.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአርሲ አዳባ የመንግስት ካድሬዎች የሃይማኖት ግጭት ለማስነሳት ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበር ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 13 ፥ 2008) ከኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ጋር ተያይዞ በተነሳው ግጭት በአርሲ አዳባ ከተማ የመንግስት ካድሬዎች በሙስሊሞችና ክርስቲያኖች መካከል ግጭት ለማስነሳት ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበር በአካባቢ የሚኖሩ ኢሳት ያነጋገራቸው ሰዎች ገለጹ። የመንግስት ካድሬዎች በመስጊድ ውስጥ ከአንድ ወር በፊት ለፈነዳው ቦምብ  ተጠያቂዎቹ “የአማራ ብሄር ተወላጆች” እንደሆኑ መስጊድ ውስጥ በመገኘት ሲቀሰቅሱ እንደነበር እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። እነዚህ የመንግስት ካድሬዎች በኦሮሚያ በተቀሰቀሰው ግጭት  ...

Read More »

የኦህዴድ አባላት አቶ አባይ ጸሃዬ በህግ እንዲጠየቁላቸው ጠየቁ

መጋቢት ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜ በተጠናቀቀው የኦህዴድ የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ግምገማ ፣ የህወሃቱ መስራችና ነባር ተጋይ አቶ አባይ ጸሃዬ፣ ኦህዴድን በተመለከተ የተናገሩት ንግግር በክልሉ ለደረሰው የሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት ውድመት ዋና ተጠያቂ ነው በማለት ህወሃት አቶ አባይን ገምግማ ለፍርድ እንድታቀርብ ጠይቀዋል። ቤቱ በውይይቱ ” ችግራችን የመስመር ወይም የአላማ ችግር ሳይሆን የአመራር ችግር ነው” ...

Read More »

የፌዴራል ፖሊስ ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ እንዲሆን የሚደነግግ አዋጅ በዛሬው ዕለት ለፓርላማ ቀረበ፡፡

መጋቢት ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአሁኑ ወቅት ፌዴራል ፖሊስ ተጠሪነቱ ለፌዴራልና አርብቶአደር ልማት ሚ/ር ሲሆን አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ፖሊስን ለአንድ አስፈጻሚ መ/ቤት ብቻ ተጠሪ አድርጎ መቀጠል የአሰራር ክፍተት ይፈጥራል ተብሎ በመታሰቡ ወደፊት በጥናት ላይ ተመስርቶ እስኪወሰን የፌዴራል ፖሊስ ተጠሪነት ለጠ/ሚኒስትሩ እንዲሆን በረቂቅ አዋጁ ተደንግጎአል፡፡ በመሆኑም አሁን በስራ ላይ ያለው የፌዴራል ፖሊስ ኮምሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከተማ የውሃ ችግር ተባብሶ ቀጥሏል

መጋቢት ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎች እንደሚሉት በተለይ በአራት ኪሎ ቤተ መንግስት አካባቢ፣ መገናኛ፣ ልደታ፣ ኮተቤ፣ ጉርድ ሾላ፣ አብነት አካባቢ ችግሩ በከፋ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል። የአካባቢው ነዋሪዎች ለአራት ቀናት ያክል ውሃ ማግኘት እንዳልቻሉና በዚህም ሳቢያ እናቶች ልጆቻቸውን ምግብ አብስሎ ለመመገብና ንጽሕናቸውን ለመጠበቅ እንዳልቻሉ ነዋሪዎቹ አስታውቀዋል። አቅሙ ያላቸው የታሸገ ውሃ በመግዛት ሲጠቀሙ ድሃው አብዛሃኛው የከተማዋ ነዋሪ ...

Read More »

የቀበሌ ቤቶችን ሲጠቀሙ የነበሩና ሃብት ያፈሩ ከፍተኛ የመንግስት ተሿሚዎችና ነዋሪዎች የተለያዩ ምክንያት በመፍጠር ቤቶችን ለተቸገሩት ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተነገረ፡፡

መጋቢት ፲፫ (አሥራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በአማራ ጠቅላይ ፍርድቤት ለተመረጡ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ በፍርድ ቤት ዙሪያ ለሚሰሩ ባለሙያዎችና ለመንግስት አመራሮች ባቀረበው የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የቀበሌ ቤትን በተመለከተ የቀረቡ በርካታ አቤቱታዎች ቢኖሩም ፍርድቤቶች አፋጣኝ ምላሽ ያልሰጡ መሆኑን ተሰብሳቢዎችና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡ በጠቅላይ ፍርድቤት በኩል ሪፖርት ያቀረቡት ባለሙያ ተሰብሳቢዎች ያቀረቡት አስተያየት ትክክል መሆኑን አምነዋል፡፡የራሳቸውን መኖሪያቤት ከመንግስት ...

Read More »

ለባለሃብቶች ሲሰጥ የነበረው የእርሻ መሬት ፈቃድ የተፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ እንዲቆም ተደረገ

ኢሳት (መጋቢት 12 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ላለፉት አስር አመታት ያህል ከሃገር ውስጥና ከውጭ ባለሃብቶች ለሰፋፊ የእርሻ መሬቶች ሲሰጥ የቆየውን ፈቃድ እንዲቀር አደረገ። የግብርና ኢንቨስትመንት እና የመሬት አስተዳደር ኤጀንሲ ከዘርፉ ይመጣል ተብሎ የታሰበው የቴክኖሎጂ ሽግግር የተፈለገውን ውጤት ሊያመጣ ባለመቻሉ ምክንያት ፕሮግራሙ እንዲቆም መደረጉን ገልጿል። ኤጀንሲው ባለፉት ጥቂት አመታት ከአራት ክልሎች 470 ሺህ ሄክታር መሬትን ተረክቦ ለ131 ባለሃብቶች ቢሰጥም ውጤታማ የሆኑት ...

Read More »

በአዲስ አበባ የከፋ የውሃ እጥረት ሊከሰት ይችላል ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 12 ፥ 2008) ለአዲስ አበባ ከተማ የመጠጥ ውሃን ለሚያቀርበው ለገዳዲ የውሃ ግድብ ተጨማሪ ውሃን በማቅረብ ሲያገልግል የነበረው የድሬ ግድብ በቀጣዩ ወር ሙሉ ለሙሉ አገልግሎትን እንደሚያቋርት የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ። የግድቡ አገልግሎት ማቋረጥም በከተማ ነዋሪዎች ዘንድ የከፋ የውሃ እጥረት እንዲከሰት እንደሚያደርግ ባለስልጣኑ አሳስቧል። ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የ24 ሰዓት የውሃ አገልግሎት የሚያገኙ ዋና ዋና አካባቢዎች ከተያዘው ...

Read More »

በኮንሶ በርካታ ሰዎች ከቀያቸው ተሰደዱ፣ በርካቶች ታሰሩ

ኢሳት (መጋቢት 12 ፥ 2008) በቅርቡ በደቡብ ክልል በኮኖሶ አካባቢ የተነሳውን አስተዳደራዊ ጥያቄ ተከትሎ በርካታ ሰዎች ከቀያቸው መሰደዳቸውንና ወደ 170 ሰዎች አካባቢ በኮንሶ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ታስረው እንደሚገኙ ከቀያቸው የተሰደዱ ነዋሪዎች ለኢሳት አስታውቀዋል። በከተማዋ በአራቱም አቅጣጫ የፌዴራልና የክልሉ ልዩ ሃይሎች ተሰማርተው እንደሚገኙ የገለጹት የአካባቢው ተወላጆች ከ80 የሚበልጡ ሰዎች ከነቤተሰቦቻቸው ተሰደው እንደሚገኙ አስረድተዋል። ለደህንነታቸው ሲሉ ማንነታቸውን ከመግለጽ የተቆጠቡት እነዚሁ የአካባቢው ...

Read More »

የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የጸጥታና የደህንነት ድጋፍ እንዲቆም ጠየቁ

ኢሳት (መጋቢት 12 ፥ 2008) የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በቅርቡ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት ተከትሎ የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በብሪታኒያ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው የጸጥታና የደህንነት ድጋፍ እንዲቆም አሳሰቡ። ሃገሪቱ ዜጋዋ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው በእስር ላይ እያሉ በየአመቱ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ለጸጥታና ደህንነት ስልጠናዎች ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኗን ጋዜጣው የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ባቀረበው ዘገባ አስፍሯል። ብሪታኒያ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው ይኸው ...

Read More »

በወልቃይት ነዋሪዎችና በትግራይ ልዩ ሃይል መካከል የተኩስ ልውውጥ መካሄዱ ተነገረ

ኢሳት (መጋቢት 12 ፥ 2008) ከወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ጋር በተገናኘ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ እሁድ በወልቃይት ዳንሻ ግጭት ማስነሳቱን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። በአካባቢው የተቀሰቀሰውን ይህንኑ ግጭት ተከትሎም በትግራይ ልዩ ፖሊስና በወልቃይት የታጠቁ ነዋሪዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ ማካሄዱንና መንገዶች መዘጋታቸውንም እማኞች አስታውቀዋል። እሁድ የተቀሰቀሰው ግጭት ሰኞ ድረስ እልባት አለማግኘቱን የተናገሩት ነዋሪዎች፣ ሁለት የዳንሻ የማንነት ኮሚቴ አባላት ለእስር መዳረጋቸውንም እማኞች ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ ...

Read More »