ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2008) በድርቅ በተጎዱ ሶስት ክልሎች በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ በተቀሰቀሰ የአጣዳፊ ተቅማጥ ወረርሽን በትንሹ 14 ሰዎች ሞተው ከ1ሺ የሚበልጡ ደግሞ በበሽታው መያዛቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። ይኸው በኦሮሚያ፣ የደቡብ እንዲሁም የሶማሊ ክልሎች የተቀሰቀሰው ወረርሽኝ በ15 ወረዳዎች ውስጥ ተዛምቶ የሚገኝ ሲሆን በሽታው ወደ አጎራባች ክልሎች ይዛመታል ተብሎም ተሰግቷል። እስከሳምንቱ መገባደጃ በደረሰው የበሽታው ወረርሽኝ በትንሹ 14 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኬንያ በስደት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በኢህአዴግ የደህንነት ሃይሎች ወከባ እየደረሰባቸው ነው
ኢሳት (ሚያዚያ 12 ፥ 2008) ከኢህአዴግ መንግስት ሸሽተው በኬንያ በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የኢትዮጵያ መንግስት ባሰማራቸው የደህንነት ሰዎች እንደሚዋከቡ ተገለጸ። በኬንያ የሚታተመው ኦኬ አፍሪካ የተባለው ጋዜጣ እንደዘገበው በኬንያ የሚኖሩ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ገንዘባቸውና ንብረታቸውን በኢህአዴግ የደህንነት ሃይሎች ከመዘረፋቸው በላይ፣ የማስፈራራት ድርጊትም ይፈጸምባቸዋል በማለት አትቷል። ታሪኩ ደበላ የሚባል አንድ በኬንያ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ስደተኛን ዋቢ አድርጎ የዘገበው ጋዜጣው፣ በናይሮቢ ከተማ ኢስትሌይ በሚባል አካባቢ ...
Read More »በጋምቤላ የተጨፈጨፉት ዜጎች ጉዳይ ኢትዮጵያውያንን ማነጋገሩን ቀጥሎአል
ሚያዚያ ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓም በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች የተገደሉት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ የአለምን ትኩረት በሳበት በዚህ ወቅት፣ የደቡብ ሱዳን መንግስት ምንም አይነት መግለጫ አለማውጣቱ ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለጥቃቱ አፋጣኝ መልስ አለመስጠቱ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከባድ የሆነውን አገራዊ ጉዳይ ትተው ወሳኝ ላልሆነ ስብሰባ ስዊድን መገኘታቸው ኢትዮጵያውያንን እያነጋገረ ነው። ...
Read More »በሃረር ለሚደረገው የብሄረሰቦች በአል 500 ሚሊዮን ብር በጀት ተያዘ
ሚያዚያ ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ ምንጮች እንደገለጹት ህዳር 29 ለሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ግማሽ ቢሊዮን ብር የተመደበ ሲሆን፣ ገንዘቡም ከሃረረ ስታዲየም እስከ አመሬሳ የሚደረሰውን 3.3 ኪሜ ባለሁለት መስመር መገድ ለማሰራት እንዲሁም፣ ከውጭ ለሚመጡ ዲያስፖራ እንግዶች ማረፊያ 600 ባለ አንድ ፎቅ ቤቶችን ለመገንባት እና ከተማዋን ለማጽዳት ይውላል ተብሎአል። ለመንገድና ለቤቶች መስሪያ በሚል በሃኪም ወረዳ የሚገኙ 250 ነዋሪዎችና ...
Read More »በሸዋሮቢት ከተማ ከፍተኛ የሆነ የጎርፍ አደጋ ደረሰ
ሚያዚያ ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋሮቢት ከተማና አካባቢው ባሉ አጎራባች ቀበሌዎች ላይ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ሳቢያ ነዋሪዎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቀሉ። ጎርፉ መጠነሰፊ አካላዊና ቁሳዊ ጉዳትቶችን አስከትሏል። እስካሁን የደረሰውን የንብረት ውድመት በውል ለይቶ አሃዙን ማስቀመጥ ባይቻልም በሸዋሮቢት ከተማ ብቻ ባሉ አራት ቀበሌዎች ውስጥ ከአራት መቶ በላይ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ አደጋ ወድመዋል። ነዋሪዎች በአሁኑ ወቅት ቤት ...
Read More »በአውስትራሊያ ሐገረ ስብከት ሆነው ለበርካታ አመታት ሲያገለግሉ የነበሩት ሊቀ ካህናት መዘምር ብሩ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ::
ሚያዚያ ፲፪(አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሜልበርን ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የበላይ አስተዳዳሪ እና እንዲሁም የአውስትራሊያ ሐገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ሆነውለበርካታ አመታት ሲያገለግሉ የነበሩት ሊቀ ካህናት መዘምር ብሩ በድንገት በተወለዱ በ71አመታቸው አፕሪል 18/ 2016 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል:: ሊቀ ካህናት መዘምር ብሩ ከልጅነታቸው ጀምሮ በቤተ/ክ ድጓ ጾመ ድጓንና አቋቋም በታወቁ የጎንደር ጉባዕዎች፣ ቅኔን በጎጃም እንዲሁም ዘመናዊ ትምህርትም በሩሲያ የተማሩ ...
Read More »በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢት ከተማ በጎርፍ አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ
ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2008) በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋ ሮቢት ከተማ ትናንት ሰኞ ከባድ ዝናብ ጥሎ ከ400 ሰዎች በላይ ሲፈናቀሉ፣ አገልግሎት ድርጅቶች መውደማቸውን የአይን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። በከተማው 03 ፥ 02 እና 05 ቀበሌ በደረሰው በዚሁ የጎርፍ አደጋ፣ በርካታ የንግድ ሱቁችና ሆቴሎችና የህክምና ተቋም በጎርፉ ተወስደዋል። በደረሰው ጎርፍ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም፣ የንግድ ሱቆችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች በጎርፍ ፈራርሰው ...
Read More »በጋምቤላ ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ ከ 20ሺ ሰዎች በላይ ተፈናቀሉ
ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2008) ከቀናት በፊት በጋምቤላ ክልል የተፈጸመውን የታጣቂዎች ጥቃት ተከትሎ ከ20ሺ በላይ ነዋሪዎች ከቀያቸው ተፈናቀሉ። እነዚሁ ነዋሪዎች በኑዌር ዞን በማላዌ፣ በጅካዎና በላሬ ወረዳዎች በሚገኙት ሶስት ወረዳዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጋትሉዊክ ቱት ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙና ይፋ አድርገዋል። ከሶስቱ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ጋምቤላ ከተማን ጨምሮ ወደተለያዩ አጎራባች አካባቢዎች ተወስደው የሚገኙ ሲሆን የክልሉ ካቢኔም ማክሰኞ የአስቸኳይ ስብሰባ ...
Read More »በጋምቤላ የተፈጸመው ጭፍጨፋ የሚያስገርም አይደለም አሉ
ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2008) የመንግስት ኮሚውኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በጋምቤላ በተደራጁ ሃይሎች የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ አዲስ ነገር አይደለም ማለታቸውን ዋሽንግተን ፖስት ዘገበ። “የምናውቀው ድርጊቱን የፈጸሙት እስከ ፍንጫቸው የታጠቁ፣ የተደራጁና የሚሰሩትን የሚያውቁ ናቸው። በዚህኛው የአፍሪካ ክፍል ጥቃቱ ያን ያክል የሚያስገርም አይደለም” ማለታቸውን ዋሽንግተን ፖስት በዘግባው አስፍሯል። አቶ ጌታቸው ረዳ መንግስታቸው ከኢትዮ- ደቡብ ሱዳን ድንበር አካባቢ በጥቃት አድራሾቹ ላይ የጋራ ...
Read More »ዶ/ር ቴዎድሮስ ለአለም ጤና ድርጅት ሃላፊነት እንዳይመረጡ ቅስቀሳ ተጀመረ
ኢሳት (ሚያዚያ 11 ፥ 2008) የኢትዮጵያውያ የሰብዓዊ መብት አቀንቃኝ ድርጅቶች ዶ/ር የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት እንዳይመረጡ ዘመቻ መጀመራቸውን አስታወቁ። በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ኢትዮጵያን አድቦኬሲ ኔትወርክ የሚባል ድርጅት ለአለም ጤና ድርጅት ዋና ሊቀመንበር ለሚስ ማሌና ፕሪሺየስ ማትሶሶ በጻፈው ደብዳቤ፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ የአለም ጤና ድርጅት ለመምራት እውቀትና አቅም የሌላቸው ሰው መሆናቸውን ገልጿል። የዶ/ር ቴዎድሮስ ለአለም ...
Read More »