ሚያዚያ ፲፩(አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብ፣ ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓም በጋምቤላ በከፍተኛ ሁኔታ የተጣቁ ወታደሮች በኑዌር ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸሙት ጥቃት፣ መንግስት እንኳን ባመነው፣ 208 ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ100 በላይ ቆስለዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ተወስደዋል፣ ከ2 ሺ ያላነሱ የቀንድ ከብቶችም ተወስደዋል።የአካባቢው አስተማማኝ ምንጮች እንደሚሉት ዋናው ጥቃት በተፈጸመበት በጅካዎ እና በላሬ መስመር ብቻ እስከዛሬ ቀን ድረስ የ230 ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በሃረሪ ክልል ሃብሊና ኦህዴድ እየተወዛገቡ ነው
ሚያዚያ ፲፩(አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ የኢሳት ወኪል እንደገለጸው፣በሃረር ከተማ የሸንኮር ወረዳ አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ አፈንዲ ሰሎሞን በጸረ-ሙስና ኮሚሽን አማካኝነት በከፍተኛ ሙስና ተወንጅልው እስር ቤት መግባታቸውን ተከትሎ፣ የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ ( ሃብሊ) እና የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲ ድርጅት ( ኦህዴድ) እየተወዛገቡ ነው። አቶ አፈንዲ የሃብሊ አባል ሲሆኑ፣ ኦህዴዶች ሆን ብለውአስገምግመው እንዲታሰር አስደርገውታል በማለት ሃብሊዎች የኦህዴድ መሪዎችን እየወነጀሉ ነው። ...
Read More »ዝዋይ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የዝዋይ ሃይቅ በደረሰበት የኬሚካል ብክለት ሳቢያ አደጋ ውስጥ ነው ተባለ
ሚያዚያ ፲፩(አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአካባቢው የሚገኙ የአበባ እርሻዎችና ፋብሪካዎች ወደ ሃይቁ በሚደፉት መርዛማ ኬሚካሎች ምክንያት የሃይቁ የአሳ ሃብት እየተመናመኑ መጥተዋል። በያዝነው ዓመት ብቻ ሃይቁ በአሁኑ ወቅት አንድ ሜትር ወደ ታች ወርዷል።የችግሩ አስከፊነት እያሳሰባቸውና እየተባባሰ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል። በአካባቢው ካሉ ገሊላ፣ ደብረሲና፣ደብረፂዮን፣ጠደቻና ፉንድሮ ደሴቶች ነዋሪዎች በተጨማሪ ሌሎችም በአሳ ማምረት ስራ ላይ መሰማራታቸው ከኬሚካሉ ቀጥሎ ሃይቁ ላይ ...
Read More »የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተቃውሞ ገጠማቸው
ሚያዚያ ፲፩(አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ውይይት ላይ ለመሳተፍ በድንገት ስዊድን የተገኙት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ መረጃው ደርሶአቸው በፍጥነት በተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ገጥሞአቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ፣ ደ/ር ቴዎድሮስን፣ ሌባ፣ ገዳይ በማለት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ወደ ስዊድን እንደሚመጡ አስቀድሞ ሳይነገር በመገኘታቸው ተቃውሞ ለማዘጋጀት አለመቻሉን የሚናገሩት ኢትዮጵያውያን፣ ከያሉበት በስልክ ተደዋውለው በመጠራራት፣ ተቃውሞአቸውን መግለጻቸውን ለኢሳት ተናግረዋል። ዶ/ር አድሃኖም በከፍተኛ የጸጥታ ሰራተኞች ታጅበው ...
Read More »በቦስተን ማራቶን ኢትዮጵያዊያን ሯጮች ድል ቀናቸው
ሚያዚያ ፲፩(አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በትናንትናው እለት የቦስተን ታሪካዊ የማራቶን ሩጫ ውድድር ላይ በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያዊያውን ሯጮች አመርቂ ድል አስመዘገቡ። በወንዶች የማራቶን ሩጫ ኢትዮጵያዊው ለሚ ብርሃኑ ኃይሌ በቀዳሚነት ሲገባ ርቀቱን ለመጨረስ 2:12:45 ሰከንድ ፈጅቶበታል። ለሚን በመከተል ኢትዮጵያዊው ያለፈው ዓመት ባለድል ሌሊሳ ዴሲሳ 2:13:32 በሆነ ሰዓት በ47 ሰከንድ ተቀድሞ ሁለተኛ ሲወጣ ሌላው የአገሩ ልጅ የማነ አድሃን ፀጋዬ ...
Read More »በረሃብ ለተጎዱ ኢትዮጵያውያን የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በሜሪላንድ ሲልቨር ስፕሪንግ ተካሄደ
ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2008) በግሎባል አልያንስ፣ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ እንዲሁም በዲሲ ግብረ ሃይል አማካኝነት በጋራ የተዘጋጀውና በኢትዮጵያ ውስጥ በረሃብ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ። እሁድ ሚያዚያ 9 ቀን 2008 ዓም በሜሪላንድ ከተማ በሚገኘው ሸራተን ሆቴል የተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም “ወገን መታደግ ቀን” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን በግዛቱ እና በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል። የገቢ ...
Read More »በሚኒሶታ ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ማጠናከሪያ የሚሆን ከ64ሺ ዶላር በላይ መገኘቱ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2008) ነዋሪነታቸው በዚህ በአሜሪካ ሚኒያፖሊስ ግዛት ሚኒሶታ ከተማና አካባቢዋ የሆኑ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ግንቦት ሰባትን ለመደገፍ በሳምንቱ መገባደጃ እሁድ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄዱ። የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች የተለያዩ ሃይማኖት ተወካዮች በተገኙበት በዚሁ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ከ64ሺህ ዶላር በላይ መገኘቱንም ፓርቲው ለኢሳት በላከው መግለጫ አመልክቷል። በዚሁ የሚኒሶታው ዝግጅት በቅርቡ የአርበኞች ግንቦት ሰባት የተቀላቀለችው ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ፣ የኢትዮጵያ አየር ሃይል አባል ...
Read More »በሜዲትራኒያን ባህር ከሰጠሙት ስደተኞች አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2008) እሁድ ሚያዚያ 9 ፥ 2008 ዓም ከግብፅ ተነስተው ወደ ጣልያን ሲጓዝ ከነበሩትና በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ ከሰጠሙት 400 ስደተኞች መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ተገለጸ። ህይወታቸውን ያጡት ወጣቶች ከሃገራቸው የተሰደዱት ምክንያትም ከዚህ አመት ከህዳር ወር ጀምሮ እየተካሄደ ባለው የኦሮሚያ ተቃውሞ የተነሳ መንግስት የሚወስደውን የሃይል እርምጃ ሸሽተው መሆኑን የሟች ቤተሰቦች ለኢሳት ገለጹ። እሁድ እለት የሶማልያ መገናኛ ብዙሃን እና ...
Read More »ሪክ ማቻር ወደደቡብ ሱዳን ጁባ ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ ተራዘመ
ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2008) መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ አድርገው የነበሩት የደቡብ ሱዳን አማጺ ቡድን መሪ ሪክ ማቻር በጋምቤላ ክልል በኩል አድርገው ወደ ደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ ልያደርጉት የነበረው ጉዞ ተራዘመ። የልተጠበቀ ነው የተባለው የአማጺ ቡድኑ መሪ መዘግየት በጋምቤላ ሊያጓጉዝ የነበረው አውሮፕላን የጉዞ ማስተካከያ ማድረጉን ጁባ አውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያ ማቻርን በመጠባበቅ ላይ ለነበሩት ጋዜጠኞች አስታውቀዋል። ላለፉት አንድ አመት ያህል መቀመጫቸውን በአዲስ ...
Read More »የጋምቤላው ጭፍጨፋን አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዘገቡ
ኢሳት (ሚያዚያ 10 ፥ 2008) አርብ እና ቅዳሚየ የተፈጸመውን የጋምቤላውን ጭፍጨፋ አለም አቀፍ ብዙሃን እየዘገቡ ነው። ኒው ዮርክ ታይምስ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ እንደዘገበው፣ ባለፈው አርብና ቅዳሜ ከ80 በላይ ቁስለኞች በጋምቤላ ሆስፒታል መድረሳቸውንና፣ አብዛኞቹ ጉዳተኞች በሰውነታቸው ውስጥ ጥይት እንዳለባቸው ዘግቧል። ሆስፒታሉም ከአቅሙ በላይ በቁስለኞች ስለተጥለቀለቀ፣ አብዛኞቹ ተጎጂዎች በሆስፒታሉ በረንዳ ላይ ተኝተው እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል ሲል ጋዜጣው ለንባብ አብቅቷል። ክላሺንኮብ መሳሪያ ...
Read More »