ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2008 መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ ህብረት በንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃትን የፈጸሙ አካላት ለፍርድ እንዲቀርቡ ሰኞ ጥሪን አቅርቧል። የግድያ ድርጊቱን ያወገዘው ህብረቱ የኢትዮጵያና የጎረቤት ደቡብ ሱዳን መንግስታት ያላቸውን ዘርፈ-ብዙ ስምምነት በመጠቀም ጥቃት የፈጸሙ አካላትን ለፍርድ እንዲቀርቡ አሳስቧል። በዚሁ ጥቃት ታፍነው የተወሰዱ ኢትዮጵያውያንም በአስቸኳይ እንዲለቀቁ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ባወጣው መግለጫው የጠየቀ ሲሆን፣ መቀመጫቸውን በዚህ በአሜሪካና የተለያዩ ሃገራት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በጋምቤላ በደረሰው ጭፍጨፋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ሲሆን መከላከያም እየየተቸ ነው
ሚያዚያ ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው አርብ ከደቡብ ሱዳን የተነሱ ታጣቂዎች ከ35 እስከ 40 ኪሜ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀው በመግባት በላሬ፣ ጃካዋ ወረዳዎች አካባቢ በሚኖሩ የኑዌር ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ የሚባል ግድያ በመፈጸም እስካሁን ባለው ቆጠራ 208 ሰዎች የተገደሉ፣ሲሆን ከእነዚህ መካከል 50 የሚሆኑት ህጻናት ናቸው፡፡ የኢሳት የጋምቤላ ታማኝ ምንጮች እንደገለጹት አስከሬን የመሰብሰቡ ስራ በተለያዩ ወረዳዎች እየተካደ ሲሆን፣ ...
Read More »የኦህዴድ ካድሬዎች የህዝቡን አመጽ ተቆጣጥረነዋል በሚል ስሜት ጥይት በመተኮስ ደስታቸው ሲገልጹ ዋሉ
ሚያዚያ ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ በሃይል መቆጣጠራቸውን የሚናገሩት የኦህዴድ ኢህአዴግ ታማኝ ካድሬዎች፣ ከትናንት ወዲያ ሚያዚያ 8 ቀን 2008 ዓም በቦረና ገላና ወረዳ ቶሬ ወረዳ የ26ኛውን የኦህዴድ በአል እናከብራለን በሚል ሰበብ፣ ከጡዋቱ 3 ሰአት ተኩል እስከ ቀኑ 11 ሰአት ተኩል በአየር ላይ ጥይት እየተኮሱ ደስታቸውን ሲገልጹ፣ በተዘዋዋሪም ህዝቡን ሲያሸብሩ ውለዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት አመጸኞችን ...
Read More »ከስድስት ሚሊዮን በላይ የኢትዮጵያ ሕጻናት የምግብ እጥረትና ንጹሕ የመጠጥ ውሃ ማግኘት እንደማይችሉና አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ዩኒሴፍ አስታወቀ።
ሚያዚያ ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የተከሰተው አስከፊ ርሃብ የዜጎችን ሕይወት አስጊ ሁኔታ ውስጥ ያስገባ ሲሆን በተለይ ሕጻናት ቀዳሚ የችግሩ ገፈት ቀማሽ መሆናቸውን ድርጅቱ ተገልጿል። በሃምሳ ዓመታት ውስጥ ተከስቶ የማያውቅ አደገኛ ችጋር በኢትዮጵያ ያንዣበበ ሲሆን ጉዳተኞችን ለመታደግ ከስድስት መቶ ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ አፋጣኝ እርዳታ ከለገሽ አገሮች ይጠበቃል። ዩኒሴፍ ሕጻናት በውሃ ጥምና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በፈጠሩባቸው የጤና ...
Read More »አለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በድርቅ ለተጎዱ ኢትዮጵያውያን ዕርዳታ ሰጠ
ኢሳት (ሚያዚያ 7 ፥ 2008) አለም-አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) በድርቅ ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን የሚሆን እርዳታና ቁሳቁስ እያቅረበ መሆኑን አስታወቀ። የአለም-አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በቅርቡ 442 የመጠለያ ፕላስቲክ፣ የወባ መከላከያ አጎበር፣ ፍራሽ፣ ብርድ ልብስና፣ ለቤት አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ቁሳቁሶች በአፋር ክልል በዱብቲ፣ ሚሌና፣ አሳይታ ወረዳዎች ለሚኖሩ ወገኖች ማቅረቡን አስታውቋል። በሚሌ 87, በዱብቲ 305 እና በአሳይታ 50 በድርቅ ምክንያት ...
Read More »በሰሜን ጎንደር የህወሃት ታጣቂዎች ነዋሪዎችን እየገደሉና እያሳደዱ ነው ተባለ
ኢሳት (ሚያዚያ 7 ፥ 2008) በሰሜን ጎንደር አርማጭሆ ውስጥ የህወሃት ታጣቂዎች በአካባቢው የሚኖሩ ገበሬዎችን እየገደሉ፣ እያሳደዱና፣ ዝርፊያ እየፈጸሙባቸው እንደሆነ ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አመለከቱ። ከሶስት ቀን በፊት ማለትም ሚያዚያ 3 ፥ 2008 ላይ አርማጭሆ ኩርቢት በተባለ ቦታ ተሰማርተው የነበሩ የህወሃት ታጣቂዎች አንድ ገበሬ ገድለው ንብረታቸውን እንደዘረፏቸው የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል። በአካባቢው ተሰማርተው የሚገኙ የህወሃት ታጣቂዎች ተቃዋሚዎችን በተለይም አርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት ናቸው ...
Read More »የደህንነት ሃላፊ የነበሩት ወልደስላሴ ወልደሚካዔል በሰባት ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ
ኢሳት (ሚያዚያ 7 ፥ 2008) ከአንድ አመት በፊት ስልጣናቸውን ተጠቅመው ሙስና ፈጽመዋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የሃገር ውስጥ የደህንነት ሃላፊ በሰባት ክሶች ጥፋተኛ ተባሉ። የደህንነት ሃላፊ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካዔል በስልጣን ላይ በነበሩ ጊዜ የተለያዩ ሙስናዎችን ፈጽመዋል ተብለው 12 ክሶች ተመስርቶባቸው እንደነበር ይታወሳል። የተከሳሹን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አርብ በሰጠው ውሳኔ አቶ ወልደስላሴን በሰባት ክሶች ጥፋተኛ ...
Read More »በድርቅ የተጎዱ ኢትዮጵያውያን በቀን አድ ጊዜ ብቻ እንደሚመገቡ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 7 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በድርቅ ከተጎዱ 10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መካከል 70 በመቶ የሚሆኑ በቀን አንድ ጊዜ ብቻ በመመገብ የእርዳታ አቅርቦትን እየተጠባበቁ እንደሚገኝ የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) አርብ ይፋ አደረገ። ከእነዚሁ ተረጂዎች መካከልም 80 በመቶ የሚሆኑት በአለም ጤና ድርጅት የተቀመጠን የእለት የምግብ ፍላጎት እያገኙ እንዳልሆነ ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል። በቀጣዮቹ ሰባት ወራቶች ተጨማሪ 425 ዶላር እንደሚፈልግ የገለጸው የአለም ...
Read More »በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰ
ኢሳት (ሚያዚያ 7 ፥ 2008) ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገነው የአምቦ ከተማ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከውሃ እጥረት ጋር በተገናኘ ያቀረቡትን ተቃውሞ ተከትሎ በአምቦ ዩኒቨርስቲ አዲስ ግጭት ተቀሰቀሰ። በተማሪዎች መቅረብ የጀመረውን ተቃውሞ ለመቆጣጠር የጸጥታ ሃይሎች በተማሪዎቹ ላይ ድብደባ መፈጸማቸውንና በዩኒቨርስቲው የመማር ማስተማር ሂደቱም ተስተጓጉሎ እንደሚገኝ እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። በከተማዋ ለበርካታ ጊዜያት የተከሰተውን የውሃ እጥረት ተከትሎ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ለተማሪዎች የምግብ አገልግልሎት ለማቅረብ ...
Read More »በኦሮምያ ዜጎች መገደላቸውን አላቆሙም
ሚያዚያ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ ዘመናዊ የመገናኛ ዘዴ የሆኑትን ቫይበር እና ዋት ስ አፕ የመሳሰሉትን በመዝጋት በኦሮምያ ክልል የሚፈጸሙት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ይፋ እንዳይሆኑ እያደረገ ነው በሚል ትችት እየቀረበበት በሚገኝበት በዚህ ጊዜ፣በክልሉ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብት ጥሰት መቀጠሉን ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል፡፡ ከትናንት በስቲያ በጉጂ ዞን አዶ ሻኪሶ ወረዳ ሙጋድ ቀበሌ ውስጥ የዩኒቨርስቲ ትምህርቱን አጠናቆ ወላጆቹ ቤት ...
Read More »