ኢሳት (የካቲት 28 ፥ 2008) መቀመጫቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ተወካዮች የጋዜጠኝነት ስራቸውን በነጻነት እንዳያከናውኑ በመንግስት ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የውጭ ጋዜጠኞች ማህበር ሰኞ ገለጠ። ከቀናት በፊት ሁለት የማህበሩ ጋዜጠኞች ለ24 ሰዓት በጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያስታወቀው ማህበሩ በመገናኛ ብዙሃን ላይ እይደረሰ ያለው ወከባ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱንም አስታውቋል። ከአስተርጓሚያቸውንጋር በአፋር ክልል አዋሽ ከተማ በቁጥጥር ስር ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በደቡብ ክልል በሱርማ ማህበረሰብ አባላት ላይ የተፈጸመው ዘግናኝ ግፍ በማህበራዊ ሚዲያው ቁጣን ፈጥረ
የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች የሱርማ ብሄረሰብ አባላትን አንገታቸውንና እግራቸውን በማሰር በፖሊስ መኪና ጭነው ሲወስዱዋቸው የሚያሳየው ፎቶግራፍ በማህበራዊ ሚዲያው ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። ድርጊቱን የፈጸሙት የደቡብ ክልል ልዩ ሃይል ፖሊሶች ይሁኑ ወይም የክልሉን የፖሊስ መኪና የተጠቀሙ የመከላከያ ሰዎች ይሁኑ ባይታወቅም፣ ይህ በዚህ ዘመን ይፈጸማል ተብሎ የማይታሰብ ዘግናኝ ድርጊት፣ በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች ለመፈጸሙ ከተሽከርካሪው፣ ...
Read More »አህዴድ አቶ ዘላለም ጀማነህን አባረረ
የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል የተነሳው ተቃውሞ በተለያዩ አካባቢዎች በመካሄድ ላይ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ኦህዴድ ነባር አመራሮቹን ከሃላፊነት ማንሳቱን ቀጥሎአል። ቀድም ብለው ያለማእከላዊ ኮሚቴው እውቅና በስራ አስፈጻሚው ትእዛዝ ብቻ ተባረው ከነበሩት መካከል የአቶ ዳባ ደበሌ መባረር በማእከላዊ ኮሚቴው ሲጸድቅ፣ ” ከዚህ በሁዋላ ከኢህአዴግ ጋር አብሬ አልሰራም” ብለዋል ተብሎ ሲነገርላቸው የሰነበተው የኢህዴድ እና የኢህአዴግ የስራ ...
Read More »ከይዞታቸው የተነሱ ነዋሪዎች ተገቢውን ካሳ ባለማግኘታቸው ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡
የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በላሊበላ አብያተ ክርስትያናት ዙሪያ ያሉት አካባቢዎች እንዲፀዱና የበለጠ መስህብነት እንዲኖራቸው በማሰብ ከመንግስት በቀረበላቸው ዕቅድ በመስማማት አካባቢውን የለቀቁት ነዋሪዎች በተነገራቸው መጠን የካሳውን ገንዘብ ካለማግኘታቸውም ሌላ ሊሰራላቸው የታሰበው መሰረተ ልማት ባለመገንባቱ በችግር ላይ መሆናቸውን ተነሺዎች ተናግረዋል፡፡ በዘላቂ ቱሪዝም መቋቋም አለባቸው በሚል ከዓለም ባንክ ለነዋሪዎች የተመደበው የ300 ሚሊዮን ብር በጀት ለታሰበለት አላማ ያለመዋሉ ሚስጥር ...
Read More »አንድ ኢትዮጵያዊ በእቃ መጫኛ አውሮፕላን ውስጥ ተደብቆ ስዊድን ገባ
የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማንነቱ ያልተገለጠው ኢትዮጵያዊ በእቃ መጫኛ አውሮፐላን ውስት በመሆን ከ10 ሰአት ከ25 ደቂቃ በረራ በሁዋላ አርላንዳ አየር ማረፊያ ደርሷል። ግለሰቡ በመልካም ጤንነት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ስደተኝነት መጠየቁም ታውቋል። ነሃሴ ወር ውስጥ አንድ የአየር መንገድ ሰራተኛ በእቃ መጫኛ አውሮፐላን ውስጥ ሆኖ ስዊድን መግባቱ ይታወቃል። በሌላ ዜና ደግሞ በደቡብ አፍሪካ አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ተገድሏል። ...
Read More »የፖለቲካ ፓርቲ አባላት በአሸባሪነት ተከሰሱ
የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የካቲት 27 ቀን 2008 ዓ.ም. በጋሞ ጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ በሆነው አቶ ሉሉ መሰለ ስም በተከፈተው የክስ መዝገብ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ 13 ግለሰቦች ላይ በፌዴራል አቃቤ ሕግ የሽብር ክስ ተመሰረተባቸው። በጋሞ ጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አደራጅ በሆነው አቶ ሉሉ መሰለ ስም በተከፈተው የክስ መዝገብ የተካተቱት ተከሳሾች አቶ ሉሉ መሰለን ...
Read More »ኦብነግ ቻይናንና ጅቡቲን አስጠነቀቀ
የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግንባሩ የዓለማቀፉን የኢንርጂ ኃይል ሪፖርት ጠቅሶ ባወጣው መግለጫ – ቻይና፣ ጁቢቱና ኢትዮጵያ ተባብረው የኦጋዴንን ጋዝ ለመበዝበዝ እየሰሩ እንደሆነ በመጥቀስ፣ ከኦጋዴን -እስከ ጅቡቲ ድረስ የተፈጥሮ ጋዝን በቧንቧ ለማስተላለፍ አዲስ የሜጋ ፕሮጀክት መነደፉን እና የጂቡቲው ፕሬዚዳንትም “ዳመርጆግ” በተባለችው የጅቡቲ ከተማ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውን አትቷል። ቻይና፣ ጅᎅቲና ኢትዮጵያ ይህን ውልና ስምምነት ሲያደርጉ የተፈጥሮ ጋዙ ...
Read More »የአሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሏል ተባለ
ኢሳት (የካቲት 25 ፥ 2008) በአዲስ አበባ የነበረው የአሽከርካሪዎችና የመኪና ባለቤቶች የስራ ማቆም አድማ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች ተጠናክሮ ቀጠለ። የኢሳት ምንጮት ከተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች የላኩልን መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል ከተሞች የስራ ማቆም አድማው አድማሱን እያሰፋ ቀጥሏል። በዛሬው እለት በኦሮሚያ ነቀምት ከተማ የተካሄደው አድማ ግጭቶችን ያስከተለ ሲሆን የመንግስት ሃይሎች በከፈቱት ተኩስ የከተማው ህዝብ ከፍተኛ ስጋት ላይ መውደቁን ለማረጋገጥ ...
Read More »ኢትዮጵያንና ግብፅ ለመሸምገል እስራዔል ጣልቃ እንድትገባ ሃሳብ ያቀረቡት የግብፅ የፓርላማ አባል ከፓርላማ አባልነታቸው ተነሱ
ኢሳት (የካቲት 25 ፥ 2008) በቅርቡ የእስራዔል መንግስት ኢትዮጵያንና ግብፅ በአባይ ግድብ ዙሪያ ያላቸውን አለመግባባት ለመሸምገል ጣልቃ እንዲገባ ሃሳብን ያቀረቡ የግብፅ የፓርላማ አባል ከፓርላማ አባልነታቸው ተነሱ። የሃገሪቱ የፓርላማ አባላት የፓርላማ አባል የሆኑ ቶፊክ ኦካሻ ከእስራዔል አምባሳደር ጋር ያደረጉት የእራት ግብዣ ስነ-ስርዓት የሃገሪቱን የፓርላማ ስርዓት የጣሰ ተግባር ነው በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ ማቅረባቸው ታውቋል። ይህንንም ተከትሎ ለግብፅ ፓርላማ የቀረበ ሃሳብ የፓርላማ አባሉ ...
Read More »በጋምቤላ የእርሻ መሬት የወሰዱ ባለሃብቶች የተሰጣቸውን መሬት እንዲመልሱ ተወሰነ
ኢሳት (የካቲት 25 ፥ 2008) በጋምቤላ ክልል የእርሻ መሬቶችን የተረከቡ ወደ 100 አካባቢ ባለሃብቶች ክልሉ መሬቱን የሰጣችሁ በስህተት ነው በሚል መሬታቸውን እንዲመልሱ ተወሰነ። ባለሃብቶቹ በበኩላቸው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማፍሰስ በህጋዊ መንገድ ወደስራ መግባታቸውንና የተሰጣቸው ማሳሰቢያ ቅሬታን እንዳሳሰረባቸው በመግለጽ ላይ መሆናቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። የፌዴራልና የክልሉ መንግስት ተናበው ባለመስራታቸው ችግሩ መፈጠሩን የሚናገሩት ባለሃብቶቹ፣ ከስድስት አመት በፊት መሬቱን በህጋዊ መንገድ ከክልሉ መንግስት ...
Read More »