መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የማንነትና የአስተዳደር መካለል ጥያቄዎች መዘጋታቸውን ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ባወጁ ማግስት በኮንሶ 2 ሰዎች ተገድለዋል። እሁድ መጋቢት 4፣ 2008 ዓም የደቡብ ክልል ልዩ ሃይል ወደ ደበና ቀበሌ በመግባት ኤፍትስ በምትባል መንደር ላይ በአርሶአደሮች ላይ ተኩስ ከፍተው፣ ፋንታዬ ኮሪያ ኮንቴ እና ዳንኤል ቱሉ ከሮ የተባሉ ጎልማሶችን መግደላቸውን ሌሎችን ወጣቶችም ማቁሰላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሰመጉ በኦሮምያ የተገደሉትን ሰዎች ስም ዝርዝር በፎቶ አስደግፎ አወጣ
መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመንግስት ጫና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የሚለውን ስሙን ወደ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እንዲቀይር የተገደደው ሰመጉ፣ ያለበትን ጫና ተቋቁሞ ከህዳር 2 እስከ የካቲት 12፣ 2008 ዓም በኦሮምያ ክልል በ9 ዞኖች ፣ በ33 ወረዳዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉትን ሰዎች ስም ዝርዝር ይዞ ወጥቷል። ድርጅቱ በመግለጫው፣ ተቃውሞው እስካሁን የቀጠለ ፣ በአብዛኛው የኦሮሞያ ወረዳዎች የተካሄደና ...
Read More »ኦፌኮ የሽብርተኝነት ታርጋ ቢለጠፍበትም ትግሉን እንደማያቆም አስታወቀ
መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ባወጣው መገለጫ “ገዢው ፓርቲ የህዝብን ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ደግፈን በመቆማችን የኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት ድርጅታችንና አባሎቻችንን መክሰስ ገፍቶበታል” ብሎአል። “ገዥዉ ፓርቲም የችግሩ መንስኤ የኦሮሚያ ክልል አካሉ ኦህዴድ መሆኑን በሕዝብ ዜና ማሰራጫዎች ቢገልጽም፣ ለጥፋቱ ይቅርታ እንደመጠየቅ ፋንታ ባለፉት አራት ወራት ዉስጥ ዉስጥ ብቻ ከ270 በላይ የኦሮሞ ዜጎች ገድሏል፤ የፓርቲያችን አባላትና ...
Read More »የኦሮሞ ህዝብ ነጻነት እየተከፈለ ያለው መስዋዕትነት፤ የኦሮሞ ህዝብን ነጻነት ሳያጎናጽፍ በጦርነት ኣዋጅና ማስፈራሪያ ወደኋላ አይመለስም” ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አስታወቀ።
መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦነግ የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ፤የኦሮሞ ህዝብ ከአራት ወር በላይ ሲያደርገው በቆየው የጭቆና ፍጻሜ ኣመጽ ፤ተፈጥሮኣዊውንና በኣለምኣቀፍ ህግ ያለውን መብቱን ከማስከበር ውጪ ለሌሎች ህዝቦች ኣንዳችም ጥላቻ እንደሌለው፣ ይልቁንም ለሁሉም ህዝቦች መብቶች መከበር ፍላጎት ያለው መሆኑን በማያወላዳ ሁኔታ ለመላው ዓለም በተለይ ደግሞ ለኢትዮጵያ ተጨቋኝ ህዝቦች አስገንዝቧል ብሏል። የህዝቦች ጠላት የሆነው አገዛዝ ...
Read More »ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል በሳሊኒ ኩባንያ ላይ አቤቱታ አሰማ
መጋቢት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለአነሳ ህዝቦች መብት መከበር የሚታገለው ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ፣ ሳሊኒ በኦሞ ወንዝ ላይ በሚያካሂደው ግንባታ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በርሃብ እንዲጠቁ ማድረጉን በመጥቀስ፣ አቤቱታውን በኢኮኖሚ የበለጸጉት አገሮች ትብብር ድርጅት (OECD) አቅርቧል። የጣሊያን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ በኢትዮጵያና በኬንያ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚኖሩ አርብቶ አደሮችን ህይወት ማበላሸቱን የገለጸው ድርጅቱ፣ ግንባታው የቱርካና ሃይቅን ፍጻሜ ሊያስከትል ይችላል ብሎአል። ሳሊኒ ...
Read More »የአስገድዶ መድፈር ድርጊት ለተፈጸመባት ኢትዮጵያዊት የ150 ሺ ዶላር እንዲከፈላት ተወሰነ
ኢሳት (መጋቢት 2 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ከአመታት በፊት የአስገድዶ መድፈር ድርጊት ለተፈጸመባት ታዳጊ ወጣት ህጋዊ መብቷን በአግባቡ አላስቀመጠም በሚል የ1500 ሺ ዶላር (3 ሚሊዮን ብር በላይ) ካሳ እንዲከፍል የአፍሪካ ህብረት የሰብዓዊ መብት ፍርድ ቤት ወሰነ። ከአስር አመት በፊት በ13 አመቷ ታዳጊ ላይ ድርጊቱን የፈጸመው አብረው ጅማ ንጉሴ ጥፋተኛ መሆኑ ቢረጋገጥም ተበዳዩዋ ልጅአገረድ አይደለችም የሚል ይግባኝ ቀርቦ ክሱ ፍትህ ሳያገኝ ...
Read More »ድርቅ በተከሰተባቸው የተወሰኑ ክልሎች የኩፍኝ በሽታ በመዛመት ላይ መሆኑ ተነገረ
ኢሳት (መጋቢት 2 ፥ 2008) በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ ድርቁ በተከሰተባቸው ስድስት ክልሎች መካከል በሶስቱ በምግብ እጥረት በተጎዱ ህጻናት መካከል የኩፍኝ በሽታ በመዛመት ላይ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጠ። በምግብ እጥረት በተጎዱ ህጻናት መካከል ተከስቶ ያለው ይኸው የኩፍኝ በሽታ ለበርካታ ህጻናት ሞትን ምክንያትን ሊሆን እንደሚችል ድርጅቱ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። ባለፈው ወር በኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ሶማሊያ ክልል ...
Read More »በኬንያ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያንና ናይጀሪያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኢሳት (መጋቢት 2 ፥ 2008) የኬንያ ፖሊስ ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል ያላቸውን ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያንና ናይጀሪያውያን በቁጥጥር ስር አዋለ። የሃገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች ከቀናት በፊት 23 ኢትዮጵያውያንን በተመሳሳይ ሁኔታ ከያዙ በኋላ 114 ስደተኞች በቁጥጥር ስር ሲዉሉ የመጀመሪያው መሆኑን ዘስታንድራድ የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። 114 የሚሆኑት የኢትዮጵያን የናይጀሪያ ስደተኞች በመዲናይቱ ናይሮቢ ኑአሪካ ተብሎ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የተያዙ ሲሆን፣ ምን ያህሉ ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ...
Read More »ብሄራዊ ጭቆና እንዲቆም የሚጠይቅ ተቃውሞ በአዲስ አበባ ኑር መስጊድ ተካሄደ
ኢሳት (መጋቢት 2 ፥ 2008) በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱና መንግስት እየፈጸመ ያለውን ብሄራዊ ጭቆና እንዲቆም የሚጠይቅ ተቃውሞ አርብ አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው በኑር መስጊድ ተካሄደ። ለሶስተኛ ሳምንት በተካሄደው በዚሁ ተከታታይ ተቃውሞ የሙስሊሙ ማህበረሰብ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማትና በማውለብለብ እየደረሰብን ነው ያሉት ብሄራዊ ጭቆና እንዲያበቃ መጠየቃቸውን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የአርብ የጸሎት ስነ-ስርዓት ተከትሎ የተካሄደው ይኸው ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል እንግልት እስር ተጠናክሮ መቀጠሉ ዶ/ር መረራ ለኢሳት ገለጹ
ኢሳት (መጋቢት 2 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል እስርና ማንገላታቱ ተጠናክሮ መቀጠሉን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ገለጹ። ዶ/ር መረራ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ትናንት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በኦሮሚያ ክልል ስላለው ህዝባዊ ንቅናቄ አስመልክቶ በፓርላማ ቀርበው የተናገሩትን ንግግርም አጣጥለዋል። አቶ ሃይለማሪያም ይቅርታ የሚመልስና ጥፋትን የማመን ዝንባሌ ያሳዩት ለፈረንጅቱ ፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ነው ያሉት ዶ/ር መረራ፣ ኣሁንም በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ...
Read More »