ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ተከትሎ አጠቃላይ በአሃጉሩ የሸቀጥ ዋጋ እየናረ ነው። የአፍሪካ ሕብረት የኤኮኖሚ ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር አንቶኒ ሞንታይ እንዳሉት የሸቀጦች ዋጋ መውረድ፣ የዶላር የወለድ መጠን በአሜሪካ መናር፣ አሳሳቢ ድርቅና የጎርፍ አደጋዎች በሃጉሪቱ ያለውን ምጣኔሃብታዊና ማኅበራዊ ችግሮች ይበልጥ አባብሰውታል ። ዶ/ር አንቶኒ “ችግሩ በመባባሱ ምክንያት የስራ አጡ ቁጥር እየጨመረ፣ የኑሮ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሰሜን ጎንደር በማንኛውም ጊዜ ግጭት ሊነሳ ይችላል ሲሉ ነዋሪዎች አስጠነቀቁ
ጥር ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ ፈጥሮታል በሚባለው በአማራና ቅማንት የሰሜን ጎንደር ተወላጆች መካከል ያለው ግጭት ለጊዜው ጋብ ያለ ቢመስልም፣ ድጋሜ ግጭት ለማስነሳት ውስጥ ለውስጥ የቅስቀሳ ስራ እየተሰራ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። አንዱ በሌላው ላይ የሚያካሂደው የማጥላላት ዘመቻ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በዚሁ የቅስቀሳ ስራ ላይ የኢህአዴግ ሹሞች ሙሉ በሙሉ እጃቸውን ማስገባታቸው ታውቋል። ...
Read More »በኮንሶ የሚታየው ውጥረት እንደቀጠለ ነው
ጥር ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮንሶ ህዝብ ራሱን ችሎ በዞን እንዲተዳደር ያቀረበው ጥያቄ ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ በርካታ ሰዎች ለእስር ከተዳረጉ በሁዋላ አሁንም አካባቢው በልዩ ሃይል ፖሊሶች እንደተከበበ መሆኑን ነዋሪዎች ከስፍራው ገልጸዋል። የልዩ ሃይል አባላት ከጥያቄው ጀርባ አርበኞች ግንቦት7ቶች አሉበት በማለት ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎች፣ አሁን ደግሞ ” ጥያቄው የእኛ አይደለም” ብላችሁ ፈርሙ በማለት በግድ ...
Read More »የውጭ ምንዛሬ እጥረት ማዳበሪያ በበቂ እንዳናስገባ አግዶናል ሲሉ ሚኒስትሩ ተናገሩ
ጥር ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የእር ሻና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው በውጪ ምንዛሪ ችግር ምክንያት ለእርሻ ግብአት የሚውል ማዳበሪያ በበቂ መጠን መግዛት እንዳልተቻለ ለፖርላማው ገልጸዋል፤፡ ለመስኖና እና ለበልግ እርሻ ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶአደሩ እንዲቀርብ ለማድረግ 832 ሺህ 400 ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ ለመግዛት ታቅዶ በውጭ ምንዛሪ አቅርቦት ችግር ጋር ተያይዞ በመተማመኛ ሰነድ (ሌተር ኦፍ ክሬዲት) ...
Read More »መንግስት በረሃቡ ላይ የያዘው አቋም የአለማቀፍ መንግስታት ተወካዮችን ግራ እያጋባ ነው
ጥር ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በያዝነው ፈረንጆች አመት ከ15 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ህዝብ ለርሃብ የተጋለጠ መሆኑ እየታወቀ በመንግስት በኩል ሁሉም ነገር በቁጥጥር ስር እንደዋለ ተደርጎ የሚሰጠው መግለጫ በለጋሽ አገራት ዘንድ ብዥታ መፍጠሩን የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ተናግረዋል። ስማቸው እንደይገለጽ የገለጹ የዲፕሎማቲክ ምንጮች እንዳሉት በኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ የሚሊዮኖችን ህይወት አደጋ ላይ መጣሉ በገሃድ እየታየ ቢሆንም፣ መንግስት ችግሩን ...
Read More »ባለፈው አመት በምስራቅ አፍሪካ ጭቆናው ተባብሶ መቀጠሉን ሂውማን ራይትስ ወች ገለጸ
ጥር ፲፰ (አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታዋቂው የሰአብዊ መብት ድርጅት ባወጣው ዘገባ የምስራቅ አፍሪካ መንግስታት የሰብአዊ መብት አያያዞችን ለማሻሻል ያደረጉት ጥረት አነስተኛ መሆኑንና በአንዳንድ አገሮች ተባብሶ የቀጠለበት ሁኔታ እንደነበር ገልጿል። ኢትዮጵያ እና ቡሩንዲ በተወሰነ መጠን ደግሞ ዩጋንዳ ሃሳብን በማፈን፣ የሰዎችን የመሰብሰብ ነጻነት በመንፈግ እንዲሁም ከምርጫ በፊትና በሁዋላ በሚፈጸሙ የመብት ጥሰቶች ቀዳሚዎች ሆነዋል። ሩዋንዳ የተቃውሞ ሃሳቦች እንዳይስተናገዱ ...
Read More »ኢንሳ የአየር ላይ ፎቶ በማንሳት ላይ የሚገኘው ለሱዳን ተሰጥቷል የሚባለውን አልፋሽጋ ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ መሆኑ ታወቀ
ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ጥር ወር መግቢያ ጀምሮ የአየር ላይ ፎቶ እየተነሳ ያለው አካባቢ የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ” ኢትዮጵያ መሬቱ የእኛ መሆኑን እውቅና ሰጥታለች” በማለት ለአልጀዚራ የተናገሩት አልፋሽጋ እየተባለ የሚጠራው ቦታ መሆኑ ታውቋል። ትናንት ኢሳት የመረጃና ደህንነት ኢንፎረሜሽን ባለሙያ በማናገር በሰራው ዘገባ ላይ በአሁኑ ሰአት የአየር ላይ ፎቶ ለማንሳት ምልክቶችን መሬት ላይ የማስቀመጡ ...
Read More »የቀድሞው የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት ዮናታን ተስፋዬ ላይ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ
ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባልፈፀመው ወንጀል በሽብር ክስ ተወንጅሎ በደኅንነት ኃይሎች ከመንገድ ታፍኖ ተወስዶ በእስር ላይ የሚገኘው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረው አቶ ዮናታን ተስፋዬ ላይ የአራዳ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለ2ኛ ጊዜ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቶበታል፡፡ በአራዳ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥር 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በዋለው ችሎት አቃቤ ሕግ ምርመራዬን አልጨረስኩም ተለዋጭ ...
Read More »በአንዳንድ አካባቢዎች ነዋሪዎች መብራትና ውሃ ከተቋረጠባቸው 5 አመታትን ማሳለፋቸውን ተናገሩ
ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በምእራብ ጎጃም ዞን የየስማላ ከተማ ነዋሪዎች መብራት ከተቋረጠባቸው 5 አመታትን ማሳለፋቸውን፣ በሰሜን ጎንደር ሃሙሲት ከተማ ደግሞ የከተማው ነዋሪዎች የቧንቧ ውሃ ከተቋረጠባቸው 5 አመታትን ማሳለፋቸውን ዘጋቢያችን ነዋሪዎችን አነጋግሮ የላከው ዘገባ ያሳያል። ነዋሪዎቹ ችግሮቻቸው እንዲፈቱላቸው በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም ሰሚ አካል አላገኙም። በሞጣ ከተማ ደግሞ መብራት ከተቋረጠ 2 ወር ያለፈው ሲሆን፣ በቁንዝላ ከተማ ውሃ ...
Read More »ታንዛኒያ ከመቶ በላይ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው ልትመልስ ነው
ጥር ፲፯ (አሥራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት ሲሞክሩ በድንበር ጠባቂዎች ባለፈው ወር በፖሊስ ተይዘው በእስር ሲንገላቱ የነበሩ 40 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ጨምሮ በዋና ከተማዋ ዳሬሰላም ካለ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ይኖሩና ይሰሩ ነበሩ ያላቸውን ኢትዮጵያዊያ ስደተኞችን ወደ ትውልድ አገራቸው ለመለስ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የታንዛኒያ የአገር ውስጥ ሚንስቴር አስታወቁ። የአገር ውስጥ ሚንስቴሩ ቻርለስ ኪታዋንጋ እንዳሉት ”ካለ ሕጋዊ የመኖሪያ ...
Read More »