ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2008) ባለፈው ሳምንት የታንዛኒያ መንግስት በኬንያ ድንበር እንዲሰፍሩ ያደረጋቸው ከ70 በላይ ኢትዮጵያውያና ስደተኞች ተመልሰው ወደታንዛኒያ እንደሚሄዱ የኬንያ ባለስልጣናት በድጋሚ ገለጡ። ሁለቱ ሃገራት በኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ውዝግብ ውስጥ ቢሆኑም የኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ መረጃ እንደሌለው አስታውቋል። ይሁንና፣ ኢትዮጵያውያኑ ስደተኖች ወደ ኬንያ ግዛት ዘልቀው እንዳይገቡ ጥበቃን እያደረጉ የሚገኙ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት 74ቱ ኢትዮጵያውያን ወደ ታንዛኒያ እንደሚመለሱ ዳግም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በድሬዳዋ የጣለው ዝናብ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ
ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2008) ሰኞ ጠዋት በድሬዳዋ ከተማ የጣለ ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በትንሹ አራት ሰዎች ሞቱ። ለተከታታይ አምስት ሰዓታት ያህል የጣለው ይኸው ከባድ ዝናብ በከተማዋ በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ላይ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ማድረሱንና በጎርፍ የተወሰዱ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችልም ፖሊስ አስታውቋል። በአካባቢው የጎርፍ አደጋን ለመከላከል ታስቦ የተሰራ ግድብም በጎርፍ አደጋው የተደረመሰ ሲሆን፣ የድሬ ዳዋ ከተማን ከሌሎች ቀበሌዎች ...
Read More »ቦብ ጌልዶፍ ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ተበረከተለት
ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2008) በ1977 በኢትዮጵያ ድርቅ በተከሰተበት ወቅት የሮክ ሙዚቃ ኮንሰርት በማዘጋጀት 65 ሚሊዮን ዶላር የዕርዳታ ገንዘብ በመሰብሰብ ለድርቅ ተጠቂዎች የለገሰው አየርላንዳዊው የሙዚቃ አቀንቃኝ ቦብ ጌልዶች ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ተበረከተለት። “ላይቭ ኤይድ” የሚል የሙዚቃ ድግስ ከማዘጋጀቱ ቀደም ብሎ በዝግጅቱ “የገና በዓል መሆኑን ያውቁ ይሆን? (Do they know it is Christmas?) የተሰኘ ነጠላ ዜማ በመስራት እኤአ በ1984 የገና ...
Read More »በደቡብ ሱዳን የሚንቀሳቀሱ የሲቪል ማህበረሰቦች የኢትዮጵያ መንግስት የሃይል እርምጃ እንዳይወስድ ጠየቁ
ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2008) ኢትዮጵያ ከ10 ቀን በፊት በጋምቤላ የተጠለፉባትን ከ108 በላይ ህጻናትን ለማስመለስና ከ 208 በላይ በግፍ የተጨፈጨፉት ዜጎቿን ለመበቀል በታጠቁ የሙልሌ ጎሳ ሃይሎች ላይ እርምጃ እንዳትወስድ በደቡብ ሱዳን የሲቪል ማህበረሰብ አባላት በመጠየቅ፣ የተጠለፉት ህጻናትም በድርድር ሊመለሱ ይችላሉ በማለት የተማፅኖ ደብዳቤ ጻፉ። የሙርሌ ብሄረሰብ በሚኖርበት በፒቦር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ሶስት የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች እንዳስታወቁት፣ በታጠቁ ሙርሌ ሃይሎች የተወሰደውን አሰቃቂ ...
Read More »በርካታ ቢሊዮን ብር የተመደበለት የጥጥ ልማት ፕሮጄክት ገንዘብ የት እንደደረሰ አልታወቀም ተባለ
ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት በሃገር ውስጥ ጥጥን ለማምረት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችንና በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብን ቢመድብም አብዛኛው የጥጥ ልማት ሳይለማ መቅረቱ ተገለጠ። ለዚሁ የእርሻ ዘርፍ ወደ 3 ቢሊዮን ብር አካባቢ በብድር መልክ ቢሰጥም አብዛኛው ገንዘብ ለተባለው አላማ እንዳልዋለ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ይፋ ማድረጉ ታውቋል። ለባለሃብቶች ከተሰጠው ብድር ውስጥም ባለሃብቶቹ ምን ያህሉን ለጥጥ ልማት እንዳዋሉትና የተቀረውንም ገንዘብ የት እንደገባ ...
Read More »በጋምቤላ ግጭቱ ተባብሶ ቀጥሏል ተባለ
ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2008) በጋምቤላ ክልል በሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መካከል በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት በትንሹ 14 ሰዎች መገደላቸውንና ግጭቱ በመባባስ ላይ መሆኑን አለም አቀፉ የእርዳታ ተቋማት ገለጡ። አንድ የግብረሰናይ ድርጅት ተሽከርካሪ ሁለት የኑዌር ጎሳ ተወላጆችን ገጭቶ በመግደሉ በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ አለመረጋጋት መፍጠሩንና ድርጊቱ ወደጎሳ ግጭት ማቅናቱን የተለያዩ አካላት ይፋ አድርገዋል። የህጻናቱን መገደል ተከትሎም በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች 10 ...
Read More »ከጋምቤላ ተጠልፈው የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን የደህንነት ሁኔታ አልታወቀም
ሚያዚያ ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሙርሌ ጎሳ አባላት ተጠልፈው የተወሰዱት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን፣ አስረኛ ቀናቸውን ቢያስቀጥሩም እስካሁን ሰዎቹ ስላሉበት ሁኔታ በቂ መረጃ ሊገኝ አልቻለም። ሚያዚያ 7 ቀን 2008 ዓም የሙርሌ ጎሳ አባላት በኑዌር ኢትዮጵያውያን ላይ በሰነዘሩት ጥቃት፣ ከ143 በላይ ሰዎች ሲገደሉ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩት መቁሰላቸው፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶችና ህጻናት እንዲሁም ከ2 ሺ በላይ የቀንድ ከብቶች ደግሞ መዘረፋቸው መዘገቡ ...
Read More »በድሬዳዋ በርካታ ሰዎች በጎርፍ ተወሰዱ
ሚያዚያ ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሚያዚያ 17 ንጋት ላይ በድሬዳዋ የጣለው ከባድ ዝናብ እስካሁን ድረስ በትንሹ 15 ሰዎች በጎርፍ መወሰዳቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ወደ መልካ ጀብዱ የሚወስደው ድልድይ የተሰበረ ሲሆን አንድ ገልባጭ የጪነት መኪናም በጎርፍ ተወስዷል። ወደ መልካ ጀብዱ በሚያሻግረው ወንዝ አንድ ድልድይ ተሰብሮ በህዝብ ማመላለሻ መኪና ውስጥ የነበሩ 18 ሰዎች መወሰዳቸውን እንዲሁም 1 ዩዲ ገልባጭ መኪና ረዳትና ...
Read More »በደብረዘይት የመከላከያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (METEC) የተሰሩ የእርሻ መኪኖች ጥራት የሌላቸው መሆኑ ቅሬታ መፍጠሩ ተነገረ፡፡
ሚያዚያ ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል የገዢው መንግስት በእርሻ ስራ ያደራጃቸው ወጣቶች እንዲሰሩበት የተሰጣቸው የእርሻ መኪና ጥራት ዝቅተኛ በመሆኑ ስራቸውን አቁመው ማህበራቸወን ለመበተን መገደዳቸውን ተናገሩ፡፡ በክልሉ ልዩ ልዩ ዞኖች የሚገኙት ቅሬታ አቅራቢ ወጣቶች ከዩኒቨርስቲና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ትምህርታችውን በመጀመሪያ ዲግሪና በዲፐሎማ ያጠናቀቁ ናቸው፡፡ ወጣቶቹ በእርሻ ስራው ለመሰማራት የሚያስችል ፕሮፖዛል አቅርበው ተቀባይነትን በማግኘቱ ገንዘብ በመቆጠብ ብድር ቢፈቀደላቸውም፤ባቀረቡት ...
Read More »አልሸባብ አንድ ወታደራዊ አዛዥን ጨምሮ ስድስት የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ
ሚያዚያ ፲፭(አሥራ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡባዊ ሶማሊያ ግዛት አወዲን ከተማ አቅራቢያ አውራጎዳና ላይ በተጠመደ ቦንብ አንድ ከፍተኛ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አዛዥን ጨምሮ ስድስት ወታደሮችን መግደሉን ድርጅቱ አስታውቋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በአካባቢው ወደ ነበረው የወታደራዊ ካንፕ ሲያመሩ በነበሩት ወታደሮች ላይ ጥቃቱ መፈጸሙን ተናግረዋል። የአፍሪካ ህብረትም ሆነ የኢህአዴግ መንግስት ስለደረሰው ጥቃት የሰጡት መግለጫ የለም።
Read More »