.የኢሳት አማርኛ ዜና

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ዛሬም ተቃውሞዎች ቀጥለዋል

መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢው ፓርቲ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎችን ባነሱ ዜጎች ላይ በአንድ በኩል የሃይል እርምጃውን አጠናክሮ በመቀጠል በሌላ በኩል ደግሞ የአገር ሽማግሌዎችንና በህብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት ይኖራቸው ይሆናል ብሎ የሚያምናቸውን ሰዎች በመጥራት፣ “ልጆቻችሁን ተቆጡልን፣ ጥያቄያቸውን እንመልሳለን” በማለት መረጋጋት ለመፍጠር ቢሞክርም፣ ሳምንቱን እንደታየው ሁሉ ዛሬም፣ ተቃውሞው በተለያዩ አካባቢዎች ተካሂዷል። ለአመታት የዘለቀው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ከጁምዐ ጸሎት በሁዋላ ...

Read More »

በዱባይ የታሰሩት ነጋዴዎች ቤተሰቦች መንግስት እንደረሳቸው ተናገሩ

መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከየካቲት 13 እስከ 17 ቀን 2008 በዱባይ “ገልፍ ፉድ ፌር ኤግዚቢሽን” ላይ ለመካፈል ሄደው ተከሰው ከሀገር እንዳይወጡ የተበየነባቸውን ስጋ ላኪ ባለሀብቶች፣ የኢትዮጵያ መንግስት በፍጥነት ጣልቃ ገብቶ ማስለቀቅ አለመቻሉ እንዳሳዘናቸው ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። ስድስት ያህል የሚሆኑት ታሳሪ ባለሀብቶች ቤተሰቦች እንደተናገሩት ኤግዚቢሽኑ በሚካሄድበት ወቅት አንድ ጥራት የሌለው የስጋ ምርት ሸጠውልኝ ለኪሳራ ዳርገውኛል ያለ የዱባይ ኩባንያ ...

Read More »

የሰቆጣ ነዋሪዎች በውሃ ጥም ልናልቅ ነው አሉ

መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ30 ሺ በላይ የሚሆነው የሰቆታ ህዝብ በከፍተኛ የውሃ እጥረት የተጠቃ ሲሆን፣ ነዋሪዎች አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር ችግሩ በሰው ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ተማሪዎች ውሃ ፍለጋ ሌሊቱን ሙሉ ሲንከራተቱ የሚያድሩ ሲሆን፣ በዚህም የተነሳ ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል አልቻሉም። በአካባቢው የውሃ ወልድ በሽታም እየተዛመተ መሆኑንም ነዋሪዎች ይናገራሉ።

Read More »

እጅግ በርካታ የቆዳ ፋብሪካዎች የአካባቢ ጥናት ሳይደረግባቸው በመቋቋማቸው በህዝብ ጤና ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው

መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መረጃዎች እንዳመለከቱት በመላ አገሪቱ 90 በመቶ የሚሆኑ የቆዳ ፋብሪካዎች የአካባቢ ደህንነት ጥናት ሳይደረግባቸው የተቋቋሙ በመሆኑ፣ በህዝቡ ላይ ችግር እያስከተሉ ነው። በአማራ ፣ በደቡብና በኦሮምያ ክልሎች ችግሩ እየተባባሰ ሄዶ ለሰዎችና እንስሳት ሞት ምክንያት እየሆነ ነው። በባህርዳር ከተማ የቆዳ ፋብሪካዎች በሚለቁት ኬሚካል የሚጠጡት ውሃ የተበከለባቸው ዜጎች በተደጋጋሚ አቤት ቢሉም የሚሰማቸው አላገኙም። በደቡብ ወሎ ...

Read More »

ኬንያ በከፍተኛ ቁጥር የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ለመቆጣጠር የድንበር ጥበቃ እንዲደረግ ጠየቀች

ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2008) በየዕለቱ ወደ ኬንያ የሚሰደዱ ኢትዮጵያን ቁጥር መጨመርን ተከትሎ የኬንያ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት መንግስት ተጨማሪ በጀትን በመመደብ የድንበር ቁጥጥሩ እንዲጠናከር ጠየቁ። በከዋሌ አውራጃ የሚገኘው የሃገሪቱ የኢሚግሬሽን ጽ/ቤት ወደ ኬንያ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመር ለጸጥታ ስጋት እየሆነ መምጣቱን ለመንግስት እንዳስታወቀ ዴይሌ ነሽን ጋዜጣ ዘግቧል። የግዛቲቱ የኢሚግሬሽን ኦፊሰር የሆኑት ቻርለስ ኡር ባለፉት ሁለት ወራቶች ብቻ ከ60 የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን በህገወጥ ...

Read More »

የወጪ ንግድ መቀነስ በሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ፈጥሯል ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2008) ባለፉት ስድስት ወራት የኢትዮጵያ ወጪ ንግድ ከተጠበቀው በታች ገቢ ማስገኘቱ በሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ተገለጠ። ዝቅተኛ አፈጻጸም ተመዝግቦበታል በተባለው በዚሁ የስድስት ወራት የውጭ ንግድ 1.6 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጓን የመንግስት ባለስልጣናት ረቡዕ አስታውቀዋል። በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለፓርላማ ሪፖርትን ያቀረቡት ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የሃገሪቱ የውጭ ንግድ ገቢ ዝቅተኛ አፈጻጸም ...

Read More »

ኢትዮጵያ የተማረ የሰው ሃይል ፍልሰት በከፍተኛ ሁኔታ ከተመዘገበባቸው አገሮች አንዷ መሆኗ አንድ አለም አቀፍ ተቋም ይፋ አደረገ

ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2008) ኢትዮጵያ የተማረ የሰው ሃይል ፍልሰት በከፍተኛ ሁኔታ ከተመዘገበባቸው 34 የአፍሪካ ሃገራት መካከል በ22ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧን አንድ አለም አቀፍ ተቋም ይፋ አደረገ። በሴኔጋል መዲና ዳካር አመታዊ ሪፖርቱን ያቀረበው የአፍሪካ የሂሳብ ሳይንስ ኢንስቲቲዩት የፖለቲካ አለመረጋጋት ዝቅተኛ ክፍያና የከፍተኛ ትምህርት እድሎች አለመኖር ችግሩን እያባባሱት እንደሚገኙ መግለጹን ሜይል ኤንድ ጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል። አፍሪካ ካላት አጠቃላት የሃኪሞችና የምህንድስና ባለሙያዎች ...

Read More »

አለም ቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት (ግሎባል አልያንስ) በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች 1 ሚሊዮን 67ሺ ብር ሰጠ

ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2008) አለም ቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት (Global Alliance for the Rights of Ethiopians) በድርቅና ረሃብ ተጠቅተው ህይወታቸው ለሞት አደጋ ለተጋለጡ ከ10 ሚሊዮን በላይ ዜጎች መርጃ የሚሆን አንድ ሚሊዮን ስልሳ ሰባት ሺህ ብር ለአለም-አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ተቋም (ወርልድ ቪዥን) በዋሽንግተን ዲሲ ጽህፈት ቤት ተገኝቶ አስረከበ። የትብብሩ ሊቀመንበር አክቲቪስት ታማኝ በየነ እና የስራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት ዶ/ር አክሎግ ...

Read More »

በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ በእስራት ተቀጡ

ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2008) በኢትዮጵያ እስላማዊ መንግስት ለመመስረት ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ ተከሳሾች ከአራት አመት እስከ 21 አመት በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን የፌዴራሉ ፍርድ ቤት ሃሙስ አስታወቀ። ማንነታቸውን ያልተገለጸው ተካሳሾች የአልቃይዳ አልሻባብ የምስራቅ አፍሪካ የሽብር መረብ ውስጥ አመራርና አባል በመሆን ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን የቀረበባቸው ክስ ማመልከቱን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በሃገሪቱ ህግ ከፍተኛ ነው የተባለው ቅጣት የተላለፈባቸው 28ቱ ተከሳሾች ከ13 አመት ...

Read More »

በሱርማ እየተፈጸመ ያለው ወንጀል፣ ለሱዳን ከተሰጠው የኢትዮጵያ መሬት ጋር ተያያዥነት እንዳለው ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 1 ፥ 2008) በሱርማ ብሄረሰብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ወንጀል ለሁለት አስርተ-አመታት የቆየ፣ መንስዔውም 100 ኪሜ የኢትዮጵያ የነበረ መሬት በደቡብ ሱዳን በመወሰዱ፣ እና አካባቢው የበለጸገና የተፈጥሮ ሃብት በኢንቨስትመንት ስም እየተነጠቀ ያለ በመሆኑ ነው ሲሉ የአካባቢው የፓርላማ አባል ገለጹ። ይህንን የገለጹት የሱርማ ብሄረሰብን በመወከል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት ከፓርላማ አባልነታቸው በፊት የቤንች ማንጂ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ...

Read More »