.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኦሮሚያ በማስተር ፕላን አማካኝነት የተነሳው ተቃውሞ በድጋሚ ማገርሸቱ ታወቀ

ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) ከማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ከሳምንት በፊት በምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ የተቀሰቀሰው ዳግም ተቃውሞ መቀጠሉ ተገልጿል። በአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለውን ግድያና የጅምላ እስራት በማውገዝ ሃሙስ የተቃውሞ ሰልፍ ማካሄዳቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ተመሳሳይ ተቃውሞዎችም በሰሜን ሸዋ አካባቢ በሚገኙ ከተሞች በመካሄድ ላይ መሆናቸውን ለመረዳት ተችሏል። ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ፓርላማ በኦሮሚያ ክልል እየተፈጸመ ያለውን ግድያና ...

Read More »

የግብፁ ፕሬዚዳንት አል-ሲሲ በአባይ ጉዳይ ሊመክሩ አርብ አዲስ አበባ ኣንደሚገቡ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ

ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2018) የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ሃገራቸው በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን ጥቅም ለማስጠበቅ ይረዳት ባሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር በአዲስ አበባ እንደሚመክሩ የግብፅ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። በቅርቡ በካርቱም ስምምነት የተደረገባቸው አዳዲስ የመግባቢያ ሃሳቦችም በዚሁ ውይይት ላይ ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። አርብ እረፋድ ላይ አዲስ አበባ ይገነባሉ ተብለው የሚጠበቁት የግብፁ ፕሬዚዳንት በአፍሪካ ህብረት ልዩ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደው ልዩ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ተከትሎ ከፍተኛ የጸጥታ ሃይል ተሰማራ

ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) የፊታችን ቅዳሜ በአዲስ አበባ ከተማ የሚካሄደው ልዩ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ተከትሎ በመዲናው በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ሃይል መሰማራቱን ነዋሪዎች ገለጡ። በአዲስ አበባ እየተካሄደ ካለው የጸጥታ ቁጥጥር በተጨማሪ በሰበታ፣ ጫንጮና አካባቢዋ ባሉ የገጠር መንደሮች የጸጥታ ሃይሎች መሰማራታቸው ታውቋል። በእነዚህ አካባቢዎች ባለፈው ወር ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲካሄድባቸው የነበረ ...

Read More »

ኢትዮጵያ ሙስና በከፍተኛ ደረጃ ከሚፈጸምባቸው አገራት አንዷ መሆኗ ይፋ ሆነ

ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) ኢትዮፕያ በአለማችን ሙስና ይካሄድባቸዋል ተብለው ከተጠኑ 168 ሃገራት መካከል 103ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን በጉዳዩ ዙሪያ ጥናትን ያካሄደው ትራስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ሃሙስ ይፋ ባደረገው ሪፖርት አስታወቀ። ሃገሪቱም ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ይፈጸምባቸዋል ተብለው በቀይ ቀለም ከተቀመጡት ሃገራት መካከል አንዷ መሆኗንም ሪፖርቱ አመልክቷል። አውሮፓዊቷ ዴንማርክ በአለማችን ሙስና በጣም አነስተኛ ሁኔታ የሚፈፀምባት ሃገር ተብላ በአንደኛ ደረጃ የተቀመጠች ሲሆን ሶማሊያና ሰሜን ...

Read More »

የምግብ አቅርቦት እጥረት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ

ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ የተጋለጡ ከአስር ሚሊዮን በላይ ሰዎች አሳሳቢ የሆነ የምግብ አቅርቦት እጥረት አጋጥሟቸው እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃሙስ አስታወቀ። በቀጣዮቹ ሁለት ወራቶች ውስጥም ከአለም አቀፍ ማህበረሰብ አፋጣኝ የእርዳታ አቅርቦት የማይገኝ ከሆነ በርካታ ተረጂዎች ህይወታቸው አደጋ ላይ ሊወድቅ እንደሚችል ድርጅቱ መግለጹን ዴይሊ ሜይል ጋዜጣ ዘግቧል። የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ወቅታዊ ምላሽ ባለማድረጉ የተረጂዎች የእለት ከእለት ...

Read More »

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት አያያዝና በፖለቲካ ነጻነት ነጻ ካልሆኑ አገራት ተርታ ተመደበች

ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች በመገደብ ነጻ ካልሆኑ አገራት መመደቧን ፍሪደም ሃውስ የተሰኘ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋም ዛሬ ባወጣው አመታዊ ሪፖርት ገለጸ። ፖለቲካዊ መብቶችን እና የሲቪል ነጻነትን አስመልክቶ የተሰራው ይኸው የዘንድሮው 2016 የፍሪደም ሃውስ ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ የዜጎችን ፖለቲካዊ መብቶችን በመጨፍለቅ ቀዳሚ አገር እንደሆነች በሪፖርቱ ላይ ተጠቅሷል። በተመሳሳይ መልኩም የዜጎችን ነጻነት ካለፈ አመት በባሰ መልኩ እጅግ እንደተሸረሸረ ...

Read More »

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኦሮምያን ሙሉ በሙሉ አረጋግተናል ባለ ማግስት ተቃውሞ ተነሳ

ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ፣ በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን በመገናኛ ብዙሃን ባስታወቀ ማግስት በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞዎች ተነስተዋል። የተቃውሞዎች ዋነኛ አጀንዳ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስረዛ ወደ ሌሎች የመብት ጥያቄዎች ተሸጋግሯል። በጉጂ ፣ ሰሜን ሸዋና ምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ በተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች፣ ነዋሪዎች የታሰሩት እንዲፈቱ፣ ለወራት በዘለቀው ተቃውሞ ግድያ፣ ...

Read More »

በጋምቤላ በቀጠለው ግጭት ሰዎች ተጎዱ

ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት በሁለት የአኝዋክና ንዌር የመንግስት ባለስልጣናት መካከል የተነሳው ጸብ ወደ ብሄረሰብ ግጭት በማምራቱ የከተማዋና አካባቢው ነዋሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በከተማዋ ውስጥ እንደልብ መንቀሳቀስ አለመቻሉን የገለጹት ነዋሪዎች፣ እስካሁን ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ ለማወቅ አለመቻሉን ገልጸዋል። በከተማዋ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የመንግስት መስሪያቤቶች ተዘግተዋል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተማዋ ቢሰማሩም ግጭቱን ሊያስቆሙት አለመቻላቸውንም ነዋሪዎች ...

Read More »

በሃዋሳ ከተማ ያሉ የበረንዳ ዳስ ሱቆች ካለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ እንዲፈርሱ እየተደረገ ነው

ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል ዋና ከተማ ሃዋሳ በተለምዶ አረብ ሰፈር አሮጌ ገበያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የበረንዳ ዳሶችን ካንድ ቀን በፊት ብቻ ማሰጠንቀቂያ በመስጠት አፍራሽ ግብረ ኃይል በማሰማራት ሕገወጥ ግንባታ በሚል ሱቆቹን ማፍረሱ ቀጥሏል። ሕጋዊ የቫትና ቲኦቲ ግብር ከፋይ የሆኑት ነጋዴዎች ሁኔታውን በመቃወም ተቃውሟቸውን ቢገልፁም፣በአፀፋው የክልሉ ፖሊስ ሰላማዊ ሰልፈኞቹን በመደብደብ አካላዊ ጉዳት ...

Read More »

በኢትዮጵያ አንድ አምስተኛ የሚሆነው ሕዝብ ለረሃብ ሊጋለጥ ይችላል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ

ጥር ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን በአሳሳቢ የርሃብ አደጋ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በሚቀጥሉት ወራት አደጋው በእጥፍ እንደሚጨምር ቅድመ ጥናቶች አረጋግጠዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ግብረሰናይ የረድኤት ተቋማት በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ከተከሰተው የርሃብ አደጋዎች በኢትዮጵያ ያለው ርሃብ አድማሱን በማስፋቱ ከአጠቃላይ የአገሪቱ ሕዝብ ውስጥ አንድ አምስተኛ የሚሆነው ወይም ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝብ በርሃብ አደጋ ውስጥ ...

Read More »