.የኢሳት አማርኛ ዜና

ኦሮሚያ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በገፍ እየታሰሩ እንደሆነ ተገለጸ

ኢሳት (መጋቢት 21 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ በቅርቡ ተጨማሪ 3ሺ ሰዎች ከተለያዩ የክልሉ ከተሞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ረቡዕ ገለጠ። ባለፈው ሳምንት ከሃገር እንዳይወጡ የታገዱትና የኮንግረሱ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና የመንግስት ባለስልጣናት ለተፈጸመው ግድያና ወከባ በቅርቡ ይቅርታን ቢያቀርቡም እስራቱ ተባብሶ መቀጠሉን ለኢሳት በሰጡት ቃለ-ምልልስ አስታውቀዋል። ይኸው የእስር ዘመቻም በወለጋ፣ አምቦ፣ አርሲ፣ ምስራቅ ሃረርጌ ...

Read More »

የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የድረገጾች ጠለፋ ተፈጽሞብናል አለ

ኢሳት (መጋቢት 21 ፥ 2008) የረቀቁ የኢንተርኔት የስለላ ተግባሮችን እንደሚጠቀም የተለያዩ መረጃዎች ሲቀርቡበት የቆየው የኢትዮጵያ መንግስት በሌላ ሃገር በመንግስታዊ ድረ-ገጾች ላይ የጠለፋ (የሃኪንግ) ተግባር ተፈጽሞብኛል ሲል አስታወቀል። ይኸው ድርጊት በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ መፈጸም መጀመሩን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢንፎሪሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካዔል ለፓርላማ ባቀረቡት ሪፖርት ይፋ አድርገዋል። በሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ዙሪያ ሰሞኑን ለፓርላማ ሪፖርትን ያቀረቡት ዶ/ር ደብረጽዮን ...

Read More »

የህንድ ኩባንያ የኢትዮጵያን መብራት አገልግሎት ለማሻሻል የ50 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጄክት ተረከበ

ኢሳት (መጋቢት 21 ፥ 2008) አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች መፍትሄ ያልተገኘለትን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ጥራትና መቆራረጥ ለመቅረፍ አንድ የህንድ ኩባንያ የ50 ሚሊዮን ዶላር (የ1.2 ቢሊዮን ብር) ፕሮጄክት ተረከበ። ለተመሳሳይ ተግባር ከአንድ አመት በፊት የ16.7 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ፈርሞ የነበረው የህንዱ ፓወር ግሪድ ኮርፖሬሽን ለችግሩ መፍትሄን አላመጣም ተብሎ የሁለት አመት ኮንትራቱ ሳይረዝም ከሃገር መሰናበቱ ይታወሳል። በመጀመሪያው ዙር የስራ አፈጻጸም ደስተኛ ...

Read More »

በኢትዮጵያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል

መጋቢት ፳፩( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መረጃዎች እንደሚመለክቱት ከድርቅ እና ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በመቶዎች የሚቆጠሩ ትምህርት ቤቶች በመላ አገሪቱ በመዘጋታቸው በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ ሆነዋል፡፡ ከድርቅ ጋር በተያያዘ በርካታ ትምህርት ቤቶች ከተዘጉባቸው መካከል ሶማሊ፣ አፋር፣ ደቡብ እና አማራ ክልሎች ሲጠቀሱ፣ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ደግሞ አበዛኞቹ ትምህርት ቤቶች የተዘጉት በኦሮምያ ነው፡፡ በደቡብ በኮንሶና ሀመር ...

Read More »

ህገወጥ ሰደተኝነት እየጨመረ ቁጥጥሩ እየላላ መምጣቱን የጠረፍ ከተማ አመራሮች ተናገሩ

መጋቢት ፳፩( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በጠረፋማ ከተሞች በተደረገው ቃለመጠይቅ ከፍተኛ የወረዳ አመራሮች ለዘጋቢያችን በሰጧት አስተያየት ከላይ ጀምሮ ያለው የክትትል አግባብ መላላቱን ተናግረዋል፡፡ “ከፌዴራል መንግስት ጀምሮ ያለው የድጋፍ ስርዓት አሁን አለ ብሎ መውሰድ አይቻልም ፡፡” የሚሉት አመራር “ሃገሪቱ በበርካታ ችግሮች መወጠሯ ለህገወጥ የሰዎች ዝውውር ትኩረት እንዲነፈገው አድረጓል፡፡” በማለት ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችን ይከሳሉ፡፡ በህጋዊ መንገድ ...

Read More »

በልምምድ ላይ እያሉ ዘጠኝ ኢትዮጵያዊያን የማራቶን ሯጮች የመኪና አደጋ ደረሰባቸው

መጋቢት ፳፩( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሰሜናዊ አዲስ አበባ ሱሉልታ መውጪያ አቅራቢያ የማራቶን ልምምድ ሲያደርጉ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ድንገተኛ የሆነ ከባድ የመኪና አደጋ ደረሰባቸው። በአደጋው የ25 ዓመቱ ወጣት አትሌት አሻግሬ ግርማ ወደ ሕክምና ተቋማት ቢወሰድም ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም። ባለፈው ዓመት በህንድ ማራቶን አራተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው አትሌት ዳምጠው ታሪኩ በበኩሉ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት በግሩ ላይ ...

Read More »

የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚን ዋና ጽ/ቤት ለመገንባት አንድ የቻይና ኩባንያ የ 1.3 ቢሊዮን ብር ዋጋ ግምት አቀረበ

ኢሳት (መጋቢት 20 ፥ 2008) አንድ የቻይና ኮንስትራክሽን ኩባንያ የመለስ ዜናዊ የአመራር አካዳሚን ዋና ጽ/ቤት ለመገንባት የ 1.3 ቢሊዮን ብራ ዋጋ ግምት አቀረበ። የማዕከሉን ዋና ጽ/ቤት ለመገንባት ጨረታን ያወጣውና ማዕከሉን እያስተዳደረ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህንጻውን ሙሉ ወጪ እንደሚሸፍን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ከሶስት እስከ አራት ሄክታር በሚሆን መሬት ላይ ያርፋል የተባለው ይኸው የአካዳሚው ማዕከል በባለ ሰባትና 19 ...

Read More »

የአሜሪካ ልዑካን ወደ አዲስ አበባ ሊጓዝ ነው

ኢሳት (መጋቢት 20 ፥ 2008) ባለፈው አመት ሃምሌ ወር የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ወቅት ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ያደረጓቸውን ውይይቶች የሚከታተል ከፍተኛ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሃላፊ ወደ አዲስ አበባ እንደሚጓዙ ተገለጠ። ይኸው በአሜሪካው ረዳት የውጭ፣ የዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ሚኒስትሩ ቶም ማሊኖውስኪ የሚመራው የልዑካን ቡድን ማክሰኞ ወደ አዲስ አበባ እንደሚገባ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል። በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ...

Read More »

በየመን እርስ በእርስ ጦርነት መውጫ አጥተው የነበሩ 485 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው ሊመለሱ ነው

ኢሳት (መጋቢት 20 ፥ 2008) የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) በየመን ካለው ጦርነት መውጫን አጥተው የነበሩ 485 ስደተኛ ኢትዮጵያውያንንን መታደጉን ማክሰኞ ገለጠ። ከኢትዮጵያ ጦርነት እልባት ወደ አላገኘባት የመን የሚደረገው ስደት መባባስ ስጋት እንደፈጠረበት ያስታወቀው ድርጅቱ ለአደጋ ተጋልጠው መውጣት ከቻሉት መካከል 122ቱ ሴቶች እንዲሁም 101 ወጣቶችና አንድ ህጻን እንደሚገኙበት አመልክቷል። እነዚሁ ስተደኛ ኢትዮጵያውያን በጎረቤት ጅቡቲ በኩል አድርጎ በአውቶቡስ ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ ...

Read More »

መንግስት በዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ላይ ከፍተኛ ክትትል እያደረገባቸው ነው ተባለ

ኢሳት (መጋቢት 20 ፥ 2008) ከወራት በፊት ከእስር የተፈቱት የዞን ዘጠኝ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን አባላት ከእስር ከተፈቱ በኋላ ከሃገር እንዳይወጡና በእለት ከእለት እንቅስቃሴያቸው ላይ ከፈተኛ ቁጥጥር እየተደረገባቸው መሆኑን አስታወቁ። በቀድሞ ስራቸው ላይ መሰማራት እንዳልቻሉ የሚናገሩት አባላቱ ዳግም ወደ እስር ቤት ልንገባ እንችላለን የሚል ስጋትም አድሮባቸው እንደሚገኝ መግለጻቸውን ቪኦኤ እንግሊዝኛው ክፍል ዘግቧል። የተመሰረተባቸው የሽብርተኛ ክስ ተቋርጦ ከአምስት ወር በፊት ከእስር የተለቀቁት ጋዜጠኞቹና ...

Read More »