.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኖረዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ግንቦት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያውያኑ ተቃውሞውን ያዘጋጁት የኖርዌይ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ ያላገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመቃወም፣ እንዲሁም ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ ከደቡብ ሱዳን ተጠልፈው የተወሰዱትና የ8 አመታት ፍርድ የተፈረደባቸውን የአቶ ኦኬሎ አኳይን ጉዳይ ኖርዌይ እንዴት እየተከታተለችው እንደሆነ ለመጠየቅና በኢትዮጵያ የሚፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለማጋለጥ መሆኑን የሰልፉ አስተባበሪ ከሆኑት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ፍቅሬ አሰፋ ...

Read More »

አምነስቲ  ኢንተርናሽናል አቶ ዮናታን ተስፋዬን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ ሲል ጠየቀ

ኢሳት ( ግንቦት 1 ፥ 2008) በማህበራዊ ድረ-ገጽ መንግስት በመተቸቱ ብቻ የታሰረው አቶ ዮናታን ተስፋዬና ሌሎች ያለምክንያት የታሰሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲቀቁ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ መንግስትን ጠየቀ። አቶ ዮናታን ተስፋዬ ከማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ተቃውሞና ከዚያ በኋላ የጸጥታ ሃይሎች በህዝቡ ላይ በወሰዱት መጠነ ሰፊ የሃይል እርምጃ ተከትሎ ፌስቡክ ላይ በጻፈው ትችት፣ ኢህአዴግ በሰላም ከመነጋገር ይልቅ  ሃይል መጠቀሙ ...

Read More »

የደቡብ ሱዳን መንግስት ከሙርሌ ታጣቂዎች ጋር ድርድር በማድረግ ህጻናትን ማስለቀቅ ጀምረዋል ተባለ

ኢሳት ( ግንቦት 1 ፥ 2008) የደቡብ ሱዳን መንግስት በቅርቡ ከጋምቤላ ክልል ታፍነው የተወሰዱ ህጻናትን በድርድር ማስለቀቅ መጀመሩን ሰኞ ገለጠ። ታፍነው የተወሰዱ ህጻናት ያሉበት ስፍራ መታወቁንና እየተካሄደ ባለው ድርድርም የተለቀቁ 19 ህጻናት ሰኞ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጉን የደቡብ ሱዳን ምክትል መከላከያ ሚኒስትር ሌተናል ጄኔራል ዴቪድ ያው ያው አስታውቀዋል። በቅርቡ በርካታ ታንኮችና ከባድ መሳሪያዎችን በመታጠቅ ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቆ ገብቷል የተባለው ...

Read More »

ሱዳንና ግብጽ በድንበር መንደሮች ላይ ያነሱት የይገባኛል ጥያቄ በአባይ ግድብ ድርድር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል ተባለ

ኢሳት (ግንቦት 1 ፥ 2008) የግብጽ እና የሱዳን መንግስታት ይገባኛል  የሚያነሱባቸው ሶስት የድንበር መንደሮች በአባይ ግድብ ድርድር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደራቸውን የግብፅ ባለስልጣናት ይፋ አደረጉ። የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አል-በሽር ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉ ጊዜ ግድቡ ሱዳንና ኢትዮጵያን የሚጠቅም ነው ሲሉ የሰጡት መግለጫ በግብፅ ዘንድ ቅሬታን መቀስቀሱንም አል-ሞኒተር የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። ሱዳንና ግብፅ በጋራ ድንበሮቻቸው ዙሪያ በሚገኙት የሃላየብ እና የሻላተን ...

Read More »

በጅቡቲ ወደብ እቃን የማያነሱ ነጋዴዎች ከንግድ ስራቸው እንዲታገዱ የሚያደርግ መመሪያ ወጣ

ኢሳት ( ግንቦት 1 ፥ 2008) ከጎረቤት ጅቡቲ ወደብ እቃን የማያነሱ ነጋዴዎች ከንግድ ስራቸው እንዲታገዱና የውጭ ምንዛሪ እንዲያገኙ የሚያደርግ መመሪያ ተግባራዊ ተደረገ። አስመጪ ነጋዴዎች በበኩላቸው መንግስት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በቂ ምክክርን ሳያደርግ እየወሰደ ያለው እርምጃ ተገቢ አይደለም ሲሉ ተቃውሞ ማቅረብ መጀመራቸው ታውቋል። ባለፈው ሳምንት መንግስት ከጅቡቲ ወደብ ገብተው በደረቅ ወደብ የተቀመጡ እቃዎች ከግንቦት 1, 2008 ጀምሮ እንደሚወረሱ ማስታወቁ የሚታወስ ሲሆን፣ ...

Read More »

ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ መከላከላይ ሰራዊት ወደ ግዛቴ አልገባም አለች

ኢሳት ( ግንቦት 1 ፥ 2008) የደቡብ ሱዳን መንግስት ከሶስት ሳምንት በፊት በጋምቤላ የተጠለፉትን ህጻናትን ለማስመለስ የኢትዮጵያ መንግስት ጦር ወደ አገሪቷ ገብቷል በሚል የአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ያቀረቡትን ዘገባ የተዛባ ወሬ ነው ሲል አስተባበለ። የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጪ ሰራዊት (SPLA) ቃል አቀባይ የሆኑን ብርጋዴር ሉል ሩዋይ ኮዓንግ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የኢትዮጵያ ጦር በደቡብ ሱዳን ገብቷል የሚለው የተዛባ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ...

Read More »

በማላዊ 34 ኢትዮጵያውያን ለእስር ተዳረጉ

ኢሳት (ግንቦት 1 ፥ 2008) የማላዊ መንግስት ወደ ሃገሪቱ በህገ-ወጥ መንገድ የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ መጨመሩ አሳስቦት እንደሚገኝ ሰኞ አስታወቀ። በቅርቡ 16 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር እንዳዋሉ የገለለጹት የሃገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች በሳምንቱ መገባደጃ እሁድ 34 ኢትዮጵያውያን በህገወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ገብታችኋል ተብለው ለእስር መዳረጋቸው ገልጸዋል። በፀጥታ ሃይሎች ከተያዙት ስደተኞች ኢትዮጵያውያኑ መካከል እንደኛው ክፉኛ ድብደባ ተፈጽሞበት ካቶንድዌ በሚባል ግዛት የህክምና ...

Read More »

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያልተወራረደና የተበላሸ ብድሩ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል።

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በየአመቱ በሚያወጣቸው የሂሳብ አያያዝ መግለጫዎቹ ከፍተኛ ትርፍ እንዳገኘ ሲናገር የቆዬው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2006 እና 2007 ዓም ባሉት 2 ዓመታት ብቻ 11 ቢሊዮን 273 ሚሊዮን ብር ያላወራረደው ገንዘብ ሲኖር፣ 1 ቢሊዮን 300 ሚሊዮን ብር ደግሞ የተበለሻ ብድር እንዳለው ሰነዶች አመለከቱ። በአውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ ሰኔ 30፣ 2014 ድረስ የተለያዩ የድርጅቱ ቅርንጫፍ ባንኮች ...

Read More »

አቶ ዳንኤል ሺበሺና የሽዋስ አሰፋ ተፈቱ

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምርጫ 2007ትን ተከትሎ በሽብርተኝነት የተከሰሱት የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሃላፊና የደቡብ ተወካይ አቶ ዳንኤል ሽበሺ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት ም/ል ሰብሳቢ አቶ የሺዋስ አሰፋ የእስር ጊዜያቸውን ጨርሰው ተፈተዋል። አቶ ዳንኤልና አቶ የሽዋስ ነሃሴ 14 ቀን 2007 ዓ•ም ፍርድ ቤት ነጻ ቢላቸውም፣ በችሎት መድፈር በተላለፈባቸው ውሳኔ እስከዛሬ በእስር እንዲቆዩ ...

Read More »

ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት መረጃ በማቀበል ወንጀል ተከሰሱ

ግንቦት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራሉ አቃቤ ህግ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 14ኛ ወንጀል ችሎት ምክትል አስር አለቃ አጃናው ታደሰና ምክትል አስር አለቃ ቻሌ ነጋ ላይ ለአርበኞች ግንቦት7 ወታደራዊ መረጃዎችን ሲያቀብሉ ነበር የሚል ክስ ተከፍቶባቸዋል። ሁለቱ ተከሳሾች 6ኛ እና 25ኛ ክፍለ ጦር ስር የሚገኙ ሬጅመንቶችን ብዛት እና መገኛ ቦታ በስልክና በቫይበር ማስተላለፋቸውን ሪፖርተር ዘግቧል። ተከሳሾቹ ...

Read More »