.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኢትዮጵያና ሱዳን በድንበር አካባቢ ተቆጣጣሪ ሃይል በሚሰማራበት ሁኔታ መከሩ

ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2008) ከኢትዮጵያ ጋር ድንበርን ለማካለል በዝግጅት ላይ የምትገኘው ሱዳን በሁለቱ ሃገራት የድንበር አካባቢ የጋራ ድንበር ተቆጣጣሪ ሃይል እንዲመሰረት አዲስ ሃሳብ አቀረበች። የኢትዮጵያና የሱዳን መከላከያ ሚኒስትሮች በዚህና ተጓዳኝ ጉዳዮች ዙሪያ በሱዳን መዲና ካርቱም መምከራቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ዘግቧል። የሱዳኑ መከላከላይ ሚኒስትር አዋድ ኢብን ኡፍ በሁለቱ ሃገራት መካከል በጋራ ሊቋቋም የታሰበው ሃይል የሁለቱን ሃገራት ጥቅም እንደሚያስጠብቅና በድንበሩ ዙሪያ ...

Read More »

የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች አሜሪካ ኢምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰማ

ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2008) የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች በኦሮሚያ ክልል የሚፈፅሙትን የሃይል እርምጃ በመቃወም ማክሰኞ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ። ያልተጠበቀ ነው የተባለውን ሰላማዊ ሰልፍ አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ያካሄዱት ተማሪዎች የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞን በሚያሰሙ ነዋሪዎች ላይ እየወሰዱ ያለውን የሃይል እርምጃ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ መጠየቃቸውም ታውቋል። ተማሪዎቹ ጥያቄያቸው ሰላማዊ እንደሆነ ለማሳየት ነጭ ጨርቅን እያውለበለቡ ጥያቄያቸውን ቢያቀርቡም ...

Read More »

በነቀምቴ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ተደበደቡ

ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2008) በነቀምቴ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ማቅረብ የጀመሩንት ጥያቄ ተከትሎ በዩኒቨርስቲው ትምህርት መቋረጡንና በርካታ ተማሪዎችም በጸጥታ ሃይሎች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል። የዩንቨርስቲ ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል እየተፈፀመ ያለው ግድያ እንዲያበቃ ጥያቄን ማቅረብ በጀመሩ ጊዜ በአካባቢው ሰፍረው የሚገኙ  የፀጥታ ሃይሎች እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ተማሪዎች ገልጸዋል። አራተኛ ወርን ዘልቆ የሚገኘው ይኸው ተቃውሞ ሰሞኑን በምስራቅና ምዕራብ ሃረርጌ አካባቢ ...

Read More »

በአርባ ምንጭ ከተማ የተቅማትና ትውከት ወረርሽን ተከሰተ

ኢሳት (የካቲት 29 ፥ 2008) በደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ የአጣዳፊ ተቅማትጥና ትውከት በሽታ በወረርሽኝ መልክ ተከስቶ ከ40 በላይ ሰዎች ለህክምና ሆስፒታል መግባታቸው ተገለጠ። ታማሚዎችን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለሞት ይዳረጋል የተባለው ይኸው ወረርሽኝ ከአርባ ምንጭ ከተማ በተጨማሪ በዙሪያዋ በሚገኙ የገጠር መንደሮች ጉዳት በማድረግ ላይ መሆኑንም የክልሉ ጤና ቢሮ ማክሰኞ አስታውቀዋል። እስካሁን ድረስ በሰው ህይወት የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የገለጸው የጤና ቢሮም ...

Read More »

ለተቃውሞ የወጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደበደቡ

የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ግድያ ይቁም የሚል መፈክር በመያዝና ነጭ ጨርቅ በማውለብለብ ወደ አሜሪካ ኢምባሲ ያመሩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ፣ በአካባቢው ሲደርሱ በፖሊሶች ተደብድበዋል። ተማሪዎቹ “እኛ አሸባሪዎች አይደለንም፣ ግድያው ይቁም!” የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን ተከትሎ ተማሪዎች ቢበታተኑም፣ ፖሊሶቹ ግን ተቃውሞውን አስተባብረዋል ያሉዋቸውን ይዘው በማሰር ላይ ...

Read More »

በአለም በር የሚገኙ አሽከርካሪዎች አድማውን ለሶስተኛ ቀን ቀጥለዋል

የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት አሽከርካሪዎችን በተመለከተ ያወጣው ህግ የሚያሰራ አይደለም በማለት ፣ በህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ሾፌሮች፣ የጀመሩት አድማ ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎአል። ሾፌሮቹ ዛሬ ወደ ደብረታቦር ከተማ በመሄድ ጥያቄያቸው መልስ እንዲያገኝ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ቢነጋገሩም ፣ ባለስልጣናቱ አድማ ላደረጋችሁበት 1 ሺ ብር ቅጣት ካልከፈላችሁ ስራ አትጀምሩም በማለታቸው፣ ተበሳጭተው መመለሳቸውንና በአድማው ለመቀጠል መወሰናቸውን ለኢሳት ...

Read More »

በኮንሶ ውጥረቱ እንደቀጠለ ነው

የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአስተዳደር ጋር በተያያዘ የኮንሶ ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ ተከትሎ በአካባቢው የሚታየው ውጥረት የቀጠለ ሲሆን፣ በደቤና ቀበሌ አቶ ሷይታ ጋራ የተባሉ ሰው በአካባቢው በሰፈሩት ፖሊሶች ተገድለዋል። ትምህርት ቤቶች አሁንም እንደተዘጉ ሲሆን፣በርካታ ሰዎችም ታስረዋል።ባለፈው ቅዳሜ የአካባቢው ህዝብ ከአርባምንጭ ጂንካ የሚወስደውን መንገድ በመዝጋት ተቃውሞውን የገለጸ ሲሆን፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት መንገዱን በመክፈት በርካታ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችን ...

Read More »

የአማራ ክልል የምክር ቤት አባላት በርካታ ጥያቄዎቸን አቀረቡ

የካቲት ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ክልሉ በሚያደርገው 5ኛ ዙር 3ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ከተለያዩ ዞኖች የተወከሉ የምክር ቤት አባላት በመቶዎች የሚቆጠሩ ጥያቄዎችን ጽፈው ለውይይት አቅርበዋል። ጥያቄዎቹ፣ በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ፣ ጸጥታና አስተዳዳር የተመለከቱ ናቸው። የምክር ቤት አባላቱ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት መፈጠሩንና ችግሩ አለመቀረፉን፣ በእርዳታ የሚሰጠው በቆሎ በቂ አለመሆን፣የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በድርቅ ምክንያት ...

Read More »

አንድ ኢትዮጵያዊ በአውሮፕላን ኮንቴይነር ተደብቆ ስዊድን ገባ

ኢሳት (የካቲት 28 ፥ 2008) ከአዲስ አበባ ወደ ስዊድን ይጓዝ በነበረ አውሮፕላን ውስጥ በኮንቴይር ተደብቆ ውስጥ ተደብቆ ወደሃገሪቱ የገባ አንድ ኢትዮጵያዊ በስዊድን ጥገኝነት ጠየቀ። ከ10 ሰዓት አስቸጋሪ በረራ በኋላ በስዊድን የደረሰ እና ማንነቱ እስካሁን ድረስ ይፋ ያልተደረገው ኢትዮጵያዊ በጥሩ ጤንነት ላይ መገኘቱን ስቶክሆልም ፖሊስ ቃል አቀባይ የሆኑት ካሪና ካገርለንድ ኤክስፕረስ ለተሰኘ ጋዜጣ ገልጸዋል። በሃገሪቱ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀው ኢትዮጵያዊ የተደበቀበት የእቃ ...

Read More »

13 ሰዎች ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ፈጥራችኋል በሚል የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

ኢሳት (የካቲት 28 ፥ 2008) በአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄን ለመሳተፍ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን አድርጋችኋል የተባሉ 13 ሰዎች የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው። ከአራት ወር በፊት ከአርባ ምንጭ ከተማ በጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ የተደረጉት እነዚሁ ተከሳሾች የፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርተው የነበሩ እንደሆነ ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ክሱን ሰዎች ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበው አቃቤ ህግ ...

Read More »