ኢሳት (መጋቢት 6 ፥ 2008) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል እየተፈጸመ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ እርምጃዎችን እንዲወስድ ሂውማን ራይትስ ዎች ማክሰኞ ጥያቄውን አቅርቧል። ምክር ቤቱ በክልሉ እየተፈጸመ ባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ስጋቱን ይፋ እንዲያደርግ የጠየቀው ሂውማን ራይትስ ዎች ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ መንግስት ከሚወስደው የሃይል እርምጃ እንዲቆጠብ ግፊትን እንዲያደርግ አሳስቧል። ተቃውሞውን ተከትሎ ለእሰር የተዳረጉ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኦህዴድ ሁለተኛ ዙር ግምገማ እያካሄደ ነው
መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ በኦህዴድ ውስጥ የተነሳው የውስጥ እንቅስቃሴ አለመቋጨቱን የሚገልጹት ምንጮች፣ ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የድርጅቱ አባላት ለሁለተኛ ዙር ግምገማ ዛሬ ወደ አደማ እንዲገቡ ተደርጓል። የተለያዩ መስሪያ ቤት የቢሮ ሃላፊዎች፣ የየዞን ባለስልጣናት፣ የካቢኔ አባላትና ሌሎችም ባለስልጣናት ለከፍተኛ ግምገማ መጠራታቸውን ምንጮች ገልጸው፣ ግምገማው ለ10 ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ ከግምገማው በሁዋላ ተቃውሞ ተጠናክሮ በቀጠለባቸው ...
Read More »የተለያዩ ነጋዴዎች ምሬታቸውን ገለጹ
መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ እና በክልል ዋና ዋና ጅምላ ማከፋፈያ ቦታዎች የሚካሄደው ሽያጭ ማዕከላዊ የግብይት ስርዓት ያልጠበቀ አሰራር በመሆኑ በገንዘብ ደረሰኝ መመዝገቢያ ማሽን (ካስሪጂስተር) ለመስራት ትልቅ ችግር እየፈጠረ መሆኑን ተጠቃሚዎች ተናገሩ፡፡ በኢህአዴግ ንብረትነት በሚተዳደረው የአምባሰል ንግድ ስራዎች ድርጅት በብቸኝነት በሚቀርበው የገንዘብ ደረሰኝ መመዝገቢያ ማሽን (ካሽሪጂስተር) ለመስራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸውን በአማራ ክልል የሚገኙ ነጋዴዎች ...
Read More »በሀረር ሁለት ህጻናት በጅብ ተበሉ
መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የክልሉ ወኪል እንዳለው ከትናንት በስቲያ በ09 ቀበሌ ውስጥ አንድ የ10 አመት ህጻን ሲበላ፣ ከአምስት ቀናት በፊት ደግሞ ከከተማው ወጣ ብሎ በሚገኝ የገጠር ቀበሌ ላይ የ4 አመት ልጅ ተበልቷል። በአካባቢው የሚታየው ከፍተኛ የውሃ እና የምግብ እጥረት እንዲሁም አለመረጋጋት በህዝቡ ህይወት ላይ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ በሚገኝበት ሰአት ፣ ጅብ በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረስ ...
Read More »በሶስት ክልሎች የኮሌራ ወረሽኝ ተከሰተ
መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ክልል አርባምንጭ ዙሪያ አማሮና አባያ ወረዳዎች በኦሮሚያ ክልል በቦረና ዞን ገላን ወረዳና በሶማሌ ክልል ሞያሌ ወረዳዎች ላይ የኮሌራ ወረሽኝ ተከስቷል። በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ በመምጣት ላይ ሲሆን፣ ካለፈው እሁድ ጀምሮ ከ140 በላይ ህሙማን በዚሁ በሽታ ተይዘው ወደ ሆስፒታል መግባታቸውንና ለህሙማኑ የህክምና ማዕከል ተቋቁሞ ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የአርባ ምንጭ ሆስፒታል ...
Read More »በኮንሶ ግጭት ተቀስቅሶ 3 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ
ኢሳት (መጋቢት 5 ፥ 2008) ሰሞኑን በደቡብ ክልል ኮንሶ ከአስተዳደራዊ ጥያቄ ጋር በተገናኘ የተቀሰቀሰው ግጭት ኣሁድ በድጋሚ አገርሽቶ ሶስት ነዋሪዎች መገደላቸውን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። የአካባቢው ነዋሪ የኮንሶ ወረዳ ወደ ዞን ደረጃ እንዲዋቀር ጥያቄን ለክልሉና ለፌዴራል መንግስት ቢያቀርቡም ጥያቄያቸው የሃይል ምላሽን እያገኘ እንደሆነ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል። አካባቢው በጸጥታ ሃይሎች ተከቦ እንደሚገኝ የተናገሩት እማኞች የጸጥታ ሃይሎች ሰላማዊ ጥያቄን ለማቅረብ በተሰባሰቡ ነዋሪዎች ላይ የተኩስ ...
Read More »በኦሮሚያ የመንግስት ሃይሎች አስገድዶ መድፈርና ሌሎች ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መፈጸማቸው ታወቀ
ኢሳት (መጋቢት 5 ፥ 2008) የኢትዮጵያ የፀጥታ ሃይሎች በኦሮሚያ ክልል በወሰዱት የሃይል እርምጃ የአገድዶ መድፈር ድርጊትን ጨምሮ የተለያዩ የሰብዓዊ መብትን ጥሰቶችን መፈጸማቸውን የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ሰኞ ይፋ አደረገ። መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ድብደባን ጨምሮ የጅምላ እስራትና ስቃዮች ስለመፈጸማቸው ማስረጃዎች መገኘታቸውን እንደገልፀ አሶሼይትድ ፕሬስ (Associated Press) ዘግቧል። በክልሉ ስለተፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው የሰብዓዊ መብቶች ...
Read More »ልማት ባንክ የውጭ ምንዛሪን ለሚያስገኙ ተቋማት ሲሰጥ የነበረውን የብድር አገልግሎት ወለድ መጠን ቀየረ
ኢሳት (መጋቢት 5 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በውጭ ንግድ ላይ ተሰማርተው ለሃገሪቱ የውጭ ምንዛሪን ለሚያስገኙ ተቋማት ሲሰጥ የቆየውን አነስተኛ የወለድ መጠን እንዲቀየር ሰኞ ወሰነ። ለኩባንያዎቹ ማበረታቻው የተሰጠው ለመንግስት ገቢ የሚያደርጉትን የውጭ ምንዛሪ ለማበረታት ታስቦ የነበረ ቢሆንም፣ ሃገሪቱ የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ እየቀነሰ በመምጣቱ ሳቢያ ማበረታቻው እንዲቀየር መደረጉን ባንኩ ገልጿል። ለመንግስት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ያመጣሉ የሚባሉ ድርጅቶች ከስምንት እስከ ዘጠኝ በመቶ ...
Read More »ከውጭ በሚገቡ ቁሳቁሶች ላይ የዋጋ ግሽበት መታየቱን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 5 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት ተከትሎ ከውጭ በሚገቡ ቁሳቁሶች ላይ የዋጋ ግሽበቱ እያደገ መምጣቱን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ። ባለፈው ወር ተመዝግቦ የነበረው ይኸው የዋጋ ግሽበት ከ7.9 በመቶ ወደ 8.2 በመቶ ማደጉን ከኤጀንሲው የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች በበኩላቸው ሃገሪቱ አጋጥሟት ያለው የውጭ ምንዛሪ እጥረት በሸቀጣሸቀቶች ላይ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ በኢኮኖሚ እድገቱ ላይ ...
Read More »በኢትዮጵያ በከፋ የምግብ እጥረት የሚጎዱ ሰዎች እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ አንድ አለም አቀፍ ድርጅት አስታወቀ
ኢሳት (መጋቢት 5 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ በከፋ የምግብ እጥረት የሚጎዱ ሰዎች ቁጥር በአለም አቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው 15 በመቶ በላይ መድረሱ እንዳሳሰበው የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ይፋ አደረገ። እየተባባሰ የመጣውን የድርቅ አደጋ ተከትሎ ለከፋ የምግብ ጉዳት የተጋለጡ ሰዎች ቁጥር ከ20 በመቶ በላይ መድረሱን የተቋሙ ሃላፊዎች መግለጻቸውን USA Today ጋዜጣ ዘግቧል። ድርቁ እያደረሰ ያለው ጉዳት በአለም አቀፍ ደረጃ ...
Read More »