የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት የሚመራው የትግራይ ክልል፣ የወልቃይት የማንነት ጥያቄ የሚያቀርቡ ግልሰቦችን የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎችን ዛሬም በሁመራ ከተማ አዘጋጅቷል። ይኸው በክልሉ መንግስት የሚቀነባበረው የተቃውሞ ሰልፍ፣ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የአማራ ማንነቱ ይከበርለት በማለት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥያቄውን እንደገና ባነሱት የወልቃይት ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ነው። የወልቃይትን ህዝብ ተወካዮች ” ማንነታቸው ከአማራ ህዝብ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ፣ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አካሄዱ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መብታቸው እንዲከበርላቸው ለአመታት ሲጠይቁ የቆዩት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከአርብ ቀን ጸሎት በሁዋላ የተለያዩ መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎችን በመልቀቅ ተቃውሞአቸውን ገልጸዋል።ፍልውሃ በሚገኘው ተውፊቅ መስጊድ በተካሄደው ተቃውሞ “ጭቆናን እንታገላለን፣ ኮሚቴው ይፈታ ፣ ድራማው ይብቃ” የሚሉና ሌሎችም መፈክሮችን የያዙ ፊኛዎች ተለቀዋል።
Read More »የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የእሰረኞች ሰንድ እንዳይወጣ አገደ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፌደራል አቃቤ ህግ ይግባኝ ተጠይቆባቸው ጉዳያቸውን ከከቃሊቲ እስር ቤት በመመላለስ በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየተከታተሉ የሚገኙት የቀድሞው አንድነት፣ የሰማያዊ እና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች ከብሄራዊ የመረጃና ደህንነት ማዕከል፣ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ማስረጃ ላይ የሰነድ አስተያየታቸውን ለማቅረብ ያዘጋጁትን ጽሁፍ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዳይወጣ እንደከለከላቸው ገለጹ፡፡ ከእስር ተፈቶ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እየተከታተለ የሚገኘው የቀድሞው ...
Read More »ቻይናዊያን በሕገወጥ የችርቻሮ ንግድ ላይ በመሰማራታቸው ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች መስራት አልቻልንም አሉ
የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመዲናችን አዲስ አበባ በቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ የሚገኙ ነጋዴዎች በቻይናዊያን የሕገወጥ ንግድ ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን እንዳልቻሉ ተናገሩ። ባለፉት ሶስት ዓመታት የውጭ ዜጎች በሚበዙበት በቦሌ ሩዋንዳ ለምግብ ፍጆታዎች የሚውሉ ምርቶች በማቅረብ ስራ ላይ ተሰማርተው ይሰሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች በሕገወጥ የቻይኖች ዜጎች አካባቢያችን ተወሮ ሱቃቸውን ለመዝጋት እየተገደዱ መሆናቸውን ገልጸዋል። በቦሌ ሩዋንዳ በሚኒ ...
Read More »በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ተታውሞ አድማሱን አስፍቶ ቀጥሏል
ኢሳት (የካቲት 17, 2008) ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ዳግም የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ሃሙስ በበርካታ አካባቢዎች መዛመቱን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የመንግስት ባለስልጣናት ተቃውሞን ለመቆጣጠር የሃይል እርምጃን እንደሚወስዱ ቢያሳስቡም ህዝባዊ ተቃውሞው በምዕራብ ወለጋ እንዲሁም በምዕራብና ምስራቅ ሃረርጌ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ መሆኑ ታውቋል። በየአካባቢው የሚኖሩ ነዋሪዎች የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለውን ግድያና የጅምላ እስራት በመቃወም ድርጊቱን ሲያወግዙ መዋላቸው ተገልጿል። ይሁንና፣ የጸጥታ ...
Read More »አስቸኳይ የምግብ እንክብካቤን የሚፈልጉ ህጻናት ቁጥር 6 ሚሊዮን መድረሱን ተመድ አስታወቀ
ኢሳት (የካቲት 17, 2008) በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ አስቸኳይ የምግብ እንክብካቤን የሚፈልጉ ህጻናት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት አስታወቀ። በድርቁ ሳቢያ እርዳታን ይፈልጉ የነበሩ የአምስት ሚሊዮን ህጻናት ቁጥርም ወደስድስት ሚሊዮን ያደገ ሲሆን ድርቁ በመባባስ ላይ መሆኑንም ድርጅቱ ገልጿል። አስቸኳይ የምግብ ድጋፍን ከሚፈልጉት ስድስት ሚሊዮን ህጻናት መካከልም ከ430ሺ በላይ የሚሆኑት ልዩ የነብስ-አድን የምግብ እንክብካቤን ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ለመጨፍለቅ መንግስት አስፈላጊውን የሃይል እርምጃ እንደሚወስድ ገለጸ
ኢሳት (የካቲት 17, 2008) ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኖ ያለውን የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ለማስቆም መንግስት አስፈላጊውን እርምጃ እወስዳለሁ ሲል ሃሙስ በድጋሚ ገለጠ። የመንግስት ባለስልጣናት የተጀመረውን የሃይል እርምጃ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቢልጹም፣ በክልሉ ተቃውሞው ዳግም በመዛመት ላይ መሆኑን የተለያዩ አካላት አስታውቀዋል። ተቃውሞው ዳግም ማገርሸቱን ተከትሎም የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑንት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከተቃውሞው ጀርባ የውጭና የውስጥ አካላት አሉ ሲሉ የገለጻቸውን አካላት በስም ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል መንግስት በሚወስደው እርምጃ ህዝቡ በፍርሃትና በጭንቀት ውስጥ መሆኑን ኤኤፍፒ ዘገበ
ኢሳት (የካቲት 17, 2008) በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ዳግም ባገረሸባቸው አካባቢዎች ነዋሪዎች የፀጥታ ሃይሎች በሚወስዱት እርምጃ በፍርሃትና በጭንቀት ውስጥ መሆናቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ የአይን እማኞችን ዋቢ በማድረግ ሃሙስ ዘገበ። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት የጊንጪ ከተማ ነዋሪዎች፣ የጸጥታ ሃይሎች በቀንና በምሽት ፍተሻን በማካሄድ ነዋሪዎች ላይ ስጋትን ፈጥረው እንደሚገኙ አስረድተዋል። ህይወታችን ትርጉም አልባ ሆኖብናል ሲሉ የገለጹት አንዲት በ40ዎቹ እድሜ ውስጥ የሚገኙ የሁለት ...
Read More »እስራዔል በአባይ ግድብ ዙሪያ አለመግባባት ላይ በአደራዳሪነት እንድትሳተፍ መጠየቋን አንድ ጋዜጣ ዘገበ
ኢሳት (የካቲት 17, 2008) ኢትዮጵያና ግብፅ በአባይ ግድብ ግንባታ ዙሪያ ያላቸውን አለመግባባት እልባት ለመስጠት እስራዔል በአደራዳሪነት እንድትሳተፍ የሃገሪቱ የፓርላማ አባላት በማግባባት ላይ መሆናቸውን የሩሳሌም ፖስት ጋዜጣ ሃሙስ ዘገበ። የሃገሪቱ የፓርላማ አባል የሆኑትና የግብፅ አል-ፋርን የቴለቪዥን ጣቢያ ባለቤት የሆኑት ቶውፊክ አካሻ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ ለመምከር ካይሮ ከሚገኙት የእስራዔል አምባሳደር ቼም ኮረን ጋር ቀጠሮ መያዛቸው ተገልጿል። እስራኤል በአደራዳሪነት መሳተፏ ከፍተኛ ጠቅሜታ ያለው ...
Read More »በኦሮምያ ተከታታይ ተቃውሞዎች እንደሚቀጥሉ ከያካባቢው የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል
የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ የአጋዚ ወታደሮችን በየቦታው አሰማርቶ ግድያና እስሩን አጠንክሮ ቢቀጥልም፣ በሚቀጥሉት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎችን ለማድረግ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው። በተለይ የሻኪሶ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የጉጂ ዞን አካባቢዎች ጠንካራ ተቃውሞች እንደሚካሄዱ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በቦረና ዞንም እንዲሁ ተቃውሞዎች እንደሚቀጥሉ የአካባቢዎች ነዋሪዎች ተናግረዋል። በምእራብ ሃረርጌ ዛሬም የተቃውሞ ሰልፍ ሲካሄድ ውሎአል። ...
Read More »