.የኢሳት አማርኛ ዜና

በየቀኑ ከ500 ያላነሱ ሰዎች በህገወጥ መንገድ ዱባይ ይገባሉ ተባለ

ሚያዚያ ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዱባይ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ለገልፍ ኒውስ እንደገለጹት ፣ በቤት ሰራተኛነት ለመቀጠር ከ500 ያላነሱ ኢትዮጵያውያን በየቀኑ የተለያዩ አየር መንገዶችን በመጠቀም በህገወጥ መንገድ ይገባሉ። በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አገራችን ገብተዋል የተባሉ ሰላሳ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ ወደ አገራቸው መላካቸውን የኤምሬትስ የስደተኞች ጉዳይ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በኤምሬትስ፣ኩዌትና በሳኡዲ አረቢያ በሕጋዊ መንገድ ከገቡ በኋላ የተሰጣቸው ...

Read More »

አይ ኦ ኤም ወደ የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ አሳስቦኛል አለ

ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2008) ጦርነት እልባት ወደ አላገኘባት የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንና ጉዳዩ አሳስቦት እንደሚገኝ የአለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ማክሰኞ አስታወቀ። ድርጅቱ ከተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር ከሃገሪቱ መውጫን አጥተው የሚገኙ ስደተኛ ኢትዮጵያውያንን በማውጣት ላይ ቢሆንም በተቃራኒው ግን ወደ የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር መጨመሩን (IOM) ይፋ አድርጓል። ባለፈው ወር ብቻ 10ሺ 424 ስደተኞች ወደ የመን ገብተው ...

Read More »

በምስራቃዊ ኢትዮጵያ የከፋ ረሃብና ሞት ሊያጋጥም እንደሚችል ቅድመ-ትንበያ ተሰጠ

ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2008) በድርቁ በተጎዱ ምስራቃዊ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የከፋ የረሃብ አደጋን ጨምሮ የሰዎች ሞት ሊያጋጥም እንደሚችል በቅድመ ረሃብ መከላከል ዙሪያ ትንበያ የሚሰጥ አንድ አለም አቀፍ ተቋም አሳሰበ። ይከው በአሜሪካ አለም አቀፍ የልማት ተቋም ስር የሚገኘው የቅድመ ማሳሰቢያ ጥምረት፣ የድርቁ አደጋ በሰዎች ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት እየተባባሰ መምጣቱን እንደገለፀ ብሉም በርግ የዜና አውታር ማክሰኞች ዘግቧል። የእርዳታ አቅርቦቱ እየተካሄደ ባለበት ...

Read More »

የምግብ ሸቀጣ-ሸቀጦች ዋጋ 6.3 በመቶ ማደጉ ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የምግብ ነክ በሆኑ ሸቀጣሸቀጦች ላይ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ተከትሎ የሃገሪቱ ምግብ ነክ የሆኑ ሸቀጣሸቀጦች ዋጋ በ 6.3 በመቶ ማደጉ ተገለጠ። በሃገሪቱ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ የምግብ እጥረት እንዲከሰትና የዋጋ ጭማሪን በማስከተሉ ምክንያት የባለፈው ወር የዋጋ ግሽበት ከአንድ በመቶ በላይ ማደጉ ታውቋል። በተመሳሳይ ህኔታም ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጣሸቀጦች ላይ የ8.7 በመቶ የዋጋ ጭማሪ የተመዘገበ ሲሆን ...

Read More »

435 ሺ ኢትዮጵያውያን ህጻናት በከፍተኛ ምግብ እጥረት ተጎድተዋል ተባለ

ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ውስጥ በበሽታ፣ በምግብ እጥረትና፣ በውሃ ጥማት ከተጋለጡት ከ6 ሚሊዮን ህጻናት ውስጥ፣ 435 ሺ የሚሆኑት በከፍተኛ የምግብ እጥረት የተጎዱ መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታወቀ። የህፃናት በምግብ መጎዳት የአእምሮና እድገትን የሚጎዳና የማሰብ ችግር የሚያመጣ መሆኑን አቶ ሳሙዔል ተፈራ የተባሉ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት ባለሙያን ጠቅሶ የአሜሪካ ድምጽ አገልግሎት የእንግሊዝኛው ክፍል ትናንት ሰኞ ...

Read More »

የመገናኛ ብዙሃን ቀንደኛ አፋኝ ተብለው ከተፈረጁ ሃገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ናት

ኢሳት (ሚያዚያ 25 ፥ 2008) በአለማችን ግንባር ቀደም የመገናኛ ብዙሃን አፋኝ ተብለው ከተፈረጁ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን በሃገሪቱ ያለው ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትም እየተባባሰ መምጣቱን የተለያዩ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ተቋማት ገለጡ። በየአመቱ በአለም ዙሪያ የሚከበረውን የፕሬስ ነጻነት ቀን አስመልክቶ ሪፖርታቸውን ያወጡት እነዚሁ ተቋማት በኢትዮጵያ 14 ጋዜጠኞች በእስር ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። ሃገሪቱ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን መቀመጫ ብትሆንም ጋዜጠኞች ...

Read More »

አቶ ሃይለማርያምን አጅበው የመጡ የአየር መንገድ ሰራተኞች ወደ ሌሎች ቦታዎች እንዳይዘዋወሩ ተከለከሉ

ሚያዚያ ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ ለእረፍት እና የአይን ማስተካከል የውበት ስራ በእንግሊዝኛ ኮስሜቲክ ሰርጀሪ ለማስደረግ በጀርመኗ የመናፈሻ ከተማ ባደን ባደን ከገቡ በሁዋላ፣ እርሳቸውን አጅበዋቸው የመጡት ፣ የአውሮፕላኑ ዋና አብራሪን ጨምሮ፣ ሌሎች የአየር መንገዱ ሰራተኞች ከከተማዋ እንዳይወጡ ተከልክለዋል። አቶ ሃይለማርያም ባደን ባደን ሲደርሱ ቀደም ብለው ለእረፍት የሄዱት ባለቤታቸውና ልጃቸው ተቀብለዋቸዋል። የአየር መንገዱ ሰራተኞችና እርሳቸውን አጅበው የመጡ ሰዎች፣ ...

Read More »

በደቡብ ኦሞ ለህወሃት አባላት ብቻ በሚል ቦታ አልሰጠንም ሲሉ የዞኑ አስተዳዳሪ ተናገሩ

ሚያዚያ ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ኦሞ ዞን ለኢንቨስትመንት በሚል መሬት ከወሰዱት መካከል 98 በመቶ የሚሆኑት የህወሃት ደጋፊና አባላት መሆናቸው በኢሳት ከተጋለጠ በሁዋላ ህዝቡ በጸረ ሙስና ስብሰባዎች ላይ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ፣ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ቦዲ ለማስተባበል ሞክረዋል። አቶ አለማየሁ ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በልማቱ ገብቶ እንዲሳተፍ መሬት አዘጋጅተን ሰጥተናል ቢሉም፣ መሬቱ በአንድ አካባቢ ሰዎች ተይዟል ወይስ አልተያዘም ...

Read More »

10 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በአራት ወራት ጊዜያት ውስጥ ተዘጉ።

ሚያዚያ ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ኤጀንሲ የተገኘ መረጃ እንደሚጠቁመው የውጭ ጉዲፈቻ ድርጅቶችን ጨምሮ የአለምአቀፍና የኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች በዋንኛነት በፋይናነንስ ችግር ምክንያት መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ተዘግተዋል። እነዚህም ድርጅቶች ኤልሮኢ አክሽን ፎር ዴቨሎፕመንት ፖዘቲቨ ውሜን ማህበር፣ አዶፕትስ ጆንስ ፍረም፣ ሄይነሪች ቦል ፋውንዴሽን፣ ካናዲያን አድቮኬት ፎር ዘአዶፕሽን ኦፍ ችልድረን፣ ሴኬም የልማት ድርጅት፣ ለውጥ በህብረት የተቀናጀ የማህበረሰብ ...

Read More »

በኢትዮጵያ በሕግ ሽፋን የዜጎችን መብት መጣስ ተባብሶ መቀጠሉን ሂውማን ራይት ሊግ አስታወቀ

ሚያዚያ ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያ ውስጥ የፀረ ሽብር ሕግን ከለላ በማድረግ መብታቸውን የሚጠይቁ ዜጎችን ማሰር፣ መግደልና ኢሰብዓዊ ድርጊቶችን መፈጸም ተጠናክሮ መቀጠሉን የምስራቅ አፍሪካ የሰብዓዊ መብት ሊግ ገልጿል። ድርጅቱ በኦሮሚያ ክልል የበርካታ ንጹሃንን ሕይወት የቀጠፈው ዘግናኝ እልቂት በህወሃት ኢህአዴግ መራሹ ገዥ ቡድን የተቀነባበረ መሆኑን አስታውቋል። ይህን ኢሰብዓዊ እልቂት ተቃውመው ለመብታቸው የታገሉት ከ 22 በላይ የኦሮሞ ብሔር ...

Read More »