.የኢሳት አማርኛ ዜና

መንግስት እየጨመረ የመጣውን የማንነት ጥያቄ እንደማይቀበል ጠ/ሚኒስትሩ አስታወቁ

መጋቢት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ የመንግስትን የ6 ወር እቅድ ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት እንዳመለከቱት፣የማንነት ጥያቄ እየጨመረ መምጣቱ፣ለመንግስት ችግር ፈጥሯል። ከእንግዲህ ወዲያ ጥያቄውን አናስተናግድም ሊባል እንደሚገባ ተናግረዋል። ጥያቄውን ይዘው በተነሱት ላይ ሁሉ እርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል።ጠ/ሚኒስትሩ በማንነት ዙሪያ ችግሮችና አፈታታቸው ላይ ሰጡት መልስ እርስ በርስ የሚጣረስና መንግስት የገባበትን አጣብቂኝ የሚያሳይ ነው። በሰሜን ጎንደር ዞን ከቅማንት ...

Read More »

አንድ የአማራ ክልል የምክር ቤት አባል ከቅማንት ህዝብ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለተነሳው ግጭት መንግስትን ተጠያቂ አደረጉ

መጋቢት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በተካሄደው የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባዔ የቅማንትን ህብረተሰብ ወክለው የተገኙት ግለሰብ ለረዢም ዓመታት የኖሩትን ህዝቦች ለማጋጨት ሙከራ ሲደረግ ፈጥኖ ለምን እርምጃ እንዳልወሰደ አልገባኝም ብለዋል። ተቻችለው የሚኖሩት ሁለቱ ህዝቦች በጋብቻ ተሳስረው ፣አንድ ዓይነት ባህልና ወግ ያላቸው፣ አንድ አንሶላ ተጋፈው ለብሰው የኖሩ ሆነው እያለ፣ ቅማንትና አማራ በሚል የማተራመሱን ሴራ ሲፋፍሙ በነበሩ ሰዎች ...

Read More »

ህወሃት 15ሺ አዲስ ሰፋሪዎችን በወልቃይት መሬት ሊያሰፍር መሆኑ ተነገረ

ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) የህወሃት አገዛዝ ከ15ሺ የሚበልጡ አዳዲስ ሰፋሪዎችን በወልቃይት አካባቢ ሊያሰፍር መሆኑ ተሰማ። በሰሜን አሜርካ የወልቃይት ማህበረሰብ ተወካይ አቶ ቻላቸው አባይ እንደተናገሩት፣ የህወሃት መንግስት የጎንደርን ታሪካዊ መሬት በጉልበት ከወሰደ በኋላ በህዝቡ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ኣየፈጸመ ነው ብለዋል። “የወልቃይት የማንነት ጥያቄ፣ የፌዴራሊዝምን ስርዓት የሚንድ በመሆኑ በቀላሉ ልናየው አይገባም” የሚል መረጃ የህወሃት ደህንነቶች በኩል እያሰራጩ እንደሆነ የገለጹት አቶ ...

Read More »

አጣዳፊ ተቅማትና ትውከት በደቡብ፣ ሶማሊያና ኦሮሚያ ክልሎች እየተዛመተ ነው ተባለ

ኢሳት (የካቲት 30 ፥2008) ከቀናት በፊት በደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ከተማና ዙሪያዋ ባሉ አካባቢዎች የተከሰተው የአጣዳፊ ተቅማትና ትውከት (አተት) በሽታ በሶማሊያና ኦሮሚያ ክልሎች በመዛመት ላይ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ረቡዕ አስታወቀ። በዚሁ በሽታ እየተያዙ ወደህክምና ጣቢያዎች የሚሄዱ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ በመሄድ ላይ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል። የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እጥረትና የንጽህና መጓደል በሽታውን በወረርሽኝ መልክ እንዲከሰት ማድረጉን የሚናገሩት የህክምና ...

Read More »

ዴንማርክ ህጻናትን በማደጎ ሲወስድ የነበረው ፕሮግራም እንዲቋረጥ ወሰነች

ኢሳት (የካቲት 30 ፥2008) ላለፉት በርካታ አመታት ከኢትዮጵያ ህጻናትን በማደጎ ስትወስድ የቆየችው ዴንማርክ ፕሮግራሙ እንዲቋረጥ ወሰነች። በቅርቡ ወደኢትዮጵያ በመጓዝ በማደጎ ማቆያ ጣቢያዎች ላይ ጉብኝትን ያደረጉ የሃገሪቱ ባለስልጣናት አሰራሩ ከፍተኛ ክፍተት ያለበት መሆኑን በመረዳታቸው ውሳኔውን እንዳስተላለፉ ዘ-ሎካል የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። የሃገሪቱ የሃገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስቴር ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎም በርካታ ህጻናትን ከኢትዮጵያ ለመውሰድ ሲጠባበቁ የነበሩ የዴንማርክ ዜጎች ሌሎች አማራጮችን እንዲፈልጉ እንደተነገራቸው ታውቋል። ...

Read More »

በርካታ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ትናንት ካደረጉት ሰልፍ በኋላ መታሰራቸው ተገለጠ

ኢሳት (የካቲት 30 ፥2008) ትናንት ማክሰኞ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች የተካሄድውን ተቃውሞ ተከትሎ ቁጥራቸው በትክክል ሊታወቅ ያልቻለ ተማሪዎች ከስድስት ኪሎ ዩንቨርስቲ መታሰራቸው ተገለጠ። በጸጥታ ሃይሎች ለእስር የተዳረጉት ተማሪዎች ተቃውሞን አስተባብራችኋል ተብለው መጠርጠራቸው ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው ግድያና የጅምላ እስራት እንዲበቃ ጥያቄን ያቀረቡት የዩንቨርስቲው ተማሪዎች አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ...

Read More »

የኮንሶ ባህላዊ ንጉስን ጨምሮ ከ200 ያላነሱ ሰዎች ታሰሩ

የካቲት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ300 ሺ በላይ የሚሆኑ የኮንሶ ማህበረሰብ አባላት የአስተዳደር ጥያቄ መጠየቃቸውን ተከትሎ፣ በአካባቢው የሚታየው ውጥረት እንደቀጠለ ባለበት በዚህ ሰዓት ፣ የማህበረሰቡ ባህላዊ መሪ የሆኑት አቶ ካላ ገዛሃኝ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አርባምንጭ ከተማ ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ከኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ ገልጸዋል። ሌሎች የአገር ሽማግሌዎች ደግሞ የሚደርስባቸውን ወከባ በመፍራት ራሳቸውን መደበቃቸው ታውቋል። አቶ ካላ ገዛሃኝ ...

Read More »

የወልቃይት ጠገዴ የኮሚቴ አባላት ” ጉዳያቸው በሽማግሌዎች እየተጠና ነው” በሚል እየተሰጠ ያለውን መግለጫ አልተቀበሉትም

የካቲት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትግራይ ክልል ስር ሆነው መተዳደራቸውን አጥብቀው የሚቃወሙት የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ተወካዮች፣ የአማራ ክልል ፕ/ት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ፣ “ጥያቄያቸው በሽማግሌዎች እየተጠና መሆኑንና በሽማግሌዎቹ ውሳኔ መሰረት የወሰን ማካለል ለማካሄድ መታቀዱን” መናገራቸውን እንዳልተቀበሉት የአዲስ አበባው ዘጋቢ ገለጸ። የወልቃይት ህዝብ ተወካዮች ፣ “ለስርአቱ በወገኑ ሽማግሌዎች ጥያቄያችን ምላሽ ያገኛል ብለን ተስፋ አናደርግም” በማለት በክልሉ የተሰጠውን መግለጫ ...

Read More »

በኦሮምያ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ በውጭ ሃይሎች የተፈጠረ አይደለም ሲሉ ጠ/ሚኒስትሩ ተናገሩ

የካቲት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከኦል አፍሪካ ጋዜጠኛ ሪድ ክራመር ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ዘጋርድያን ይዞት የወጣ ሲሆን፣ ጠ/ሚኒስትሩ በኦሮምያ የሚታየው የህዝብ ተቃውሞ ከስራ አጥነት እና ከመሬት ዝርፊያ ጋር የተያያዘ እንጅ የውጭ ተጽእኖ የለበትም ብለዋል። የስራ አጡ ቁጥር 16 በመቶ በላይ መድረሱን፣ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው እድሜው ከ30 አመት በታች መገኘቱን የገለጹት አቶ ሃይለማርያም፣ ለዚህ ...

Read More »

የኤፍ 97.1 ዋና ዳይሬክተር ስርዓቱን ትተው እንግሊዝ ገቡ

የካቲት ፴ (ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደገለጹት አቶ አንድነት ዳኘው ስራቸውን በመልቀቅ ጥገኝነት የጠየቁት ከ2 ሳምንት በፊት ነው። በእርሳቸው ቦታ ምክትላቸው የነበሩት አቶ ኤርምያስ ጌታቸው ተተክተዋል። ኤፍ 97.1 በብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ ስር የሚተዳደር የመጀመሪያው የኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ነው።

Read More »