ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ተከስቶ ባለው የድርቅ አደጋ በከፋ የምግብ እጥረት የአካልና የጤና ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል ወደ 100ሺ የሚጠጉት በሆስፒታል ተኝተው ልዩ የህክምና ክትትልን የሚፈልጉ እንደሆነ ተገለጠ። ለአስቸኳይ የምግብ እጥረት ከተጋለጡ 10.2 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መካከል ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት ሲሆኑ 435ሺ የሚሆኑት ደግሞ በምግብ እጥረት ክፉኛ የአካልና የጤና ጉዳት ደርሶባቸው እንደሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል። ከእነዚሁ ህጻናት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በወላይታ ዞን በደረሰ የመሬት መንሸራተት የ41 ሰዎች ህይወት ጠፋ
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2008) በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮሻ ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት በትንሹ 41 ሰዎች ሞቱ። በዞኑ በሚገኙ አምስት ቀበሌዎች የጣለን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በደረሰው በዚሁ የመሬት መንሸራተት አደጋም ወላይታ ከተማን ከዳውሮ ዞን የሚያገናኝ መንገድ ከአገልግሎት ውጭ መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል። በደረሰው የመሬት መንሸራተት ቁጥራቸው ሊታወቅ ያልቻለ ሰዎች የተቀበሩ በመሆኑ የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑንም ለመረዳት ተችሏል። ...
Read More »ከማኑፋክቸሪን ዘርፍ ከእቅድ በታች ገቢ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚንስቴር ገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2008) በተያዘው በጀት አመት ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ወደ 500 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 290 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 290 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መገኘቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ማከስኞች አስታውቋል። መንግስት የውጭ ንግዱን ልዩ ድጋፍ በመስጠት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪን ለማግኘት እቅድ ቢይዝም የታሰበው ገቢ ሊገኝ አለመቻሉንም ባለስልጣናት በመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። በተያዘው በጀት አመት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የተለያዩ ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት የሚደርስበትን ተቃውሞ በሃይል እና በፍርድ ቤት ለመቆጣጠር እየሞከረ እንደሆነ ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል ከማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ ከተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት በኋላ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ሃሳብን በነጻነት የሚገልጹትን ዜጎች በጥይት ብቻ ሳይሆን፣ ፍርድ ቤቶችን ጭምር በመጠቀም ሙሉ በሙሉ ማፈን መጀመሩን የሰብዓዊ መብቶች ተመልካች ድርጅት (Human Rights Watch) ገለጸ። እንደ Human Rights Watch ገለጻ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በታዋቂ ሰዎች፣ በተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና በሌሎች ሰዎች ላይ ሽብርተኝነትን ጨምሮ አዳዲስ የፖለቲካ-ነክ ...
Read More »ዘላለም ወርቅ አገኘሁ እስራት ተፈረደበት
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2008) ከእነ መምህር አብርሃ ደስታ ጋር በአሸባሪነት ተከሶ ላለፉት ሁለት አመታት ያህል በወህኒ ቤት የቆየው ዘላለም ወርቅ አገኘሁ ማክሰኞ ግንቦት 2 ፥ 2008 እስራት ተፈረደበት። ከአንድነት፣ ሰማያዊና አረና ፓርቲ አመራሮች ጋር በሃምሌ ወር 2006 የታሰረውና ላለፉት 22 ወራት ያህል በማዕከላዊ ምርመራና በአዲስ አበባ ወህኒ ቤት የቆየው ዘላለም ወርቅ አገኘሁ የግንቦት 7ትን የሽብር ዓላማ በመደገፍ በሚል ተወንጅሎ ...
Read More »በአርባ ምንጭ ያልታወቁ ሃይሎች የፖሊስ አባላትን ገደሉ
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2008) በአርባ ምንጭ ነጭ ሳር ፓርት አካባቢ ያልታወቁ ሃይሎች ከመንግስት ሃይሎች ጋር ባደረጉት ግጭት ቁጥራቸው ያልተገለጸ የፖሊስ አባላት ሲገደሉ፣ ከጣታቂዎች ወገን እንግዳ አበበ የተባለ ወጣት መገደሉን የአካባቢ ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። በርካታ የፌዴራል ፖሊሶች ለህክምና ሆስፒታል መግባታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በከተማዋ የቤት ለቤት አሰሳ መቀጠሉም መረዳት ተችሏል። ቅዳሜ ሚያዚያ 29 ፥ 2008 ነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርት አካባቢ በፌዴራል ...
Read More »በምስራቅ ሃረርጌ በተነሳው ተቃውሞ ከ3 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉ
ግንቦት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው በምስራቅ ሃረርጌ ዞን በካራ ሚሊ ከተማ ትናንት በመንግስት ደጋፊ እና በመንግስት ተቃዋሚ ግለሰብ መካከል የተነሳው አለመግባባት ወደ ህዝባዊ አመጽ ተቀይሯል። የጸቡ መነሻ በከተማው ውስጥ በመሰራት ላይ ካለው መስጊድ ግንባታ ጋር የሚያያዝ ሲሆን፣ መንግስት ያስቀመጣቸው የመስኪዱ ተወካዮች መንግስትን ከሚቃወሙት ጋር ግጭት ውስጥ መግባታቸው ታወቋል። የመንግስት ደጋፊ የሆነው አቶ ሰኢዴ የተባለው ግለሰብ ...
Read More »በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሃረር ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ታወቀ
ግንቦት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሆኑ በብዛት የአማራ እና ደቡብ ተወላጆች ምስራቅ እዝ ሚሊተሪ እስር ቤት ጨለማ ቤት ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል። እስረኞቹ ከተለያዩ አካባቢዎች ተሰብሰብው የመጡ ሲሆን፣ አንዳንዶች በሰራዊቱ ውስጥ ፍትሃዊ የሆነ የብሄር የስልጣን ክፍፍል እንዲኖር የጠየቁ ናቸው። ምስራቅ እዝ እስር ቤት ከምስራቅ እዝ ሆስፒታል ጎን የሚገኝ ሲሆን፣ እስር ቤቱ ከምድር በታች ...
Read More »ፍርድ ቤት በአቶ ዘላለም ወርቅአገኘሁ ላይ የፍርድ ውሳኔ አሳለፈ
ግንቦት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሽብር ተጠርጥሮ ከሁለት ዓመታት በላይ በእስር ሲንገላታ የነበረው የደ-ብርሃን ብሎግ ተባባሪ ጦማሪ ዘላለም ወርቅአገኘሁ አምስት ዓመት ከአራት ወራት እስራት ተፈርዶበታል። አቃቤ ሕግ በዘላለም ወርቅ አገኘሁ ላይ ያቀረበበት ክስ በሽብርተኝነት ከተፈረጀው ከአርበኞች ግንቦት ሰባት ጋር በማበር በመንግስት ላይ አመጽ ማነሳሳት የሚል ነው። በዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ የተከሰሱት አቶ ሃብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሽበሺ፣ አብርሃ ...
Read More »በኮንቴነር ውስጥ ሆነው ሲጓዙ የነበሩ 33 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ዛንቢያ ውስጥ ተያዙ
ግንቦት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዛንቢያ የስደተኞች ጉዳይ በሕገወጥ መንገድ በኮንቴነር ውስጥ ተደብቀው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በጉዞ ላይ የነበሩ 33 ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ስደተኞችን መያዙን አስታውቋል። ካፉ ከተማ አቅራቢያ በካርጎ ኮንቴነር ተሸሽገው ሲጓዙ የነበሩት ስደተኞች ማንነታቸውን የሚገልጽ ምንም ዓይነት ሕጋዊ ፓስፓርትና ሰነድ አለመያዛቸውን የስደተኞች ጉዳይ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ናማቲ ኒሺንጋ አስታውቀው ስደተኞቹን ጭኖ ሲያጓጉዝ የነበረው የመኪናው ...
Read More »