዳልተቻለም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጀት ለሁለተኛ ጊዜ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል። ሃሙስ ከሌሎች ሁለት አለም ...

Read More »

ሂውማን ራይትስ ወች “መንግስት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን መሰረዙ ለተቃዋሚዎች ትልቅ ድል ቢሆንም ውሳኔው ዘግይቷል” አለ

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሂውማን ራይትስ ወቹ ፍሊክስ ሆርን ፣ ደም አፋሳሽ ከሆነው የ9 ወራት ተቃውሞ በሁዋላ መንግስት ተቃዋሚዎች ላቀረቡት ጥያቄ ፣ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመሰረዝ መልስ ቢሰጥም፣ ኦሮምያን ለማረጋጋት ግን የዘገየ ውሳኔ ነው ብሎአል። መንግስት ተቃዋሚዎች ላቀረቡት ጥያቄ መልስ መስጠቱ ያልተለመደ ነው የሚለው ሆርን፣ ለተቃዋሚዎች ደግሞ ትልቅ ድል ነው መሆኑን ገልጿል። በመጀመሪያ ተቃውሞው ...

Read More »

“ያለንበት ዘመን ጨለማና መከራ የበዛበት ነው”ሲሉ አርሶአደሮች ተናገሩ

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በድርቁ በተጎዱ የአማራ ክልል አካባቢዎች በመዘዋወር ተጎጂዎችን ለተመለከቱት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ያለባቸውን ችግር የተናገሩት አርሶአደሮች ‹‹ አሁን ያለንበት ዘመን አስከፊ የሆነ አሰቸጋሪ ጊዜ ነው ፡፡››በማለት እየደረሰባቸው ያለውን የውሃ ችግር በምሬት ቢናገሩም እስካሁን ምንም መፍትሄ እንዳልተሰጠ ተጊጂዎች ቅሬታቸውን ተናግረዋል፡፡ ‹‹ የደረሰብን ድርቅ ታይቶ የማይታወቅ እጅግ አሳዛኝ ነው ›› ያሉት ተጎጂዎች ዛሬ የደረሰብን ...

Read More »