የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእስር ላይ የሚገኙትን አቶ መላኩ ፋንታን በመተካት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ከሶስት አመታት በፊት የተሾሙት አቶ በከር ሻሌ ፣ ከዛሬ ጀምሬ የኦህዴድ ድርጅት ጽ/ቤት ሃላፊ ሆነው መሾማቸውን ፎርቹን ዘግቧል።በኦሮምያ በመካሄድ ላይ ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ ፣ አቶ በከር የክልሉን ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድርን ይተካሉ ተብሎ በስፋት ሲወራ ቆይቷል። ይሁን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በዲላ፣ ሱሉሉታና አዳማ ከተሞች ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር ተከሰተ
የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዲላ ከተማ በተፈጠረው ከፍተኛ የሆነ የውሃ ችግር ነዋሪዎች ፣ቢጫ ጀሪካኖቻቸውን አሰልፈው ወንዝ እየወረዱ ለመቅዳት ተገደዋል። ከዚህ ቀደም በ15 ቀን አንድ ቀን ይገኝ የነበረው የቧንቧ ውሃ አሁን በወር አንድ ቀን ለማግኘት እየቸገረ መሆኑን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። በሱሉልታም እንዲሁ ውሃ ከጠፋ ወራት በመቆጠራቸው ህዝቡ የቆሸሸና የተበከለ ውሃ ለመጠቀም መገደዱን የአካባቢው ምንጮች በቪዲዮ አስደግፈው ...
Read More »ዘጠኝ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የድራግ ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ተገለጸ።
የካቲት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ጸረ- ድራግ ኤጀንሲ ጀነራል ሴክሬታሪን ጠቅሶ ዘጋርዲያን እንደዘገበው ምርመራ እየተደረገባቸው ካሉት ዘጠኝ አትሌቶች መካከል አምስቱ ታዋቂና ስመ-ጥር አትሌቶች ናቸው። ሴክሬታሪው አቶ ሰሎሞን መአዛ ለአሶሲየትድ ፕሬስ እንደተናገሩት ታዋቂዎቹ አምስት አትሌቶች አስደናቂ ድል አስመዝግበው መመለቸውን ተከትሎ አበረታች መድሀኒት ወስደዋል የሚል ቅድመ-ምርመራ ውጤት በመደረጉ ነው በኤጄንሲው ምርመራ እየተደረገባቸው ያለው። ይሁንና ጀነራል ሴክሬታሪው ...
Read More »በክልሎች ህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ሰጪዎች በአዲስ አበባ የተቀሰቀሰውን የስራ ማቆም አድማ ተቀላቀሉ
ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2008) የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎቶችን በክልል የሚሰጡ አውቶቡሶች በአዲስ አበባ የተቀሰቀሰውን የስራ ማቆም ተቃውሞውን ሰኞ እንደተቀላቀሉት ታውቋል። በአሰላ፣ ባሌ፣ እና ሮቤ ከተሞች የተጀመረው የትራስፖርት ማቆም አድማ ተከትሎም በየከተሞቹ የትራንስፖርት እጥረት መከሰቱን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በስራ ማቆም አድማ ላይ ያሉ ታክሲዎች አገልግሎታቸውን እንዲጀምሩ ጥሪን ቢያቀርቡም የታክሲ ማቆም አድማው ሰኞ ምሽትም መስተዋሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
Read More »በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ህዝባዊ እምቢንተኝነቱ ቀጥሏል
ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2008) በሰሜን ጎንደር ዳባት ወረዳ ለሁለተኛ ቀን ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ቀጥሎ መዋሉን እሳት ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጹ። ተቃውሞው ከተቀሰቀሰ በኋላ በወረዳዋ ባለስጣናት መካከል ውዝግብ መፈጠሩም ከውስጥ ምንጮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ህዝባዊ እምቢተኝነቱን ተከትሎ የዳባት ወረዳ የደህንነት ሃላፊ፣ የሚሊሺያ ዘርፍ ሃላፊና፣ የሲቪል ሰርቪስ መስሪያ ቤት ሃላፊ መታሰራቸውን ከስፍራው የተገኘው መረጃ አመልክቷል። በዛሬው ምሽት ከሌሎች ከተሞች ጋር የሚያገናኙ መንገደችም ...
Read More »የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ዋጋ የቀነሰ ቢሆንም መንግስት ተገቢውን ቅናሽ አለማድረጉ ቅሬታን ቀሰቀሰ
ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2008) በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ዋጋ የቀነሰ ቢሆንም መንግስት ተገቢውን ቅናሽ አላደረገም በሚል የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ቅሬታን አቀረቡ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አካላት በበኩላቸው በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ካልፈው አመት ጀምሮ የ40 በመቶ ቅናሽን ቢያሳይም መንግስት ተግባራዊ ያደረገው ቅናሽ ከ12 በመቶ እንደማይበልጥ መግለጻቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ስራ ...
Read More »ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለመታደግ የሚደረገው ጥረት አነስተኛ ነው ተባለ
ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ የተጋለጡ ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለመታደግ የሚደረገው ጥረት አነስተኛ መሆኑን እንዳሳሰበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰኞ ገለጠ። ለተረጂዎች እየቀረበ ያለው እርዳታ በማለቅ ላይ ቢሆንም ተተኪ የእርዳታ አቅርቦትን ለማድረስ እየተደረገ ያለው ጥረት ግን እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ድርጅቱ በአፅንዖት አስታውቋል። አለም አቀፍ የምግብ እርዳታን ወደሃገር ውስጥ ለማስገባት በትንሹ የሶስት ወር ጊዜን የሚወስድ ሲሆን እርዳታው ...
Read More »በአዲስ አበባ የታክሲ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ ጀመሩ
ኢሳት (የካቲት 21 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎትን በመስጠት ላይ ይሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የታክሲ አሽከርካሪዎች ተግባራዊ የተደረገን አዲስ የትራፊክ ቁጥጥር ደንብ በመቃወም ሰኞ የስራ ማቆም አድማ ጀመሩ። የታክሲ አሽከርካሪዎች የወሰዱትን እርምጃ ተከትሎም የከተማዋ ነዋሪዎች የዕለት ከእለት የኑሮ እንቅስቃሴያቸው መስተጓጎሉን እማኞች ገልጸዋል። ከአራት አመት በፊት የወጣውና ከቀናት በፊት ተግባራዊ መደረግ የጀመረው የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ ለስራ አስቸጋሪ በመሆኑ ደንቡ መሻሻል እንዳለበት ...
Read More »በአዲስ አበባ የሚካሄደው የታክሲ አሽከርካሪዎች አድማ እንደቀጠለ ነው
የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አሽከርካሪዎች ጥፋት ሲያጠፉ ፈቃዳቸውን እስከመሰረዝ የሚያደርሰውን ከበድ ያለ ቅጣት የያዘውን ህገደንብ በመቃወም በአ/አ ከተማ የተጀመረው የታክሲ ማቆም አድማ የቀጠለ ሲሆን ፣ በተለያዩ አካባቢዎች ታክሲ በመጠበቅ ላይ የነበረው ህዝብ ሆን ብሎ መንገዶችን በመዝጋት፣ ሌሎች የግል፣የንግድና የመንግስት ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ እንዲታወክ በማድረግ ተቃውሞውን ተቀላቅሏል። ተቃውሞውን ተከትሎ የመንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ደንቡ ...
Read More »የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በታክሲዎች አድማ ምክንያት ተሰረዘ
የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራው የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት 120ኛውን የአድዋ ድል በዓል በነገው እለት ለማካሄድ የያዘውን የፖናል ውይይት ከአ/አ ታክሲዎች አመጽ ጋር በተያያዘ ለመሰረዝ ተገዷል። ጽ/ቤቱ የካቲት 22 ቀን 2008 ዓ.ም በኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል የፖናል ውይይቱን ለማካሄድ አቅዶ ለሆቴሉ ክፍያ የፈጸመውና ለተሳታፊዎች ጥሪ ያስተላለፈው ከሳምንት በፊት ነበር። ሆኖም በአ/አ ከተማ በመካሄድ ...
Read More »