.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአምቦ ወህኒ ቤት አንድ ወጣት በደረሰበት አሰቃቂ በድብደባ ተገደለ

ኢሳት ( መጋቢት 29 ፥ 2008) አምቦ ወህኒ ቤት ውስጥ የታሰረ አንድ ወጣት በድብደባ መገደሉን ወላጅ እናቱ ለኢሳት ገለጹ። ላለፉት 10 አመታት በወህኒ ቤት ውስጥ የቆየው ወጣት ጌጡ በቀለ ቶሎሳ፣ ህይወቱ ያለፈው ከአምቦ ወህኒ ቤት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ እጅ አለበት በሚል በደረሰበት ድብደባ መሆኑም ተመልክቷል። በፖለቲካ ሳቢያ ከ10 አመት በፊት ወህኒ ቤት መግባቱ የተገለጸው ወጣት ጌቱ በቀለ፣ እዚያው እያለ በመጣበት ...

Read More »

በኢትዮጵያ የካንሰር በሽታ በየአመቱ 44ሺ ሰዎችን እንደሚገድል የጤና ባለሙያዎች ገለጹ

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2008) መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶች በአግባቡ አልተስፋፋባትም በምትባለው ኢትዮጵያ የካንሰር በሽታ በየአመቱ 44ሺ ሰዎችን እንደሚገድል የጤና ባለሙያዎች ሃሙስ ይፋ አደረጉ። ይኸው በአደጉ ሃገሮች ብቻ ይታወቅ የነበረው የካንሰር በሽታ ከሚገድላቸው ሰዎች በተጨማሪ ወደ 70ሺ የሚጠጉ ሰዎች በዚሁ በሽታ እንደሚያዙም የቱርኩ አናዱሉ የዜና አውታር ዘግቧል። የካንሰር በሽታ በኢትዮጵያ አሳሳቢ የጤና ችግር እየሆነ መምጣቱን የገለጹት የጤና ባለሙያዎች ይኸው በሽታ በሃገሪቱ ...

Read More »

ለኮ/ል አታክልቲ ገ/ሚካዔል ልጅ ማሳከሚያ ከብረታ ብረት ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን 3 ሚሊዮን ወጪ ተደረገ

ኢሳት (መጋቢት 29 ፥ 2008) የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለአንድ ባለስልጣን ልጅ ማሳከሚያ ሶስት ሚሊዮን ብር የህዝብ ገንዘብ ወጪ ማድረጉን ለኢሳት የደረሰው ሰነድ ያስረዳል። ኮሮፖሬሽኑ የወጣውን ገንዘብ በስሩ ያሉ ድርጅቶች በመዋጮ እንዲሸፍኑት መመሪያ ተላልፏል። በብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሰው ሃይል አስተዳደርና ዕቅድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በኮ/ል ፅጌ አለማየሁ ስምና ፊርማ ህዳር 8 ፥ 2005 የተጻፈው ደብዳቤ ለኮ/ል አታክልቲ ገ/ሚካዔል ልጅ ማሳከሚያ የወጣው ወጪ ...

Read More »

በአማራው ክልል ፕሬዚዳንት ላይ ያነጣጠረ ግምገማ እየተካሄደ ነው

መጋቢት ፳፱( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቅርቡ በአማራ ክልል ተነስተው የነበሩትንና እስካሁንም መቁዋጫ ያልተገኘላቸውን የቅማንትና የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄን ተከትሎ ለደረሰው ደም መፋሰስ የክልሉን ፕሬዚዳንት አቶ ገዱ አንዳጋቸውን ተጠያቂ በማድግ የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን በመሩዋሩዋጥ ላይ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል፡፡ የወልቃይት ጥያቄ የአቶ ገዱ የአመራር ችግር እንጅ የአማራ ህዝብ ጥያቄ አይደለም በሚል፣ ...

Read More »

የቤት ለቤት ፍተሻ የመርካቶ ነጋዴዎችን አበሳጭቶአል

መጋቢት ፳፱( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በፖሊስ ሀይል እየታገዘ መደብሮቻችንን መፈተሽ መጀመሩ ህገወጥ እርምጃ ነው በሚል የመርካቶ ነጋዴዎችተቃውመዋል። አንዳንድ ነጋዴዎች ለአዲስ አበባው ሪፖርተራችን እንደነገሩት ፖሊሶች በድንገት ሱቆቻችንን በመውረር ፍተሻ እናደርጋለን በሚል ለእያንዳንዱ እቃ በህጋዊ መንገድ የገባበትን ማስረጃ ካላቀረባችሁ ብለው እንደሚያዋክቡ፣ አንዳንዶች ማስረጃዎችን እስከሚያሰባስቡ እድል እንኩዋን ሳይሰጡዋቸው እቃዎቻቸውን ኮንትሮባንድ ናቸው ...

Read More »

በአበረታች መድሃኒት ምክንያት የኢትዮጵያ አትሌቶችና አትሌቲክስ ማኅበር ቅጣት ይጠብቃቸዋል

መጋቢት ፳፱( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ታሪክ ውስጥ ተደርጎ የማያውቅ ድርጊቶች በቅርቡ ከዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ማኅበርና ከመገናኛ ብዙሃን በኩል መደመጥ ተጀምርዋል። ውጤታማው የኢትዮጵያ የመሃከለኛና የረዥም ሩጫ ተወዳዳሪዎች አበረታች መድሃኒት መጠቀማቸውን የፀረ አደንዛዥ እጽ ተቆጣጣሪ ድርጅት በምህጻረ ቃሉ ዋዳ /WADA/ አስታውቋል። ዓለምአቀፉ አትሌቲክ ማኅበር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ማኅበር የሯጮችን የደም ምርመራ ናሙና ውጤት ካላቀረበ በኢትዮጵያ ላይ ...

Read More »

በዱባይ የታሰሩት ኢትዮጵያዊያን ሥጋ ላኪዎችን እስካሁን አልተለቀቁም

መጋቢት ፳፱( ሃያ ዘጠኝ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ በዱባይ በተካሄደው ዓለምአቀፍ የምግብ ኤግዚብሽን ላይ ለመካፈል በተጓዙበት የተበላሸ ሥጋን አቅርበዋል በሚል ውንጀላ በተባበሩት አረብ ኤሜሬት ፓሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉት የስድስቱን ኢትዮጵያዊያን ሥጋ ላኪዎችን ለማስለቀቅ እንዳልተቻለ ታውቋል። የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤትና የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እስረኞቹን ማስፈታት እንዳልቻሉ የተገለፀ ሲሆን የሥጋ ላኪዎች ማኅበር በበኩሉ ለተደጋጋሚ ጊዜያት ...

Read More »

በህገወጥ ንግድ ተሰማርታችኋል የተባሉ ነጋዴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008) በህገ-ወጥ ንግድ ተሰማርታችኋል የተባሉ 120 ነጋዴዎች በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ባለፉት 30 ቀናት ብቻ በቁጥጥር ስር የዋሉት እነዚሁ ነጋዴዎች ያለ-ደረሰኝ ግብይትን ሲፈጽሙ ቆየተዋል ሲል ረቡዕ አስታውቋል። ባለስልጣኑ 85 አምራቾች፣ አስመጪዎችና የጅምላ አከፋፋይ ድርጅቶች ላይ ድንገተኛ ዘመቻ ማካሄዱን አውስቶ ከ85ቱ የንግድ ድርጅቶች መካከል 77 የሚሆኑት ያለ-ደረሰኝ ግብይት ሲፈጽሙ መገኘታቸውን ይፋ ...

Read More »

ኢትዮ-ቴሌኮም ያልተቀረጡ ስልኮችን በአገልግሎት ላይ እንዳይውሉ የሚያደርግ ቁጥጥርን ተግባራዊ ሊያደርግ ነው

ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የስልክ አገልግሎትን በብቸኝነት እየሰጠ የሚገኘው ኢትዮ-ቴለኮም በተለያዩ መንገዶች ወደ ሃገሪቱ የገቡና ያልተቀረጡ ስልኮችን በአገልግሎት ላይ እንዳይውሉ የሚያደርግ ቁጥጥርን ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ። ኢኪዩፕመንት አይደንቲቲ ሬጂስተር የተሰኘ ቴክኖሎጂን አገልግሎት ላይ ለማዋል በዝግጅት ላይ የሚገኘው ድርጅቱ በሃገሪቱ ያሉ ሁሉ የእጅ ስልኮች ምዝገባ እንደሚያደርጉም ገልጿል። በምዝገባው ያልተካተቱና በስጦታና በተለያዩ መንገዶች ወደ ሃገር ውስጥ የገቡ ስልጎችም ተገቢው ምርመራ ...

Read More »

ግብፅ ለኢትዮጵያ ስደተኞች የምትሰጠው ድጋፍና ከለላ ፖለቲካዊ አይደለም አለች

ኢሳት (መጋቢት 28 ፥ 2008) የግብፅ መንግስት በሃገሪቱ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች እየሰጠ ያለው ድጋፍና ከለላ ፖለቲካዊ ትስስር የሌለው መሆኑን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጎረቤት ሃገራት ለኢትዮጵያ ስደተኞችን አሳልፈው መስጠት መጀመራቸውን ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ግብፅና ሌሎች ሃገራት በመግባት ላይ መሆናቸውን አል-ሞኒተር የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። ሃገሪቱ ለኢትዮጵያውን ስደተኞች እየሰጠች ያለችው ድጋፍም አለም አቀፍ ህጎችን መሰረት ያደረገ እንደሆነና ፖለቲካዊ ...

Read More »