.የኢሳት አማርኛ ዜና

የጋይንት ህዝብ ስለወልቃይት ጉዳይ አትጠይቅም በመባሉ ስብሰባ ረግጦ ወጣ

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር ዞን በጋይንት ከተማ የክልሉ ባለስልጣናት ህዝቡን ለማወያየት ትናንት እሁድ የጠሩት ስብሰባ፣ በተቃውሞ ተበትኗል። የተቃውሞው መነሻ ደግሞ ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ፣ ህዝቡ ጥያቄ ማቅረብ በመጀመሩና ስብሰባውን የሚመራው ጋዜጠኛ ” ስለወረዳችሁ እንጅ ስለሌሎች አካባቢዎች ጥያቄ መጠየቅ አትችሉም” ማለቱን ተከትሎ ነው። ስብሰባው የተጠራው ከዚህ ቀደም የከተማዋ ነዋሪዎች የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ...

Read More »

ኤርትራ – ከኢትዮጵያ መንግስት የተሰነዘረባት ክስ ፈጽሞ ውሸት እንደሆነና የኢትዮጵያ መንግስት ከውስጥ የተነሳበትን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማድበስበስ የፈበረከው መሆኑን አስታወቀች።

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ፦” ውሸት ቢደጋገምም፤ እውነትን ሊቀብር አይችልም” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ የህወሀት አገዛዝ እንደተለመደው ኤርትራን ለማጠልሸት ኋላ ቀርና ርካሽ ፕሮፓጋንዳ መንዛቱን በመጥቀስ፤ የዚህ ፕሮፓጋንዳ ዓላማውም እውነታውን ለመደበቅና ከውስጥ እያየለ የመጣበትን ህዝባዊ ተቃውሞ ውጫዊ ለማስመሰል እንደሆነ ገልጿል። የኤርትራ ህዝብና መንግስት የዚህ ዓይነት ተደጋጋሚ የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየተነዛባቸው ባለበትና መሬታቸው በኃይል በተያዘበት ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት በበርን ስዊዘርላንድ የተሳካ ህዝባዊ ውይይት አደረገ

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንቅናቄው አመራር የሆኑት አርበኛ ኤፍሬም ማዴቦ፣ ጋዜጠኛ አፈወርቅ አግደው ፣ የኢሳት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ የጀርመን ሃገር ቃል አቀባይ ሃይሉ ማሞ፥ ተቀማጭነታቸው በስዊዘርላንድ የሆኑ የሃይማኖት አባቶችና ከተለያዩ የስዊዘርላንድ ከተሞችና ከሙኒክ ጀርመን ከተማ በመጡ ሃገርወዳድ ኢትዮጵያውያን በታደሙበት በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ውይይት ላይ የወቅቱ የሃገራችን ፖለቲካዊና ማህበራዊ ሁኔታ፣ የአርበኞች ግንቦት 7 የትግል እንቅስቃሴ ፣ ላለፉት ...

Read More »

ቤተ-እስራዔላውያንን ለማጓጓዝ የወጣው እቅድ እንዲዘገይ ተደረገ

ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008) በቅርቡ የመጨረሻዎቹ ዘጠኝ ሺህ ቤተ-እስራዔላውያን ከኢትዮጵያ ወደእስራዔል ለማጓጓዝ ቃል ገብታ የነበረችው እስራዔል እቅዱ እንዲዘገይ ማድረጓን አርብ ይፋ አደረገች። የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ እቅዱ ከበጀት ጋር በተያያዘ እንደዘገይ መደረጉን ቢገልፅም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አካላት ድርጊቱ በእስራዔል ጥያቄን አስነስቶ ካለው ከዘረኝነት ጉዳይ ጋር የተያያዘ እንደሆነ ገልጸዋል። የእስራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ጄኔራል ዳይሬክተር የሆኑት ኤሊ-ግሮነር እቅዱ ከመነሻውም በጀት ሳይያዝለት ...

Read More »

ፍል ውሃ አካባቢ በሚገኘው ተውፊቅ መስጊድ ተቃውሞ ተካሄደ

ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008) በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱና በሃገሪቱ ያለን ጭቆና እንዲቆም የሚጠይቅ ተቃውሞ አርብ ፍል ውሃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኘው ተውፊቅ መስጊድ ተካሄደ። የአርብ ልዩ የጾም (ጁምዓ) ስነ-ስርዓት ተከትሎ በተካሄደው በዚሁ ተቃውሞ የሙስሊም ማህበረሰብ መፈክሮች የተጻፉባቸው ፊኛዎችን ወደሰማይ መልቀቃቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት በድምፅና ድምፅ አልባ የሆኑ ተቃውሞዎች በአንዋር መስጊድ ...

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኖርዌይ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ተገዢ እንድትሆን ጠየቀ

ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008) የኖርዌይ መንግስት በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ያለፍላጎታቸው ወደሃገራቸው ለመመለስ የያዘውን እቅድ ተከትሎ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሃገሪቱ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ተገዢ እንድትሆን አሳሰበ። ሃገሪቱ በስደተኞች ላይ እየያዘች የመጣችውን አዳዲስ አቋሞች የተቸው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ኖርዌይ ለአለም አቀፍ ህግጋት ተገዢ ያለመሆን አቅጣጫ እየተከተለች እንደሆነም አስታውቋል። ኖርዌይ ተግባራዊ ለማድረግ ያሰበችውን የስደተኞች አዲስ እቅድ ምክንያት በማድረግ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ከ500 የሚበልጡ ...

Read More »

ህወሃት/ኢህአዴግ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ካለው ተቃውሞ ጀርባ የኤርትራ እጅ አለበት ሲል ከሰሰ

ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008) የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ካለው ተቃውሞ ጀርባ የኤርትራ እጅ አለበት ሲሉ አዲስ ተቃውሞ ማቅረባቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ አርብ ዘገበ። መነሻውን ከጎረቤት ኤርትራ ያደረጉ አካላት በተቃውሞ ስለመሳተፋቸውንና ችግሩን በማባባስ ላይ ስለመሆናቸው በቂ ማስረጃ አለን ሲሉ የመንግስት ቃል አቀባዩ አቶ ጌታቸው ረዳ ለዜና አውታሩ ገልጸዋል። የመንግስት ባለስልጣናት በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ላለው ተቃውሞ በክልሉ የመልካም አስተዳደር ተግባራዊ አለመደረጉ ...

Read More »

በወሊሶ ከተማ ተቃውሞ ተካሄደ

ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008) በተለያዩ የኦሮሚያ የክልል ከተሞች ዳግም ያገረሸው ህዝባዊ ተቃውሞ አርብ ከአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ወሊሶ መዛመቱን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች በከተማዋ የተዘረጋን ዋና መንገድ በመዝጋት ተቃውሞ ሲያቀርቡ መዋላቸው ታውቋል። በምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ አካባቢዎች በሚገኙ የገጠር ከተሞች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አርብ የቀጠለ ሲሆን ተመሳሳይ ተቃውሞዎች በምዕራብ ሸዋ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች እንዲሁም ...

Read More »

በደብረብርሃን ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 14 ሰዎች ሞቱ

ኢሳት (የካቲት 18 ፥2008) በአዲስ አበባ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ደብረ-ብርሃን ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በትንሹ 14 ሰዎች መገዳላቸውን ፖሊስ አርብ አስታወቀ። አንድ መለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከሌላ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨታቸው አደጋው ሊደርስ መቻሉንና፣ ሌሎች ሶስት ሰዎችም ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል። በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በፅኑ በመጎዳታቸው የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ተብሎ የተሰጋ ሲሆን ፖሊስ የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ...

Read More »

በኦሮምያ ተቃውሞው ዛሬም ቀጥሎ ዋለ

የካቲት ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ላለፉት 4 ወራት በተከታታይ ሲደረግ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል።ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአጋዚ ሰራዊት በሰፈነበት ምእራብ ሃረርጌ፣ሀብሩ ወረዳ ዴፎ ከተማ ህዝቡ ለተቃውሞ በመውጣት፣ መሰረታዊ የሚባሉ የመብት ጥያቄዎችን ሲጠይቅ አርፍዷል።በወለጋ ሆድሮጉድሩ የሻምቡ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችም እንዲሁ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በክልሉ የሚገኙ በርካታ ትምህርትቤቶች የተዘጉ ሲሆን፣መንግስት ትምህርት ቤቶችን መክፈት ለተጨማሪ ...

Read More »