ሚያዚያ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ በፌደራል ፖሊስ እና በከተማው ልዩ ፖሊስ ከፍተኛ ጥበቃ በሚካሄደው የቤት ማፍረስ ዘመቻ፣ በርካታ ነዋሪዎች ለችግር መዳረጋቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቶአል፡፡ ከሚያዚያ 4 ቀን 2008 ዓም ጀምሮ በቀበሌ 02 ልዩ ስሙ ሳቢያን እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በሚካሄደው የቤት ፈረሳ ፣ እናቶች ፣ ኀጻናትና አሮጊቶች ሜዳ ላይ ወድቀዋል፡፡ ቤታቸው የሚፈርስባቸው ሰዎች ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ፓርላማው ያጸደቀው የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማቐቐሚያ አዋጅ ክስ የማንሳት የመጨረሻ ስልጣኑን ለጠ/ ሚኒስትሩ መስጠቱ እያነጋገረ ነው።
ሚያዚያ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠ/አቃቤ ህግ ሚኒስቴር መ/ቤት የተሙዋላ ተቁዋማዊ ነጻነት እንደሚኖረው በአዋጁ መግቢያ ላይ የተጠቀሰ ቢሆንም ክስ ማንሳትን በተመለከተ የጠ/ሚኒስትሩ ፈቃድ እንዲጠየቅ መደንገጉ፣ የተቁዋሙን ነጻነት ከወዲሁ ጥያቄ ላይ ጥሎታል። በአዋጁ አንቀጽ 6 ንኡስ አንቀጽ ሰ ላይ እንደተመለከተው ጠቅላይ አቃቢ ህግ “የፌዴራል መንግስትን በመወከል የወንጀል ጉዳዮች ክስ ይመሰርታል፣ ይከራከራል፣ ለህዝብ ጥቅም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ...
Read More »በዘላላም ወርቃገኘሁ መዝገብ ከተከሰሱት መካከል ሁለቱ በነጻ ሲሰናበቱ ሌሎች ጥፋተኞች ተባሉ
ሚያዚያ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በመዝገብ ቁጥር 166/07 በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው ጉዳያቸው በ19ኛው ችሎት እየታየ ከሚገኙት መካከል አቶ ባህሩ ደጉናና ዮናታን ወልዴ በነጻ ሲሰናቱ ቀሪዎቹ ጥፋተኞች ተብለዋል፡፡ በዚህ መዝገብ ውስጥ ስማቸው ሰፍሮ የሚገኘው ተከሳሾች ዘላለም ወርቃገኘሁ፣ ሃብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ አብርሃ ደስታ ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዮናታን ወልዴ፣ አብርሃም ሰሎሞን፣ ሰሎሞን ግርማ፣ ባህሩ ዳጉ እና ተስፋዬ ብርሃኑ ናቸው፡፡ ...
Read More »አርባ ስድስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በማላዊ ተያዙ
ሚያዚያ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በትናትናው እለት ድንበር አቋርጠው ካለ ሕጋዊ ቪዛ ወደ ማላዊ የገቡ አርባ ስድስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዙን የአገሪቱ ፓሊስ አስታወቀ። በሚዚምቢ አውራጃ ኢኳንዳ በሚባል አካባቢ በትምባሆ እርሻ ውስጥ ተደብቀው ባሉበት በአካባቢው ነዋሪዎች ጥቆማ ስደተኞቹ መያዛቸውንና በአሁኑ ወቅትም በሙዙዙ እስር ቤት ውስጥ እንደሚገኙ የፓሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ማርቲን ቡማናሊ ገልፀዋል። በቁጥጥር ስር የዋሉትን ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ...
Read More »በአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት የታሰሩ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን በግዳጅ ወደኢትዮጵያ ሊመለሱ ነው ተባለ
ኢሳት (ሚያዚያ 6 ፥ 2008) የተለያዩ አገራትን አቋርጠው በስደት ወደ አሜሪካ የገቡትና ፍሎሪዳ ታስረው የሚገኙ 11 ኢትዮጵያውያንን በግዳጅ ወደ አገር ቤት ለመመለስ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተገለጸ። በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኗል፣ ግለሰቦቹም ወደ ኢትዮጵያ ቢመለሱ ምንም አይሆኑም በሚል የአሜሪካ መንግስትን ያታለለው የኢትዮጵያ መንግስት፣ የታሳሪዎችን ዶክመንትም በራሱ ሰዎች እጅ እንዳስገባ ታውቋል። በዚሁ በፍሎሪዳ ክፍለ ግዛት ታስረው የሚገኙ 2 ኢትዮጵያውያን በቅርቡ ወደከፋ እስርቤት ...
Read More »የፍትህ ሚኒስቴርን ህልውና እንዲያከትም የሚያደርገው ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 6 ፥ 2008) የፍትህ ሚኒስቴርን ህልውና እንዲያከትም የሚያደርገውን ከበርካታ የህግ ባለሙያዎች ዘንድ ትችት ሲቀርበት የቆየው የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ረቂቅ አዋጅ ሃሙስ በፓርላማ ጸደቀ። የአዋጁ መጽደቅ የፍትህ ሚኒስቴርን እንዲፈርስ የሚያደርግ ሲሆን የህግ ባለሙያዎች ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለብቻቸው ተቋቋሞ የፍትህ ሚኒስቴር እንዲቀጥል ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል። ሃሙስ ህግ ሆኖ የፀደቀው የፌዴራል ጠቅላ አቃቤ ህግ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን የበርካታ የፍትህ ...
Read More »በኢትዮጵያ የብሄር ጥያቄ የግጭት ምንጭ ሆኖ መቀጠሉ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 6 ፥ 2008) በአፍሪካ ሃገራት የብሄረሰብ ጥያቄ የቅራኔና የግጭት ምክንያት መሆኑ እያበቃ ቢመጣም፣ በኢትዮጵያ ግን ችግሩ መቀጠሉ ተገለጸ። ከየትኛውም የአፍሪካ ሃገር ምናልባትም በአለም ላይ ጭምር የብሄረሰብ ጥያቄን መሰረት ያደረጉ የመገንጠል እንቅስቃሴዎች እየተካሄደ የሚገኙት በኢትዮጵያ ብቻ መሆኑን የአፍሪካ የስትራቴጂና ጸጥታ ተቋም ዋና ስራ-አስፈጻሚ ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ገልጹ። አፍሪካ ኢንቲትዩት ፎር ስትራቴጂክ ኤንድ ሴኩሪቲ ስተዲስ የሚባለውንና በአፍሪካ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ...
Read More »የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያቤት በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብአዊ መብት ጥሰት አለመሻሻሉን ገለጸ
ሚያዚያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ2015ትን የአለም የሰብአዊ መብት አያያዝን የሚተነትነው ሪፖርት በኢትዮጵያ የሚታየው አፈናና ዜጎችን በእስር ቤት ማሰቃየት መቀጠሉን ይተነትናል፡፡ የአሜሪካ መንግስት በያመቱ በሚያወጣው የሰብአዊ መብት አያያዝ ሪፖርት የኢትዮጵያ የደህንነት ሰራተኞች ተቃዋዎችን ፣ ደጋፊዎቻውንና ጋዜጠኞችን እንደሚያሳድዱ፣ እንደሚያስሩ፣ በእስር ቤት ውስጥ አሰቃቂ ድደባ እንደሚፈጽሙ፣ እንዲሁም በህግ ስም ፖለቲካዊ ክስ እንደሚመሰር ዘርዝሮአል፡፡ ያለ ህግ እንደፈለጉ መግደል፣ ማሰር፣ ለፍርድ ...
Read More »እነ አቶ ዓለማዬሁ መኮንን በድጋሜ ተቀጠሩ
ሚያዚያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ በሽብርተኝነት የፈጠራ ውንጀላ ታስረው በሌሊት ወደ አዋሳ የተወሰዱትና ከመጋቢት 20፣ 2008 ዓም ጀምሮ በአዋሳ ፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ታስረው የሚገኙት የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ጽ/ቤት ኃላፊ መምህር ዓለማዬሁ መኮንን ፣ የኦህዲኅ አባል አቶ አብርሃም ብዙነህና የቀድሞ አንድነት የዞኑ ተጠሪ የነበሩት አቶ ስለሺ ጌታቸው ፖሊስ የጠየቀባቸውን የ14 ...
Read More »85 በመቶ የሚሆነው አርሶ አደር ባልተማረበት ሁኔታ የመንግስትን የልማት እቅድ ማሳካት አይቻልም ተባለ
ሚያዚያ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ሁለተኛውን የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ከያዛቸው እቅዶች መካከል የተጠናከረ የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም አንዱ ቢሆንም፣ ባለሙያዎች ግን በእቅዱ አተገባበር ላይ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል፡፡ ሰሞኑን በክልል ደረጃ በተደረገው የባለሙያዎች ውይይት እንደተነገረው የ2008 ዓም የጎልማሶች ትምህርት እየተቀዛቀዘ ሄዶአል፡፡ የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም የልማቱ ቁልፍ መሳሪያ ነው ብሎ የሚያምን አመራር አለመገኘቱን ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡ በእድገትና ትራንስፎርሜሸን ...
Read More »