.የኢሳት አማርኛ ዜና

በማዕከላዊ እስር ቤት የህወሃት መርማሪዎች ከፍተኛ ሰቆቃ እንደሚፈጽሙ ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 14 ፥ 2008) በማዕከላዊ እስር ቤት የህወሃት መርማሪዎች ከፍተኛ አካላዊና ሞራላዊ ሰቆቃ በታሳሪዎች ላይ እንደሚፈፅሙ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ምክትል ፕሬዚደንት የነበሩት አቶ ዘመነ ምህረቱ ገለጹ። ከአስራ አራት ወራት እስር በኋላ ባለፈው መጋቢት 8, 2008 በዋስ የተለቀቁት አቶ ዘመነ ምህረት፣ በወህኒ ቤቶች ውስጥ ለምርመራ የተሰማሩት የህወሃት ገራፊዎች ለመናገር የሚከብድ ሰቆቃ በእርሳቸው ላይ እንደፈጸሙባቸው ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ...

Read More »

ወደ ዳንሻ የሚወስዱት መንገዶች በቅድመ ሁኔታ ተከፈቱ

መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ሊላይ ሲሳይ፣ ከጎንደር ከተማ ተንስተው ወደ ዳንሻ ሲያመሩ መንገድ ላይ በጥቁር ላንድ ክሩዘር መኪና ይጓዙ የነበሩ ሰዎች፣ ከሾፌሮች ጋር በመነጋገር አፍነው ከወሰዱዋቸው በሁዋላ የአካባቢው ህዝብ ባስነሳው ተቃውሞ፣ መንገዶች ላለፉር አራት ቀናት ተዘግተዋል። በዳንሻና በሶረቃ ትምህርት ቤቶች የተዘጉ ሲሆን፣ መረጃው ወደ ተለያዩ ...

Read More »

የአባይን ግድብ ሊጎበኙ የሄዱ የመንግስት ጋዜጠኞች ታገዱ

መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአባይን ግድብ 5ኛ የምስረታ አመት ለማክበር ሽር ጉድ እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ስለግድቡ ለመዘገብ ወደ ስፍራው የተንቀሳቀሱ ጋዜጠኞች መንገድ ላይ እገዳ ተጥሎባቸዋል። ከአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ የተውጣጣው የጋዜጠኞች ቡድን፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በሚል ወደ ግድቡ እንዳይገቡ ተደርጓል። የፕሮጀክቱ ስራ መሪ ኢንጂነር ስመኛው ጉብኝቱ ከመካሄዱ በፊት ተጠይቀው፣ ጋዜጠኞች ቢመጡ ችግር እንደሌለና ሙሉ ...

Read More »

በኦሮምያ በተነሳው ግጭት ከፍተኛ ንብረት አልወደምም ሲሉ አቶ ሃይለማርያም ተናገሩ

መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኮሚኒኬሽን ሚኒስትርና የመንግስት ጋዜጠኞች በክልሉ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከፍተኛ የሆነ የንብረት መውደም አስከትሏል በማለት ሲዘግቡ ቢቆዩም፣ ጠ/ሚኒስትሩ ግን በባለሀብቶች ንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት ከ100 ሚሊየን ብር የማይበልጥና ጉዳቱም አነስተኛ በመሆኑ ባለሀብቶቹን እንዳላስደነገጠ ተናግረዋል። አቶ ሀይለማርያም ከመንግስታዊው ዜና አገልግሎት ጋር ሰሞኑን ባደረጉት ቃለምልልስ በሀገሪቱ ቱርክ፣ ቻይናና ህንድ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እንዳላቸው፣ ባለሀብቶቹ መሰል ...

Read More »

ለንግድ ሱቆች በወጣ የሽያጭ ጨረታ አስደንጋ ጭ ዋጋ ተሰጠ።

መጋቢት ፲፬ (አሥራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአብዛኛው ባለፈው አመት መጋቢት ወር በ10ኛ ዙር እጣ የወጣባቸው ኮንደሚኒየም ቤቶች ጋር አብረው ለተሰሩ ለንግድ ሱቆች በወጣ ጨረታ አስደንጋጭ ዋጋ ተሰጥቷል። ንብ ባንክ በልደታ አካባቢ ለሚገኝ የኮንደሚኒየም የንግድ ቤት ለአንድ ካሬሜትር 101 ሺ111 ብር ከ11 ሳንቲም እጅግ የተጋነነ ዋጋ በመስጠት 87 ነጥብ 19 እና 76 ነጥብ 29 ካሬሜትር ሁለት ቤቶችን አሸናፊ ...

Read More »

የኢህአዴግ መንግስት 499ሺ ቶን ስንዴን ለመግዛት አለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱን ሮይተርስ ዘገበ

ኢሳት (መጋቢት 13 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ መንግስት 499ሺ ቶን ስንዴን ለመግዛት አለም አቀፍ ጨረታ ማወጣቱን ሮይተርስ የአውሮፓ የንግድ ተቋማት ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘገበ። የእርዳታ ድርጅቶት በበኩላቸው ከሁለት ሳምንት በኋላ ለተረጂዎች የሚቀርብ እርዳታ ሊያልቅ የሚችል በመሆኑ ድርቁ የከፋ ጉዳት ማድረስ ይጀምራል ሲሉ በድጋሚ አሳስበዋል። ከአለም አቅፍ ገበያ ተገዝቶ ወደሃሪቱ የሚገባው የስንዴ አቅርቦት በትንሹ ...

Read More »

የመሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር አዋጅ እየተዘጋጀ ነው ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 13 ፥ 2008) በተለያዩ ክልሎች የህገ ወጥ መሳሪያዎች ዝውውር መስፋፋትን ተከትሎ የመሳሪያ ዝውውሩን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ (ህግ) እየተዘጋጀ መሆኑን የፌዴራልና አርብቶ አደር ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታወቀ። በጋምቤላ ክልል ብቻ በ13 ወረዳዎች ውስጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር መኖርንና ችግሩ ከክልሉ ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት መፍጠሩን የክልሉ ባለስልጣናት ገልጸዋል። ክልሉ ከጎረቤት ደቡብ ሱዳን ጋር የሚዋሰን በመሆኑ በርካታ የህገ ወጥ መሳሪያዎች ዝውውር በክልሉ በመታየት ...

Read More »

በዚምባቡዌ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን በምግብ እጦት እየተሰቃዩ መሆናቸውን በመግለጽ ከፍርድ ቤት አንወጣም ቢሉም በጸጥታ ሃይሎች ተገደው መውጣታቸው ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 13 ፥ 2008) በቅርቡ ወደ ዚምባብዌ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ 13 ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት በምግብ እጦት በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። የኢትዮጵያውያኑን ጉዳት ለመመልከት ተሰይሞ የነበረ ችሎትም ስደተኞቹ ያቀረቡት የረሃብ ቅሬታ ተከትሎ ጉዳዩን ሳይመለከት ለሌላ ጊዜ መቅጠሩን ክሮኒክል የተሰኘ እለታዊ ጋዜጣ አስነብቧል። ፍርድ ቤት ቀርበው የነበሩት ስደተኛ ኢትዮጵያውያንም የደረሰባቸውን የምግብ እጥረት ችግር በመግለጽ ...

Read More »

በድርቅ በተጎዱ ክልሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች 75% የሚሆኑት የውሃ አቅርቦት የሌላቸው መሆኑን ተመድ አስታወቀ

ኢሳት (መጋቢት 13 ፥ 2008) በድርቅ በተጎዱ ክልሎች ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 75 በመቶ የሚሆኑት የውሃ አቅርቦት የሌላቸው መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማክሰኞ አስታውቋል። አስር በመቶ ጭማሪን ያሳየው ይኸው የውሃ እጥረት ተማሪዎች በአግባቡ ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ አድርጎ እንደሚገኝም ድርጅቱ በድርቁ ዙሪያ በየሳምንቱ በሚያወጣው ሪፖርት ገልጿል። በስድስት ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ወደ አንድ ሚሊዮን አካባቢ ሰዎችም ካለባቸው የውሃ እጥረት የተነሳ ውሃን በተሽከርካሪ ለማቅረብ ...

Read More »

በአማራ ክልል ዳንሻ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በአጎራባች አካባቢዎች ተጠናክሮ መቀጠሉ ተነገረ

ኢሳት (መጋቢት 13 ፥ 2008) በሳምንቱ መገባደጃ እሁድ በአማራ ክልል በዳንሻ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ማክሰኞ ለሶስተኛ ቀን መቀጠሉንና በአጎራባች ያሉ ነዋሪዎች ከወልቃይት ተወላጆች ጎን በመሰልፍ ላይ መሆናቸው እማኞች ለኢሳት ገለጡ። በሶሮቃ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችና ነዋሪዎች “ጥያቄው የእኛም ነው” በማለት ከወልቃይት ተወላጆች ጎን በመቆም ተቃውሞን እንደተቀላቀሉት ማክሰኞ ከስፍራው የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በዳንሻና በሶሮቃ መንገዶች ተዘግተው መዋላቸውን የተናገሩት እማኞች በፀጥታ ሃይሎችና በወልቃይት ተወላጆች ...

Read More »