ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዘ ሰን ዴይ ታይምስ እንደዘገበው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 ያለህጋዊ ወረቀት ወደ ማላዊ የገቡ 40 የሚሆኑ ህጻናት ኢትዮጵያውያን በሉሊዌንጌ በሚገኘው የካቸረ ጂቬኒለ እስር ቤት ታስረው ይገኛሉ። ኢትዮጵያውያኑ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያደርሷቸው ቃል የገቡላቸው የህገ- ወጥ አሻጋሪዎችና ደላሎች ተጠቂዎች መሆናቸውን ጋዜጣው ጠቅሷል። ማላዊ በክፍለ አህጉሩ ከአንድ ሀገር ወደ ሌላ ሀገር ለሚደረጉ እንዲህ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያውያን በየመንና ሶሪያ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ ሆነው እንኳን ወደ ሃገራቸው መመለስ እንዳማይፈልጉ ተገለጸ
ኢሳት (ሚያዚያ 28 ፥ 2008) በመካከለኛው ምስራቅ በችግር ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያዋውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን CAJ news Africa የተሰኘ ጋዜጣ ዘገበ። ባለፈው መጋቢት ወር ብቻ በጦርነት በምትናጠው ሶሪያ ችግር ውስጥ የነበሩ ከ1220 በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ታውቋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታየው ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመላቀቅ ወደመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የሚጓዙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር እየጨመረ መሄዱንም መረዳት ተችሏል። ኢትዮጵያውያኑ ለህገ ወጥ ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት በቡና ነጋዴዎች ላይ እስከ 5 አመት ድረስ የሚያስቀጣ አዲስ መመሪያ ተግባራዊ አደረገ
ኢሳት (ሚያዚያ 28 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ከቡና ንግድ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለማሳደግና በቡና ነጋዴዎች ላይ እስከ 5 አመት እስራትን የሚያስቀጣ አዲስ የቁጥጥር መመሪያን ተግባራዊ አደረገ። በሃገሪቱ በቡና ንግድ ላይ ተስማርተው የሚገኙ አካላት ደረጃቸውን ካልጠበቁና ካልተሰባበሩ ቡናዎች በስተቀር ሁሉንም ምርቶቻቸውን ለውጭ ገበያ ማቅረብ እንዳለባቸው መመሪያው ማስገዱዱን ዘ-ዎል ስትሪት የተሰኘ ጋዜጣ ዘጓል። አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ በማያደርጉ ቡና ነጋዴዎች ላይም ከ40ሺ ...
Read More »ኢትዮጵያውያን በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ገቡ የተባሉ አፍሪካውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኢሳት (ሚያዚያ 28 ፥ 2008) የደቡብ አፍሪካና የኬንያ መንግስታት ወደ ሃገሪት በህገ-ወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ በርካት ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አርብ አስታወቁ። የደቡብ አፍሪካ የፀጥታ ሃይሎች ጀርዎስተን ተብሎ በሚጠራው ምስራቃዊ ከተማ ሃሙስ ምሽት ባካሄዱት አሰሳ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 96 የሶማሊያ፣ የሞዛምቢክ፣ የዚምባብዌና የናይጀሪያ ስደተኞችን በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ለእስር ከተዳረጉት መካከልም ስድስቱ ሴቶች ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ19 ኣስከ 52 ...
Read More »በድሬዳዋ ጎርፍ የሰው ህይወት አጠፋ ፥ ንብረት አወደመ
ኢሳት (ሚያዚያ 28 ፥ 2008) ሃሙስ ምሽት በድሬዳዋ ከተማ ለሁለተኛ ጊዜ የተከሰተን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ በትንሹ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ። አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋማት በበኩላቸው በሃገሪቱ መከሰት የጀመረው የጎርፍ አደጋ የእርዳታ እህል አቅርቦት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖን በማሳደር ድርቁ እንዲባባስ ማድረጉን ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት በከተማዋ ደርሶ በነበረ ተመሳሳይ የጎርፍ አደጋ ጉዳት ደርሶበት ነበር የተባለውና ከተማዋን ከመልካጀብድ የሚያገናኝ ድልድይ በዚሁ ...
Read More »በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ አርሶደአሮች ከእንግዲህ ከመሬታችን በፈቃደኝነት አንፈናቀልም አሉ
ሚያዚያ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአቃቂ ቃሊቲ አካባቢ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች መሬታቸውን ለኮንዶሚኒዬም ግንባታ እንዲለቁ የመንግስት ባለስልጣናት ሊያግባቡዋቸው ቢሞክሩም፣ አርሶ አደሮቹ ግን ከእንግዲህ ለዲያስፖራ የኮንዶሚኒዬም ግንባታ መሬታችንን አንለቅም፣ እስዛሬ ያታለላችሁን ይበቃል በሚል፣ በታንታኮዬ የመሰብሰቢያ ቦታ የተዘጋጀው ስብሰባ ያለውጤት ተበትኗል። በአርሶ አደሮች ያልተጠበቀ መልስ የተበሳጩት ባለስልጣናት በውድ የማትለቁ ከሆነ በግድ ትለቃላችሁ በማለት ዝተዋል። በስብሰባው ላይ ...
Read More »ከትግራይ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር ጨምሯል
ሚያዚያ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህወሃት ስር በመትተዳደረዋ ትግራይ የሚኖሩ አርሶደአሮች በረሃቡ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች ክልሎች እየተሰደዱ መሆኑን ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው አርሰዶአደሮች ገልጸዋል። በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ምጽዋት የሚጠይቁ ከትግራይ የመጡ አርሶዶአሮች በብዛት እንደሚታዩ የገለጸው ዘጋቢያችን፣ አርሰዶአደሮቹ በድርቁ ምክንያት መሰደዳቸውን እንደነገሩት ገልጿል። ወደ አዲስ አበባ ከመጡ አንድ ወር ያክል የሆናቸው አርሶአደር፣ በድርቁ ምክንያት የሚቀመስ ...
Read More »ከገዢው ፓርቲ ደጋፊ ጋዜጦች መካከል አንደኛው በኪሳራና በድጎሟ እጦት ተዘጋ
ሚያዚያ ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲን የሚደግፉና በድጎማ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ጋዜጦች በገበያ እጦትና በድጎማ መቀነስ እየተዘጉ ሲሆን፣ በዜድ ፕሬስና ማስታወቂያ ኤጀንሲ ኃ/የተ/የግ/ማ በመባል በሚታወቀው የአቶ ሳምሶን ማሞ ድርጅት አማካይነት በየሳምንቱ ቅዳሜ የሚታተመው «ኢትዮቻናል» ጋዜጣ በኪሳራ ምክንያት መዘጋቱን አሳታሚው እንደገለጸላቸው አንዳንድ ጋዜጠኞች ለኢሳት ተናግረዋል። ኢትዮቻናል ጋዜጣ ፣ የሪፖርተር ጋዜጣ ባለቤት አቶ አማረ አረጋዊ ከሼክ አልአሙዲ ጋር ...
Read More »የኢንዱስትሪ ምርቶች የወጪ ንግድ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር ከአምስት በመቶ በላይ ቀነሰ ተባለ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2008) በተያዘው አመት የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ምርቶች የወጪ ንግድ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር ከአምስት በመቶ በላይ መቀነሱንና ድርጊቱ በውጭ ምንዛሪ ገቢ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ ተገለጠ። መንግስት ለተለያዩ ድርጅቶች ልዩ የማበረታቻ ድጋፍን በመስጠት የውጭ ንግድ ገቢን ለማሳደግ ጥረት ሲያደርግ ቢቆይም የተገኘው ውጤት ግን እጅግ አነስተኛ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቀዋል። የሃገሪቱ የኢንዱስትሪ ምርቶች ወጪ ንግድ በማስመልከት ለተወካዮች ምክር ...
Read More »በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ጎርፍ የእርዳታ አቅርቦትን አስተጓጎለ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2008) በቅርቡ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የጣለው ከባድ ዝናብ በአገሪቷ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የእርዳታ አሰጣጥ ሂደት እያስተጓጎለና እያወሳሰበ እንደሚገኝ ተገለጸ። የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች በጎርፉና ጭቃ ምክንያት እርዳታ ወደሚፈልጉ አካባቢዎች መሄድ እንዳልቻሉ ለመረዳት ተችሏል። በመሆኑም ራቅ ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ እርዳታ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን፣ እርዳታውን ሳያገኙ ለሳምንታት ችግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙ አሶሼይት ፕሬስ ረቡዕ አስነብቧል። በአንዳንድ አካባቢዎች ከከባድ ዝናብ ...
Read More »