.የኢሳት አማርኛ ዜና

ጥር ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየመን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ አስታወቀ

በአውሮፓዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2015 ቁጥራቸው ከ100 ሽህ በላይ የሚሆኑ የኢትዮጵያዊያንና የሶማሊያ ስደተኞች ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው በጀልባ የመን ገብተዋል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት ቃል አቀባይ የሆኑት አድሪያን ኤዲዋርድስ ” ስደተኞቹ ወደ የመን የሚያደርጉት የባሕር ጉዞዋቸውና የመን ውስጥ ከገቡ በኋላ የሚጠብቁዋቸው ሁኔታዎች በጣም አደገኛ ነው። ከሁለት ሳምንት በፊት 36 የሚሆኑ ስደተኞች በጀልባ ሲጓዙ ሰምጠዋል” ሲሉ ስደተኞቹ ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን አስታውቀዋል። ወደ ...

Read More »

ለቤተ እስራኤላዊያን ማቋቋሚያ ልዩ በጀት ተመደበላቸው

ጥር ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የእስራኤል መንግስት በአገሩ ውስጥ ለሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ቤተእስራኤላዊያን ማኅበረሰብ አባላት ማቋቋሚያ ይሆን ዘን 55 ሚሊዮን የእስራኤል ሻክል መመደቡን አስታውቋል። ቁጥራቸው ከ 3 ሽህ 600 በላይ የሚሆኑት ቤተ-እስራኤላዊያን ከተቀረው የእስራኤል ማኅበረሰብ ጋር የውህደት መስተጋብር ያደርጉ ዘንድ ያስችላል የተባለውን ውሳኔ የአገሪቱ ፓርላማ በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል። የቤተ እስራኤላዊያንን አቅም በመገንባት በትምህርትና በሥራ መስክ ...

Read More »

የግብፅ መንግስት 45 የኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱዳንና ማሊ ዜጎችን ወደሃገራቸው መለሰ

ኢሳት (ጥር 10  ፥ 2008) የግብፅ መንግስት በህገ-ወጥ መንገድ ወደሃገሪቱ ገብተዋል ያላቸውን 45 የኢትዮጵያ፣ ኬንያ ሱዳንና ማሊ ዜጎችን ወደሃገራቸው መመለሱን ማክሰኞ ገለጠ። በሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉት እነዚሁ ስደተኞች ወደ እስራኤልና ሊቢያ የመጓዝ እቅድ እንደነበራቸው ዘ-ካይሮ ፖስት ጋዜጣ አስነብቧል። ስደተኞቹ ወደሃገራቸው የመመለሱ ሂደትም በግብፅ ከሚገኙ ኢምባሲዎች ጋር ምክክር ተካሂዶበት መሆኑን ጋዜጣው የደህንነት ምንጮች ዋቢ በማድረግ በዘገባው አመልክቷል። ይሁንና ከስደተኞቹ መካከል ...

Read More »

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ የተነሳት ተቃውሞ አሁንም በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች እንደቀጠለ ነው

ኢሳት (ጥር 10 ፥ 2008) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በተቃውሞ ለሚሳተፉ አካላት ጥረትን ቢያቀርብም ዳግም የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች መቀጠሉ ተገለጠ። በምስራቅ ሃረርጌ መኢሶ አካባቢ በሳምንቱ መገባደጃ የተጀመረው ተቃውሞ ለአራተኛ ቀን መቀጠሉንና ነዋሪዎች በጸጥታ ሃይሎች የሚወስዱ ግድያዎች እንዲያቆሙ መጠየቃቸው ታውቋል። ሰኞ የክልሉ መንግስት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በተቃውሞ የተሳተፉ አካላትን በሆደ-ሰፊነት እንደሚመለከት በመግለፅ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን እንዲያቆሙ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ያለው አለመረጋጋት ኢኮኖሚው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል አንድ አለም አቀፍ ተቋም ገለጸ

ኢሳት (ጥር 10 ፥ 2015) ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በሃገሪቱ ያለው አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ግሎባል ሪስክ ኢንሳይት (Global Risk Insight) የተሰኘ የፋይናንስ ተቋም ማክሰኞ አስታውቋል። በኦሮሚያ ክልል ቀጥሎ የሚገኘው ይኸው ተቃውሞ የፖለቲካ አለመረጋጋት እንዲፈጠር በማድረግ በውጭ ባለሃብቶች ዘንድ ስጋትን እንደሚፈጥር ተቋሙ ገልጿል። በኢትዮጵያ ያለው የኢኮኖሚ እድገት ሁሉን አሳታፊ መሆን እንዳለበት ያሳሰበው ድርጅቱ በልማት ...

Read More »

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድቤት በነጻ በተሰናበቱትና በይግባኝ ጉዳያቸው ሲታይ በነበሩት አመራሮች ላይ ሊሰጥ የነበረውን ብይን ለሁለተኛ ጊዜ አራዘመ

ኢሳት ( ጥር 10 ፥ 2008) የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከቀረበባቸው የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ነጻ ተሰናብተው ጉዳያቸው በይግባኝ በመታየት ላይ ባሉ አምስት የፓርቲ አመራሮች ላይ ሊሰጥ የነበረን ብይን ለሁለተኛ ጊዜ አራዘመ። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ አቃቤ ህግ ከብሄራዊ ደህንነት ተገኝቷል የተባለ ማስረጃ “ኦሮጂናሉ” እንዲቀርብ ሲል ማክሰኞ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ፍርድ ቤቱ ባለፈው ቀጠሮው “የምንመረምረው ነገር አለ” ...

Read More »

በሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎች የተከሰተው ውሃ-ወለድ ወረርሽ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ጉዳት አደረሰ

ኢሳት (ጥር 10 ፥ 2008) በቅርቡ በሶማሊ እና ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ በርካታ ቀበሌዎች የተከሰተው ውሃ ወለድ ተላላፊ ወረርሽን በሽታ በቁጥጥር ስር አለመዋሉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማስከኞ አስታወቀ። የድርቁን አደጋ ተከትሎ በተከሰተው በዚሁ ወረርሽን በኦሮሚያ ክልል ቦረና እና በሶማሌ ሊበን ዞን በሚገኙ ቀበሌዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች በወረርሽኙ ክፉኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል። የወረርሽኙ ስርጭት ወደሌሎች ወረዳዎችና ክልሎች እንዳይዛመት ለማድረግም ከእርዳታ ሰጪ ተቋማት የተውጣጡ ...

Read More »

የአዲስ አበባ መስተዳድር ማስተር ፕላኑን በግሉ ለመተግበር አቅም የለውም ተባለ

ጥር ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ150 ላላነሱ ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት የሆነው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በኦህአዴድ በኩል ተቀባይነት እንደሌለው መገለጡን ተከትሎ የአዲስ አበባ መስተዳድር በአስተዳደር ክልሉ ስር በሚገኙ ቦታዎች ላይ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ ቢጀመርም፣ እንቅስቃሴው ከእልህና ከግራ መጋባት የመጣ በመሆኑ ውጤታማ አይሆንም ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ወገኖች ይገልጻሉ። ከመጀመሪያው ጀምሮ በእቅዱ የተለያዩ ደረጃዎች የተሳተፉ ...

Read More »

ለኪሳራ የተዳረጉ መለስተኛ ፋብሪካዎች ሰራተኞችን መቀነስ ጀመሩ

ጥር ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ ችግር እጅግ ተባብሶ ከመቀጠሉ ጋር ተያይዞ በተለይ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ተቁዋማት ለከፍተኛ ኪሳራ እየተዳረጉ፣ ሰራተኞችም እየቀነሱ ነው። የሃይል እጥረቱ ተባብሶ በአሁኑ ወቅት በእየለቱ ቢያንስ ለግማሽ ቀን ወደመጥፋት ደረጃ ተሸጋግሯል። ት/ቤቶች፣ሆስፒታሎች ፣ዳቦ ቤቶችና የመሳሰሉ ስራቸው እየተስተጉዋጎለ ሲሆን አምራች ተቁዋማት ሰራተኞችን እየቀነሱ ነው። አንድ በዳቦ መጋገር ስራ የተሰማሩ ባለሀብት ሀይል ...

Read More »

እነ አቶ ሃብታሙ አያሌው ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው

ጥር ፲ (አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሰው ነጻ የተባሉትና እንደገና ይግባኝ የተጠየቀባቸው አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሽ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ እና አቶ አብርሃም ሰለሞን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም እንደገና ሌላ ተጨማሪ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ፍርድ ቤቱ ፣ አቃቤ ህግ በስር ፍርድ ቤት አልተመረመረልኝም ያለው ከብሄራዊ ደህንነትና መረጃ ማዕከል የተገኘው ማስረጃ፣ ማስረጃ ሳይሆን ...

Read More »