የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአምቦ እና አካባቢዋ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የሚታሰሩ ወጣቶች ቁጥር በመጨመሩ፣ ከአምቦ ወጣ ብሎ የሚገኘው የጥይት ፋብሪካ ወደ እስር ቤት መለወጡን ምንጮች ገልጸዋል። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በጥይት ፋብሪካው ግቢ ታስረው የሚገኙ ሲሆን፣ ብዙዎቹ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል። በሌላ በኩል መንግስት የኦሮሞ የአገር ሽማግሌዎችን “በመሰብሰብ ህዝባዊ ተቃውሞው እንዲበርድ አስተዋጽኦ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢህአዴግ መንግስት በኤርትራ ላይ ጥቃት ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው ተባለ
የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንዳሉት በተለያዩ የውስጥ ችግሮች ተወጥሮ የሚገኘው ኢህአዴግ በኤርትራ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው። በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በአካባቢው በሚገኙ የመንግስት ወታደሮች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ቆይተዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶችም እነዚህን ነጻ አውጭዎች ለመቀላቀል ድንበር አቋርጠው እየተጓዙ ነው። ይህ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ስጋት ላይ የጣለው የኢህአዴግ መንግስት፣ በኤርትራ ...
Read More »ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በመንግስት ድጋፍና ቅስቀሳ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ብዙዎችን እያስቆጣ ነው።
የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከሰልፉ ጋር በተያያዘ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጣቸውን እየገለጹባቸው ካሉት ምክንያቶች መካከል አንደኛው በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በኦሮሚያ ክልል እየተፈጸመ ያለውን ግድያ ለመቃወም ባዲስ አበባና በአንዳንድ ከተሞች ለማድረግ ያቀረቡት የሰልፍ ፈቃድ ጥያቄ በተከለከለበት ሁኔታ፤ መንግስት “ወልቃይት -ትግራይ ናት” የሚል ሰልፍ በማስደረጉ ነው። ይህም በአንድ ሀገር ውስጥ ያሉ ህዝቦች በሁለት ...
Read More »የአቶ ሃይለማርያም ዛቻም ሆነ የሃይማኖት አባቶች ተማጽኖ በኦሮምያ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ አላስቆመውም
የካቲት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአጋዚ ወታደሮች ለተቃውሞ በሚወጡት ወጣቶች ላይ በቀጥታ እንዲተኩሱ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል፣አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም መንግስታቸው የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ በአደባባይ ዝተዋል። የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚወክሉ የሃይማኖት አባቶች፣ በመንግስትና በህዝቡ መካከል መነጋጋር እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል። ይህ ሁሉ ዛቻና ምክር እየተሰጠ ቢሆንም፣ የክልሉ ወጣቶች የሚያቆመን የለም በማለት ዛሬም ትግላቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። የቦረና እና የጉጂ ዞኖች የዛሬው ...
Read More »የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት/ኦህዲኅ/ ም/ሊቀመንበር ተፈቱ
የካቲት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ም/ል ሊቀመንበሩ አቶ ዓለማየሁ መኮንን በትናንትናው ዕለት ‹‹የፍትህ ጥያቄ የነጻነት ጥያቄ ነው›› በማለት ስለዞኑ ፍትህ መናገራቸውን ተከትሎ ታስረው ነበር፡፡ ‹‹ፍትህ በሌለበት፣ነጻነት አይኖርም ፣ነጻነት በሌለበትም ፍትህ አይኖርም ›› ብለው ተናግረዋል በሚል በዳኛ ዳዊት አድማሱ ጥሩነህ በቀረበባቸው አቤቱታ መታሰራቸው በፖሊስ የእለት መዝገብ ላይ ሰፍሮ ቢገኝም፣ ማንም ቀርቦ ስለሁኔታው ሊያስረዳ ባለመቻሉ ዛሬ ከሰዓት ...
Read More »የእንግሊዙ ጠ/ሚኒስትር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው
የካቲት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን ጉብኝቱን መቼ እንደሚያካሂዱ ባይገለጽም፣ኢትዮጵያን በሚጎበኙበት ወቅት የስደተኞች ጉዳይ ዋና አጀንዳ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በጉብኝታቸው በእስር ላይ የሚገኙትን የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ አንስተው ከኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ይነጋገሩ አይነጋገሩ የታወቀ ነገር የለም። ይሁን እንጅ በእንግሊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተከታታይ የተቃውሞ ሰልፎችን በማካሄድ ጫና መፍጠር ከቻሉ፣ ጠ/ሚኒስትሩ ...
Read More »በኦሮምያ የሚካሄደው ተቃውሞ ግለቱን ጨምሮ ቀጥሎአል
የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እጅግ ደም አፋሳሽ እየሆነ በመጣው የኦሮምያ ተቃውሞ፣ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶች በአጋዚ ጥይት እየተረፈረፉ ነው። በምእራብ አርሲዋ ኮፈሌ ከተማ ወደ 20 የሚጠጉ ሰዎች ሲያልቁ፣ በርካቶችም ሆስፒታል ገብተዋል። በአሳሳ ትናንት የተገደለችው የ8 አመት ህጻን የቀብር ስነስርዓት ዛሬ የተፈጸመ ሲሆን፣ የከተማው ነዋሪ መንገድ በመዝጋት ተቃውሞን ገልጿል። በምእራብ አርሲ ወደ ባሌ አቅጣጫ በሚወስደው መንገድ ላይ ...
Read More »በዛሬው የአንዋር መስጊድ የጁማዓ ጸሎት ላይ የተቃውሞ ድምጾች ተሰሙ
የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ሳምንት በአንዋር መስጊድ ድንገተኛ ተቃውሞ መደረጉን ተከትሎ ፖሊስ የጸጥታ ቁጥጥሩን በማጠናከር ፍተሻዎችን ሲያካሂድ ቢያረፍድም፣ ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ ግን ተቃውሞአቸውን በድምጽ ከማሰማት ያቆማቸው አልነበረም። “ኮሚቴው ይፈታ፣ መንግስት የለም ወይ” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል። መንግስት የኮሚቴው አባላትን ሞራል ለመስበር የተለያዩ የፈጠራ ዜናዎችን እያሰራጨ መሆኑን ድምጻችን ይሰማ ማስታወቁ ይታወቃል።55
Read More »በአማራ ክልል በረሃብ የተጎዱ ቤተሰቦች ቀያቸውን ለቀው እየሄዱ ነው
የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መንግስት አመራር እስካለ ድረስ ለችግራቸው መፍትሄ እንደማያገኙም ተናግረዋል። የገዢው መንግስት ‹‹… ድርቁ ሊያስከትል የነበረውን አደጋ ተቆጣጥረናል፤ በየአከባቢው ተገቢውን እርዳታ ለተጎጂዎች እያደረስን ነው….››ቢልም ፤ በምስራቅ አማራ የትግራይ ድንበር አካበቢ የሚገኙ ተጎጅዎች ሰሞኑን እንደተናገሩት ፡- በአንድ ቀበሌ ብቻ በደረሰው ድርቅ በከፍተኛ ደረጃ የተጎዱ አምስት ሽህ ያህል ሰዎች እርዳታ ሳይደርሳቸው በችግር ላይ ይገኛሉ፡፡ ...
Read More »በደቡብ ጎንደር የተነሳው ከባድ ጉንፋን የብዙ ሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው
የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በደቡብ ጎንደር ደብረታቦር አካባቢ የተነሳው ከባድ ጉንፋን ሰዎችን ለህልፈት እየዳረገ ቢሆንም የአካባቢው ባለስልጣናትም ሆኑ የክልሉ አመራሮች የወሰዱት ጠንከር ያለ እርምጃ ባለመኖሩ የአካበቢው ህብረተሰብ በጭንቀት ላይ መሆኑን ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ለየት ብሎ በተከሰተው ጉንፋን እስካሁን ስድስት ሰዎች መሞታቸው የታወቀ ሲሆን በተለይ በደብረታቦር ማረሚያ ቤት በሽታው እየተስፋፋ በመሆኑ በበሽታው የተለከፉ ሰዎችን ...
Read More »