ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ቦርድ ለኢሳት አለም-አቀፍ አዲስ ዳይሬክተር መሾሙን ይፋ አደረገ። የቀድሞውን የኢሳት አለም አቀፍ ዳይሬክተር አቶ ነዓምን ዘለቀ በክብርና በምስጋና የሸኘው የኢሳት ቦርድ ጋዜጠኛ አበበ ገላው የኢሳት አለም አቀፍ ዳይሬክተር እንደሆነ ከኤፕሪል 1 ፥ 2016 ጀምሮ መሾሙን አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት በካሊፎርኒያ ግዛት ሲልከን ቫሊ የሚገኘው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ከኢሳት አስተዳደር ቦርድ በተሰጠው ሹመት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአቶ አለማየሁ መኮንን ላይ እንዲመሰክሩ የሃሰት ምስክሮች እየተመለመሉ ነው ተባለ
ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) በጂንካ ከተማ እቶ አለማየሁ መኮንንን በሽብርተኛ ፈርጆ የሚመራው ቡድን እስካሁን የሄደበት መንገድ ህገ-ወጥና በማሰረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ በፈጠራ ውንጀላ የሃሰት ምስክሮችን ለማዘጋጀት እየተሯሯጠ መሆኑን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለኢሳት አድርሰዋል። ለዚሁ ውንጀላ ይረዳቸው ዘንድ እቶ አለማየሁ ከመያዛቸው በፊት ሃሙስ ዕለት ምሽት በከተማው ውስጥ ቦንብ መፈንዳቱን እንደመነሻ በስፋት እያስወራ መሆኑን ምንጮቹ አስታውሰው፣ በገንዘብና ጥቅማ-ጥቅሞች የሃሰት ምስክሮች እየተመለመሉ ያሉት ...
Read More »ከማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አሁንም ድረስ ቀጥሏል
ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ተቀስቅሶ የነበረው ተቃውሞ በመንግስት ባለስልጣናት ዘንድ እልባትን እንዳገኘ ቢገልጽም ተቃውሞ አሁንም ድረስ እልባት አለማግኘቱን ከሃገር ቤት ከተገኘ መረጃ ለመረዳት ተችሏል። ከተቃውሞው ጋር በተገናኘ ለእስር የተዳረጉ ሰዎች እንዲፈቱና በየከተሞቹ ያሉ የጸጥታ ሃይሎች ከአካባቢው እንዲወጡ የሚጠይቁ ተቃውሞዎች በምስራቅ ሃረርጌና በተለያዩ የክልል ከተሞች እየተካሄዱ መሆኑም ታውቋል። አራተኛ ወሩን ዘልቆ የከሚገኘው ከዚሁ ተቃውሞ ...
Read More »በሶማሊ ክልል 24 ወረዳዎች ለረሃብ ሊጋለጡ እንደተቃረቡ ተመድ ገለጸ
ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ በሶማሊ ክልል ብቻ ለረሃብ ሊጋለጡ የተቃረቡ ወረዳዎች ቁጥር 24 መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አርብ አስታወቀ። በዚሁ የድርቅ አደጋ ከቀያቸው የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥርም መጨመርን አሳይቶ እስከ ባለፈው ወር ድረስ በክልሉ ከ 147 ሺ በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው መሰደዳቸውን ድርጅቱ ይፋ አድርጓል። የሶማሊ ክልል በድርቅ ከተጠቁት ስድስት ክልሎች አንዱ ሲሆን፣ ...
Read More »በድርቅ የተመቱት የሰቆጣ አካባቢ ነዋሪዎች ቀያቸውን ጥለው እየሸሹ ነው
ኢሳት (መጋቢት 30 ፥ 2008) በሰቆጣ የተከሰተው ድርቅ እየተባባሰ በመምጣቱ ነዋሪዎች ቀዬአቸውን ጥለው በመሰደድ ላይ መሆናቸው ታወቀ። ከፊሉ ነዋሪ ወደ ባህር ዳርና መቀሌ ሲሰደድ፣ 400 የሚሆኑ ደግሞ ደብረ-ብርሃን መድረሳቸው ታውቋል። ረሃቡን ሸሽተው ምግብ ፍለጋ ደብረ-ብርሃን ከደረሱት የሰቆጣ ነዋሪዎች ውስጥ አንዱ ለኢሳት እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት በሰቆጣ የቀሩት የመንግስት ሰራተኞችና ዕድሚያቸው የገፉ አዛውንቶች ብቻ ናቸው። ነዋሪው በርሃብ ከደረሰበት ችግር ባሻገር የሚጠጣ ውሃ ...
Read More »ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችና ደህንነቶች በዋልድባ ቁጥጥር ሲያደርጉ መሰንበታቸው ታወቀ
መጋቢት ፴( ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የገዳሙ አባቶች እንደገለጹት መጋቢት 27 የተከበረውን የመድሃኒአለም በአል ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወታደሮችና ደህንነቶች በገዳሙ በመግባት ቁጥጥርና ክትትል ሲያደርጉ ሰንብተዋል፡፡ ሁሉም ደህንነቶች ትግርኛ ብቻ የሚናገሩ የህወሃት ደህንነቶች መሆናቸውን የሚናገሩት አባቶች፣ ከወልቃይትና ከጎንደር ወደ ገዳሙ የሄዱ ምእመናን ከቤተሚናስ መነኮሳት ጋር ምን አይነት ግንኙነት አላችሁ በማለት ሲያዋክቡዋቸው እና ሲከታሉዋቸው ሰንብተዋል፡፡ የወልቃይት ህዝብ ጥያቄ ያሰጋቸው ...
Read More »በአፋር መጪው ጊዜ እጅግ አስፈሪ ነው ተባለ
መጋቢት ፴( ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ20 ሚሊዮን ያላነሱ ዜጎችን ለረሃብ አደጋ ያጋለጠው ድርቅ፣ በአፋር ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍቶአል፡፡ እናቶች በየሳምንቱ በሞትና በህይወት መካከል ያሉ ህጻናትን ይዘው ረጅም ርቅት ተጉዘው ህክምና ለማግኘት ይጥራሉ፡፡ ረሃቡ የከፋ መሆኑንና አለማቀፉ ማህበረሰብ ባይደርስ ኖሮ ከዚህም በላይ ሊሆን እንደሚችል የአይ ቲ ቪ ኒውስ ጋዜጠኛ ቦታው ድረስ በመሄድ ዘግቦአል፡፡ በአንድ የህክምና ማእከል ውስጥ የሚሰራ ...
Read More »ወደ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ኤግዚቢሽን ለመካፈል ሄደው ከሀገር እንዳይወጡ የታገዱ ሰባት በስጋ ላኪነት የተሰማሩ ዜጎችን የኢትዮጵያ መንግስት ማስለቀቅ አልቻለም።
መጋቢት ፴( ሠላሳ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከየካቲት 13 እስከ 17/2008 አም በዱባይ ከተማ አንድ ኤግዚቢሽን ላይ ለመሳተፍ ወደስፍራው ካመራው የመንግስት ልኡካን መካከል በስጋ ላኪነት ስራ ውስጥ የነበሩ ሰባት ባለሀብቶች በሻርጂያ ከተማ ፖሊስ ተይዘው ክስ ሳይመሰረትባቸው ከታሰሩ በኋላ ፖስፖርታቸውን አስይዘው በዋስ ቢለቀቁም ከሀገር እንዳይወጡ ከታገዱ የአንድ ወር ተኩል ጊዜ አሳልፈዋል። ባለሀብቶቹ የታገዱበት ምክንያት ከስድስት ወራት በፊት ለአንድ የዱባይ ...
Read More »ከ300 በላይ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን የማበረታቻ መድሃኒት ምርመራ ሊያካሄድባቸው መሆኑ ተነገረ
ኢሳት ( መጋቢት 29 ፥ 2008) የኢትዮጵያ አትሌቶች በውድድር ወቅት የተከለከሉ ማበረታቻ መድሃኒቶች ተጠቅመዋል የሚለው መረጃ ይፋ መደረግን ተከትሎ ከ300 በላይ አትሌቶችን ምርመራ ሊያካሄድባቸው መሆኑ ተገለጠ። የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በበኩሉ ሃገሪቱ መጠነ ሰፊ የምርመራ ዘመቻን ካላካሄደች ከአለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድሮች ስትታገድ እንደምትችል ሃሙስ ማሳሰቡን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙህን ዘግበዋል። የአለም አቀፉ የጸረ-ማበረታቻ ኤጄንሲ በአሁኑ ወቅት በስድስት የኢትዮጵያ አትሌቶች ላይ ...
Read More »በ2016 በድርቅ እና በጎርፍ አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተመድ ገለጸ
ኢሳት ( መጋቢት 29 ፥ 2008) በተያዘው የፈረንጆች አመት (2016) ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በኢትዮጵያ ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጠ። ድርቁ እያደረሰ ካለው ጉዳት በተጨማሪ የጎርፍ አደጋም ለሰዎቹ መፈናቀል ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ድርጅቱ በወቅታዊው የኢትዮጵያ የድርቅ ሁኔታ ዙሪያ በወጣው ሪፖርት አመልክቷል። አሁን በሃገሪቱ ተከስቶ ካለው የድርቅ አደጋ አንጻርም በቂ የህክምና አገልግሎቶች ተሟልተው አለመገኘታቸውን የገለጸው ...
Read More »