ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) በሼህ መሃመር አላሙዲን የገንዘብ ድጋፍ በሰሜን አሜሪካ የሚንቀሳቀሰው AESA One (ኤሳ ዋን) የተባለው ተቋም በኢሳት ጋዜጠኛ ላይ የከፈተው ክስ ውድቅ ሆነ። በኢሳት የመዝናኛ ክፍል ጋዜጠኛ በሆነው beተወልደ በየነ ላይ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት የተመሰረተው ክስ ውድቅ የተደረገው፣ ራሱ ከሳሽ አካል ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉና ክሱን በማቋረጡ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። አመታዊ የስፖርት ውድድሮችን ለማካሄድ ባለፉት 4 አመታት በአንዳንድ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ከጋምቤላ ታፍነው የተወሰዱ ከ100 በላይ ህጻናት ያሉበት ስፍራ ተለይቶ ታውቋል ሲል የደቡብ ሱዳን መንግስት ረቡዕ አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) በቅርቡ በጋምቤላ ክልል በተፈጸመው ጥቃት ወደ ጎረቤት ደቡብ ሱዳን ታፍነው የተወሰዱ ከ100 በላይ ህጻናት ያሉበት ስፍራ ተለይቶ መታወቁን የደቡብ ሱዳን መንግስት ረቡዕ አስታወቀ። እነዚሁ ህጻናት ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው በታጠቁ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መሆናቸው እንደተረጋገጠ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ የሆኑት አቴኒ ወክ-አቴኒ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። ከ100 የሚበልጡት ኢትዮጵያውያን ህጻናቱ ከደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ 300 ኪሎሜትር ...
Read More »ዱባይ አየር ማረፊያ የደረሱ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወደ አገሪቷ እንዳይገቡ የመግቢያ ፈቃድ ተከለከሉ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) በዱባይ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በኩል ወደ ዱባይና የተባበሩት አረብ ኤመሬቶች ለመግባት የተጓዙ 30 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወደ ኢትዮጵያ ሊባረሩ እንደሆነ ተነገረ። ገልፍ ኒውስ የተባለ ጋዜጣ ትናንት ማክሰኞ እንደዘገበው ፍላይ ዱባይ በተባለ በዱባይ አየር መንገድ በአንድ የጉዞ መስመር ቲኬት ቆርጠው የተጓዙት ሴቶች ወደ አዲስ አበባ ተገደው እንደሚመለሱ ተነግሯል። የፍላይ ዱባይ ቃል አቀባይም የኢትዮጵያውያኑ ሴቶች መባረር ...
Read More »አቶ ዮናታን ተስፋዬ የሽብርተኛ ክስ ተመሰረተበት
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ለእስር ተዳርጎ የነበረው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወጣት ዮናታን ተስፋዬ በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ የጻፋቸው ጹሁፎችና አስተያየቶች በማስረጃነት ቀርበውበት የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል። ተከሳሹ የማህበራዊ ድረ-ገጾችን በመጠቀም አመጽና ብጥብጥን የሚያነሳሱ ጽሁፎች አሰራጭቷል እንዲሁም መንግስትን የሚተቹ ጽሁፎች ጽፏል ተብሎ በከሳሽ አቃቢ ህግ ራሱ እንደተመሰረተበት ታውቋል።
Read More »እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ 10 የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትንና 141 ሌሎች ሰዎችን ለምስክርነት እንዲቀርቡላቸው ጠየቁ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) ከወራት በፊት የግንቦት ሰባት ሃይልን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሲያቀኑ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉ አራት ተከሳሾች 10 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ 141 ሰዎችን በምስክርነት እንደቀረቧቸው ጠየቁ። አቶ አባይ ፀሃኤ፣ አቶ በረከት ስምዖን፣ ጄኔራል ሳሞራ የኑስ፣ አቶ አዲሱ ለገሰና አቶ ተፈራ ዋልዋ ተከሳሾቹ ለምስክርነት እንዲያቀርቧቸው የጠየቋቸው ምስክሮች መሆናቸው ታውቋል። የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የነበሩት አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ወ/ት ...
Read More »በርካታ ኢትዮጵያውያንን በህገወጥ መንገድ በማዘዋወር የተጠረጠረው ሃዱሽ ኪዳኑ በቁጥጥር ስር ዋለ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) በርካታ ኢትዮጵያውያን እና የሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ዜጎችን በህገ ወጥ መንገድ በማዘዋወር ወንጀል የተጠረጠረና ለዘጠኝ አመታት ያህል ሲፈለግ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ በስዊዘርላንድ በቁጥጥር ስር ዋለ። ሃዱሽ ኪዳኑ የተባለው ይኸው የ58 አመት ኢትዮጵያዊ በማልታ መንግስት የሚፈለግ በመሆኑ የስዊዘርላንድ መንግስት ተጠርጣሪውን ለማልታ መንግስት አሳልፎ መስጠቱም ታውቋል። ሃዱሽ በማልታ በነበረበት ወቅት በህገ-ወጥ የሰዎች ማዘዋወር ክስ ተመስርቶበት እንደነበርና የዋስትና መብት ...
Read More »የኢትዮጵያ ጦር ለመወረር ተዘጋጅቷል በሚል እሳቤ፣ ባላንጣ የነበሩ የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣናት ለመተባበር መስማማታቸው ተነገረ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016) ከሁለት ሳምንት በፊት በጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ድንበር ተሻግረው በመጡ ታጣቂዎች የተገደሉትን 208 ዜጎችን ለመበቀልና፣ የተጠለፉ ህጻናቱን ለማስለቀቅ የኢትዮጵያ መንግስት አጸፋዊ እርምጃ ሊወስድ ይችላል የሚለውን መላ ምት ተከትሎ፣ የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣናት በጥቃቱ እርስ በዕርስ መወነጃጀላቸውን ትተው አብረው ለመስራት መስማማታቸውን ሬዲዮ ታማዙጂ የተባለ የሱዳን ጣቢያ ገለጸ። የደቡብ ሱዳን ምክትል መከላከያ ሚንስትር የሆኑት ዲቪድ ያው ያዉ ...
Read More »የደሴ ነጋዴዎች የሁለት ቀናት የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
ሚያዚያ ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የከተማው ወኪላችን እንደገለጸው፣ ሚያዚያ 24 እና 25 ሙሉ በሙሉ፣ ዛሬ ደግሞ በከፊል የገበያ አዳራሾች ተዘግተዋል። በሰላም የገባ የአዳራሽ 624፣ በእድገት የገበያ አዳራሽ 638 ፣ በላኮመዛ የገባያ አዳራሽ 632 እንዲሁም በሚሊኒየም የገበያ አዳራሽ 562 ሱቆች የተዘጉ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል ከፊሎቹ ዛሬ ስራ ጀምረዋል። የአድማው ምክንያት ከአቅም በላይ የተጣለባቸው ግብርና ካሽ ሬጅስትራር ማሽን ...
Read More »አርበኞች ግንቦት 7ትን ሊቀላቀሉ ሲሉ መያዛቸው የተገለጸው ተከሳሾች የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ሳያቀርቡ ቀሩ
ሚያዚያ ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በብርሃኑ ተክለያሬድ መዝገብ ስር የሚገኙት ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ ፍቅረ ማርያም አስማማውና እየሩሳሌም ተስፋው ፣ ሚያዚያ 26፣ 2008 ዓም ከፍተኛው ፍርድ ቤት የቀረቡ ቢሆንም፣ ምስክሮቻቸውን አቅርበው ማሰማት ሳይችሉ ቀርተዋል። በበቂ ሁኔታ ሊከላከሉልን ይችላሉ ያሉዋቸው ምስክሮች ቃሊቲ እስር ቤት ሊያስወጣቸው ፈቃደኛ ባለመሆኑ መሆኑን እስረኞቹ ገልጸዋል። አቶ ብርሃኑ ፤ እራሳቸውን ችለው እየተከራከሩ መሆናቸውን ገልጸው፣ እንዲቀርቡላቸው ...
Read More »የደቡብ ሱዳን መንግስት ከ100 በላይ የተጠለፉ ህጻናት ያሉበትን ቦታ ማወቁን ገለጸ
ሚያዚያ ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ወር ከጋምቤላ በሙርሌ ጎሳ አባላት የተወሰዱት ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን ፣ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙና የኢትዮጵያ ጦርም ወደ ደቡብ ሱዳን ድንበር ዘልቆ መግባቱን ብሉምበርግ ተርሚናል የፕሬዚዳንቱን ቃል አቀባይ በመጥቀስ ዘግቧል። ቢቢሲ እንደዘገበው ደግሞ እስካሁን የተገኙት 41 ህጻናት ናቸው። የኢትዮጵያ ጦር በደቡብ ሱዳን መንግስት ፈቃድ ወደ አገሪቱ መግባቱንና ፍለጋም እያካሄደ መሆኑን ቃል ...
Read More »