ኢሳት (መጋቢት 16 ፥ 2008) የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአክሰስ ሪል ስቴት መስራችና ባለቤት በግማሽ ሚሊዮን ብር ዋስትና እንዲፈቱ የሰጠው ውሳኔ ከፖሊስ በቀረበ ይግባኝ ምክንያት ታገደ። ፍርድ ቤቱ ፖሊስ ምርመራውን ለማጠናቀቅ የተሰጠው ጊዜ በቀና በህጉ መሰረት ነው በማለት የቀረበን ተቃውሞ ውድቅ በማድረግ አቶ ኤርሚያስ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲለቀቁ መወሰኑ ይታወሳል። ይሁንና፣ ፖሊስ የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማቅረቡንና ተፈቅዶ የነበረውም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በመሬት ቅርምት ወቅት አንድ ሄክታር በ20 ብር ሲሸጥ እንደነበረ ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 16 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ትችት ሲቀርብበት በቆየው የመሬት ቅርምት ፕሮግራም ከሁለት ሚሊዮን ሄክታር መሬት በላይ አንዱን ሄክታር በ20 ብር ሲሸጥ መቆየቱ ተገለጠ። የስዊዘርላንድ ሃገርን ያክል የቆዳ ስፋት ያለው መሬትን ለሽያጭ አቅርቦ የነበረው መንግስት ባለፉት አምስት አመታት ብቻ ከ204 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለባለሃብቶች ማስረከቡን ሮይተርስ የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ አርብ ዘግቧል። ለአለም አቀፍ ገበያ ቀርቦ ከነበረው 3.6 ሚሊዮን ...
Read More »በኢትዮጵያ አምስት ቢሊዮን ብር የሚፈጅ የኬሚካል ፋብሪካ ሊገነባ ነው
ኢሳት (መጋቢት 16 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በአይነቱ የመጀመሪያ ነው የተባለና አምስት ቢሊዮን ብር የሚፈጅ የኬሚካል ግንባታ ለማካሄድ በትግራይ መልሶ ማቋቋምና በአንድ የቻይና ኩባንያ አርብ ስምምነት ተፈረመ። በመቀሌ ከተማ አቅራቢያ ይገነባል የተባለውን ይህንኑ የፋብሪካ ስምምነት የትግራይ መልሶ ማቋቋም ድርጅት ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ አዜብ መስፍንና የቻይናው CEO ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ተወካይ መሆናቸውን ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል። ከ 250 ሚሊዮን ዶላር ይፈጃል ...
Read More »ወደ ደቡብ ምስራቃዊ ሱማሌ ግዛት ሲፈስ የነበረው የሸበሌ ወንዝ እንዲቆም ተደረገ
ኢሳት (መጋቢት 16 ፥ 2008) በሶማሌ ክልል ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ የክልሉ ባለስልጣናት ወደምስራቅ ደቡባዊ ሶማሊያ ግዛት የሚፈሰውን የሸበሌ ወንዝ ፍሰት እንዲቆም ማድረጋቸው ተገለጠ። የወንዙ ፍሰት እንዲቆም መደረግን በወንዙ ላይ ህይወታቸው የተመሰረተ በርካታ ሶማሊያውያን ህይወት አደጋ ላይ እንደሚጥል የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን አርብ ዘግበዋል። የሶማሌ ክልል አስተዳደር ሃላፊ የሆኑት አቶ አብዲ ሞሃመድ ኦመር የወንዙ ፍሰት እንዲቀር የተደረገው የመስኖና የግድብ ስራን ...
Read More »በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሀብ እጅግ አስፈሪ ደረጃ ላይ መድረሱን የዓይን ምስክሮች በተለይ ለኢሳት ገለጹ።
መጋቢት ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርቁ በተለየ መልኩ በከፋባቸው እንደ ሶማሌና አፋር ባሉ ክልሎች ሁኔታውን ተዘዋውረው የተመለከቱ የረድኤት ሰራተኞች ለኢሳት እንደተናገሩት ፤ በተጠቀሱት ክልሎች ባሉ የማገገሚያ ጣቢያዎች ከመክሳታቸው ብዛት ቆዳቸው አጥንታቸው ጋር የተጣበቀና ጭንቅላቶቻቸው ብቻ የቀሩ ህጻናት በሞት ቋፍ ላይ ሆነው እያጣጣሩ ይታያሉ። በህይወቴ በረሀብ ሳቢያ የዚህ አይነት ዘግናኝ ነገር ሲከሰት ዓይቼ አላውቅም የሚሉት አቶ መስፍን ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ተቃውሞ አካሄዱ
መጋቢት ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው በተለምዶ ጀርመን መስጅድ ውስጥ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። “የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ!” በሚል ምእመናኑ መፈክሮችን በማንገብ በግቢው ውስጥ ሰላማዊ ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል። ምእመናኑ ” የነቃ ህዝብን ያሸነፈ አፈና የለም! ሰላማዊ ያደረገን የአሚሮቻችን ቃል እንጂ የአምባገነን ጡጫ አይደለም! ሰላም ከነሳችሁን ተመሳሳይ ኑሮ እንድንኖር ታስገድዱናላችሁ! ትግላችን ይቀጥላል! ፍትሕን ቀበሯት! ...
Read More »የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን ለቀቁ።
መጋቢት ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በገዛ ፍዳቸው ስልጣናቸውን የለቀቁት አቶ ሀብቴ ፊቻላ በሁለት ወራት ልዩነት ውስጥ የፌዴራል ፍ/ቤቶችን ከለቀቁ ከፍተኛ ባለስልጣናት መካከል አራተኛው ሆነዋል። ባለፈው የካቲት ወር የመጀመሪያ ሳምንት የጤና እክል ገጥሞኛል በሚል በገዛ ፈቃዳቸው ከሀላፊነታቸው የለቀቁት የፌዴራል ጠ/ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት እና የህገመንግስት አጣሪ ጉባኤ ቁልፍ ሰው የነበሩት አቶ ተገኔ ጌታነህ ነበሩ። አቶ ተገኔን ተከትሎ የፌዴራል ...
Read More »በአዲስ አበባ ውሃ በፈረቃ ማደል ሊጀመር ነው
መጋቢት ፲፮ (አሥራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በፈረቃ ሊታደል መሆኑን የውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን አስታውቋል። ድርጅቱ በአየር መዛባት ምክንያት በለገዳዲና በድሬ ግድቦች ውስጥ ሲገባ የነበረው ውሃ መጠን በማነሱ በፈረቃ ለማደል መወሰኑን ገልጿል። የፈረቃ እደላው የካቲት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ይጀምራል። ኢሳት በከተማው ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የውሃ እጥረት ማጋጠሙንና በከተማዋ ነዋሪዎች እለታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ከፍተኛ ...
Read More »አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲለቀቁ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ወሰነ
ኢሳት (መጋቢት 15 ፥ 2015) የፌዴራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከሁለት ወር በፊት የገቡትን ቃል አልፈጸሙም ተብለው ለእስር የተዳረጉት የአክሰስ ሪል ስቴት መስራችና ባለቤት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የዋስትና መብታቸው ተጠብቆ ከእስር እንዲለቀቁ ሃሙስ ወሰነ። ፍርድ ቤቱ ተከሳሹን በግማሽ ሚሊዮን ብር ዋስትና ከእስር ቤት እንዲወጡ ቢወስንም ከሃገር እንዳይወጡ ግን እገዳ ማስቀመጡን ከሃገር በት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። በአቶ ኤርሚያስ ላይ ምርመራን እያካሄደ የሚገኘው ...
Read More »ኢትዮጵያ በአለማችን በከፋ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ከተጠቁ 20 አገሮች አንዷ መሆኗ ተገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 15 ፥ 2015) ኢትዮጵያን ጨምሮ 20 የአለማችን ሃገራት በከፋ የሳንባ ነቀርሳ (ቲቢ) በሽታ መፈረጃቸውን የአለም ጤና ድርጅት ሃሙስ አስታወቀ። በየአመቱ መጋቢት 15 የሚከበረውን የቲቢ (TB) ቀን አስመልክቶ ሪፖርትን ያወጣው የጤና ድርጅቱ እነዚሁ 20 አገራት በበሽታው መዛመት የተነሳ የጤና መሰረተ ልማታቸው ፈተና አጋጥሞት እንደሚገኝ ገልጿል። ባለፉት አስር አመታት በሃገሪቱ የበሽታውን መስፋፋት ለመቆጣጠር የተለያዩ ጥረቶች ቢያደርጉም አጥጋቢ ውጤት ሊገኝ አለመቻሉን ...
Read More »