መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የወልቃይትን የአማራ ማንነት ጥያቄ ከሚመሩት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ሊለይ ብርሃነ በትግራይ ፖሊሶች ታፍነው መወሰዳቸውን ተከትሎ፣ የአካባቢው ህዝብ የጀመረው ተቃውሞ እንደቀጠለ ሲሆን፣ ተቃውሞውን ለመበተን በደንሻ ነዋሪዎች ላይ ጥይቶችን ተኩሰዋል። የፖሊስ እርምጃ ያበሳጫቸው ነዋሪዎች መንግዶችን በመዝጋት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥ ያደረጉ ሲሆን፣ በአካባቢው ያለው ውጥረት ይህን ዜና እሳካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ቀጥሎአል። የትግራይ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በደቡብ ኦሞ መሬት የወሰዱት የህወሃት አባላት በአካባቢው ብቅ ብለው እንደማያውቁ ተነገረ
መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ኦሞ ዞን መሬትና የባንክ ብድር ከወሰዱት ባለሃብቶች መካከል ከ98 በመቶ በላይ የሚሆኑት የህወሃት አባላት መሆናቸውን በሚመለከት ኢሳት ዜና መዘገቡን ተከትሎ፣የደቡብ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ እንደተናገሩት፣ መረጃው ሙሉ በሙሉ ትክክል እንደሆነና ድርጅታቸው በቅርብ የሚያውቀው ጉዳይ መሆኑን ግልጸዋል።መሬቱን የወሰዱት የትግራይ ተወላጅ የህወሃት አባላትና ደጋፊዎች፣ ወደ አካባቢው ብቅ ብለው ...
Read More »ቤተ እስራኤላዊያን በእየሩሳሌም የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- እስራኤል ውስጥ የሚኖሩ ቤተ እስራኤላዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ቤተሰቦቻቸው እንዲመጡላቸው በማለት እሁድ እለት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በእየሩሳሌም አካሂደዋል። ኢትዮጵያዊ ቤተ – እስራኤላዊያኑ በኢትዮጵያ ያሉ ቤተሰቦቻቸውን ምስልን በመያዝ መድልዎ ይቁም፣ ዘረኝነት ይብቃ፣ የሚልና ሌሎችንም መፈክሮች በማንገብ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት ፊት ለፊት በመሄድ ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ቁጥራቸው በግምት ከሁለት ሽህ ...
Read More »በወሎና ደቡብ ጎንደር አዲስ ወረርሽኝ ተከሰተ
መጋቢት ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ምንነቱ እስካሁን ያልታወቀው ወረርሽኝ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎችን አጥቅቷል።በበሽታው የተያዘ ሰው ከፍተኛ ሙቀት፣ ራስ ምታት፣ ሳልና ተቅማጥ እንደሚኖረው የገለጹት ነዋሪዎች፣በሽተኞች እስካሁን ህክምና ባለማግኘታቸው ህይወታቸው በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ገብቷል። በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ የምግብና የውሃ እጥረት መኖሩ፣ ችግሩን እንዳባባሰው ነዋሪዎች ግልጸዋል።
Read More »በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎች ወደ ረሃብ ሊደርስ በሚችል ደረጃ መመደባቸው ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 9 ፥ 2008) በአፋርና በሶማሊ ክልሎች እንዲሁም በሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ በርካታ ዞኖች ወደረሃብ ደረጃ ሊሻገር በሚችል ድረጃ ውስጥ መመደባቸውን የረሃብ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ትንበያ የሚሰጥ ፋሚን ኧርሊ ዋንርኒንግ (Famine Early Warning System) የተባለ ድርጅት አርብ ይፋ አደረገ። በሃገሪቱ ተከስቶ ያለውን የድርቅ መባባስ ተከትሎ አብዛኛው የሰሜን አርቶብ-አደር አካባቢዎች ደረጃ አራት ተብሎ በሚመደበውና ለረሃብ አንድ ደረጃ በቀረው ሰንጠረዥ ውስጥ መመደባቸውን ...
Read More »የሉቴኒያ ኩባንያ የኢትዮጵያ ተዋጊና እቃ-ጫኝ አውሮፕላኖችን ሊጠግን ነው
ኢሳት (መጋቢት 9 ፥ 2008) መቀመጫውን በቀድሞ ሶቪየት ህብረት ስር በነበረችው ሉቴኒያ ያደረገ አንድ የአውሮፕላን ቁሳቁሶች አቅራቢ ኩባንያ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ተዋጊና እቃ ጫኝ አውሮፕላኖች ለመጠገን ስምምነት ፈፀመ። ይኸው ኤፍ-ኤል-ቴክኒክስ (FL-Technics) የተሰኘው ተቋም ኤሮ L-39 የተሰኙ የመለማመጃ ጀቶች እንዲሁም ሁለገብ ለሆኑ አንቶኖቭ አውሮፕላኖችና ተዋጊ አውሮፕላኖች መለዋወጫ እቃዎችን እንደሚያቀርብ ገልጿል። የተደረገውን የገንዘብ ስምምነት ከመግለጽ የተቆጠበው ኩባንያው እድሜ ጠገብ የሆኑ አውሮፕላኖች ለመጠገን ...
Read More »የፌዴራልና የክልል ጸጥታ ሃይላት በሻሸመኔ ከተማ መሰብሰባቸው ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 9 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልልና ሌሎች አካባቢዎች የተቀሰቀሱ ግጭቶችን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፌዴራልና የክልል የጸጥታ አካላት ሃገራዊ የጸጥታ ምክክርን ለማካሄድ በሻሼመኔ ከተማ መሰብሰባቸው ተገለጸ። የፖሊስ ኮሚሽነሮችን ጨምሮ ሌሎች የጸጥታና የደህንነት እንዲሁም የማረሚያ ቤት አስተዳደሮችን ያካተተው ይኸው ልዩ የምክክር መድረክ በተለያዩ አካባቢዎች ተቀስቅሰው በሚገኙ ግጭቶች ዙሪያ እንደሚመክር ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ...
Read More »በኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራሮችና ሌሎች ታሳሪዎች ተጨማሪ የ28 ምርመራ ቀን ተጠየቀባቸው
ኢሳት (መጋቢት 9 ፥ 2008) ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተቃውሞ ጋር በተገናኘ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ለእስር የተዳረጉ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራርና ሌሎች 22 የፓርቲው አባላት ፖሊስ የተጠየቀባቸው የ28 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ከፍርድ ቤት ተቀባይነት አገኘ። በኢህአዴግ የተጻፈው የኢትዮጵያ ህገ-መንግስት ማንኛውም የፍርድ ሂደት ግልጽ በሆነ ሁኔታ ይካሄዳል ቢልም፣ አርብ አራዳ በሚገኘው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተሰይሞ የነበረው ችሎት በዝግ መካሄዱንና በሰፋሪው ቁጥር ...
Read More »ዜጎች በርሃብ ምክንያት መሰደዳቸውን ቀጥለዋል
መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የሚታየውን ረሃብ መንግስት ለገጽታ ግንባታ በሚል ለመደበቅ ጥረት በማድረግ ላይ ቢሆንም፣ ዜጎች ግን የመንግስትን ከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር እያለፉ ወደ ተለያዩ ከተሞች በመሰደድ ላይ ናቸው። ከዚህ ቀደም በታሪካቸው ድርቅ ጎብኝቷቸው የማያውቁት ቦታዎች ሳይቀሩ ረሃቡን መቋቋም ተስኖአቸው እየተሰደዱ ነው። የአዲስ አበባው ወኪላችን ያነጋገራቸው አርሶአደር የሁለት ልጆች አባት ሲሆኑ ከሁለት ሳምንት በፊት እርሳቸውና ...
Read More »መንግስት በህዝብ እየተተቸ ቢሆንም፣ የባለስልጣናቱን ቤት ግንባታ ቀጥሎበታል።
መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ ረሃብ የህዝቡን ህይወት አደጋ ውስጥ በከተተበት በዚህ ወቀት ከ150 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚወጣበት የ6 ባለስልጣናት ቤት ስራ በፍጥነት እየተሰራ ነው። የኢሳት የአዲስ አበባ ወኪል ግንባታውን በቅርብ ሄዶ ተመልክቶታል። ለስድስት ከፍተኛ ጡረተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለእያንዳንዳቸው በ25 ሚሊየን ብር ወጪ በስጦታ የሚለገሳቸው የመኖሪያ ቤት የሚገነባው ከህወሃት ጋር በቅርበት ይሰራሉ በሚባሉት በተክለብርሃን ...
Read More »