ግንቦት ፲፪ (አሥራ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በሕገወጥ መንገድ ድንበር አቋርጣችሁ ወደ ኬንያ ገብታችኋል ተብለው በኢንቡ እስር ቤት ላለፉት ሃያ ሰባት ቀናት ታስረው የነበሩና የእስር ጊዜቸውን ያጠናቀቁ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የኬንያ መንግስት ወደ አገራቸው ሊመልሳቸው መወሰኑን በመቃወም የርሃብ አድማ አድርገዋል። ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ምንም ዓይነት ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው በመሆኑ ኬንያ ውስጥ መቀመጥ አይችልም ሲል የአገሪቱ ፍርድ ቤት በይኗል። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የጎርፍ አደጋ ከ230ሺ በላይ ሰዎችን አፈናቀለ
ኢሳት ዜና (ግንቦት 11 ፥ 2008) በቅርቡ በተለያዩ ክልሎች የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከ230 ሺ በላይ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቀሉ። ሃገሪቱ ለምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ዜጎች በቂ ምላሽን ባላገኘችበት በአሁኑ ወቅት የጎርፍ አደጋ እያደረሰ ያለው ጉዳት ተጨማሪ ስጋት ፈጥሮ መገኘቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሃሙስ አስታውቋል። በምስራቃዊ ኢትዮጵያ እና በሶማሊ ክልል ካለፈው ወር ጀምሮ የደረሰው ይኸው የጎርፍ አደጋ በአጠቃላይ 237 ...
Read More »በአዲስ አበባ ቤቶችን የማፍረስ እርምጃ ቀጥሎ፣ በግጭቱ ሶስት ሰዎች መሞታቸው ተነገረ
ኢሳት ዜና (ግንቦት 11 ፥ 2008) ህገወጥ የተባሉ ቤቶችን የማፍረሱ እርምጃ ዛሬ ሃሙስ ቀጥሎ በተፈጠረ ግጭት ተጨማሪ ሶስት ሰዎች መሞታቸውን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል። የመኖሪያ ቤታቸው ከፈረሱባቸው ግለሰቦች መካከልም አንደኛው ሁለት የጸጥታ ሃይሎችን በመግደል የራሱን ህይወት እንዳጠፋም የአካባቢው ነዋሪዎች ከዜና ክፍላችን ጋር በደረጉት ቃለ ምልልስ አስረድተዋል። የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሚናገሩት ነዋሪዎች ወረገኑ የሚወስዱ መንገዶች በሙሉ ዝግ ተደርገው ...
Read More »የመኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ በተካሄደው የጸጥታ ሃይሎች እርምጃ በትንሹ 12 ሰዎች ተገደሉ
ኢሳት ዜና (ግንቦት 11 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ህገወጥ ናቸው የተባሉ የመኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ በተካሄደው የጸጥታ ሃይሎች እርምጃ በትንሹ 12 ሰዎች ተገደሉ። የከተማው አስተዳደር በቦሌ አውሮፕላን አየር ማረፊያ ጣቢያ አቅራቢያ በተለምዶ ወረገኑ አካባቢ የተገነቡ በርካታ መኖሪያ ቤቶች በህገወጥ መንገድ የተያዙ ናቸው በማለት የማፍረስ እርምጃን እየወሰደ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ለኢሳት አስረድተዋል። እነዚሁ የመኖሪያ ቤቶችን ለማፍረስ ፖሊስ አፍራሽ ግብረ ...
Read More »በግብፅ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ 66 ተሳፋሪዎች ሞቱ
ኢሳት ዜና (ግንቦት 11 ፥ 2008) ትናንት ማክሰኞች ሌሊት ከፓሪስ 66 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የግብጽ አየርመንገድ አውሮፕላን በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ በመከስከሱ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩት ሁሉም ተሳፋሪዎቹ መሞታቸው ተገለጸ። ኤር ቡስ 320 የተባለው ይኸው አውሮፕላን ትናንት በመጀመሪያ 90 ዲግሪ ወደግራ፣ ቀጥሎ 360 ዲግሪ ወደቀኝ በመሽከርከር ከ7.5 ኪሎሜትር ከፍታ ተምዘግዝጎ በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ መውደቁን የተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በ2003 ...
Read More »በአዲስ አበባ ከቤት ፈረሳ ጋር በተያያዘ በተነሳው ተቃውሞ የሟቾች ቁጥር አሻቀበ
ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በህገወጥ መንገድ ተገንብተዋል የተባሉትን ቤቶች ለማፍረስ ወደ ወረዳ 12 የተጓዙት አፍራሽ ግብረሃይሎች እና እነሱን የሚያጅቡዋቸው በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የፌደራል ፖሊሶች ከነዋሪዎች ያጋጠማቸውን ሰላማዊ ተቃውሞ፣ በጥይት ለመመለስ በወሰዱት እርምጃ ከ8 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን፣ ከ100 ያላነሱ ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውን የአይን እማኞች ለኢሳት ተናግረዋል። ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ነዋሪዎች እንደሚሉት ፣ የሟቾቹን ቁጥር በትክክል ...
Read More »በኦሮምያ ህዝባዊው ተቃውሞው አገረሸ
ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለሳምንታት ጋብ ብሎ የነበረው የኦሮምያ ክልል ተቃውሞ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መጠነኑን እያሰፋ በመምጣት ላይ ሲሆን፣ ዛሬ በምእራብ ሃረርጌ የማሳለ ከተማ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ አሰምተዋል። ከሁለት ቀናት በፊት በአሰቦ ከተማ ተመሳሳይ ተቃውሞ የተካሄደ ሲሆን፣ ትናንት ምሽት ደግሞ በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የፈደራል ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ እርምጃ ወስደዋል። በርካታ ተማሪዎችም መጎዳታቸው ታወቋል። ...
Read More »የሼር ኩባንያ ገመና ይፋ ሆነ
ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሆላንዱ ሼር ኩባንያ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ የአበባ አምራጭ ኩባንያ ነው። ድርጅቱ በፈርንጆች አቆጣጠር በ2004 ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት 1 ሺ የእግር ኳስ ሜዳ በሚያክል መሬት ላይ የአበባ እርሻ ልማት ስራ ጀምሯል። ድርጅቱ በአመት 1 ቢሊዮን 200 ሚሊዮን የጽጌረዳ አበባ ወደ ሆላንድ ይልካል። አበባዎቹን ለማሳደግ ደግሞ በእያመቱ 2 ሺ የኦሎምፒክ የመዋኛ ...
Read More »በደቡብ ሱዳን የሃይል አዛዥ የሆኑት ሌ/ተ ጄ/ል ዮሃንስ ገብረመስቀል በኬንያዊው ጄኔራል ተተኩ
ግንቦት ፲፩ (አሥራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባንኪ ሙን በደቡብ ሱዳን የሃይል አዛዥ የሆኑትን ሌ/ተ ጄ/ል ዮሃንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያምን በኬኒያው ጄኔራል ጆንሰን ሞጎአ ኪማኒ መተካታቸው ታወቀ:: ሌተናት ጀነራል ዮሃንስ ላለፉት ሶስት አመታት በደቡብ ሱዳን ያገለገሉ ሲሆን በአብዬ ግዛት የሃይል አዛዝ ሆነው አገልግለዋል:: ኒወርክ ካለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሰሩ ሰራተኞች ባደረሱን መረጃ ጄ/ል ...
Read More »በ94 በሚሆኑ መንግስታዊ መ/ቤቶች ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደ ሂሳብ መገኘቱን ፌዴራል ዋና ኦዲተር ገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 10 ፥ 2008) የፌዴራል ዋና ኦዲተር ጽ/ቤት የመከላከያ ሚኒስቴርን ጨምሮ በ94 መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ያልተወራረደ ሂሳብ መገኘቱን ይፋ አደረገ። የ2007 የመንግስት መሪያ ቤቶች በጀት አጠቃቀም በተመለከተ ሪፖርቱን ለፓርላማ ያቀረበው ጽ/ቤቱ በመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች የሚፈጸሙ የፋይናንስ ጥሰቶች ከአመት አመት እየተባባሰ መምጣቱንም አስታውቋል። የመከላከያ ሚኒስቴር የምርጫ ቦርድ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ኤርፖርቶች ቅርንጫፍ ...
Read More »