.የኢሳት አማርኛ ዜና

ጠላቶቻችን ወደ ውስጥ ሰርገው በመግባት ሊያዳክሙንና ሊያሽመደምዱን እየሞከሩ ነው ሲል ኢህአዴግ አስታወቀ

ግንቦት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 25ኛውን የግንቦት20 በአል በማክበር ላይ የሚገኘው ኢህአዴግ ለውይይት ባዘጋጀው ሰነዱ ላይ ግንባሩ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ መውደቁን አትቷል። ባለፉት 25 አመታት ከፍተኛ ድል በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መስኮች የተመዘገበ ቢሆንም፣ እነዚህን ድሎች የሚቀለብሱ እንዲሁም የአገሪቱን ህልውና አደጋ ውስጥ የሚጥሉ አዝማሚያዎች እየታዩ ነው ብሎአል። ኪራይ ሰብሳቢዎችና የኒዮ ሊበራል ሃይሎች ከውጭ ሆነው ከሚያካሂዱት ጥቃት ...

Read More »

የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና መውጣቱን ተከትሎ ፈተናው መሰረዙን መንግስት አስታወቀ

ግንቦት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ሊካሄድ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና መውጣቱን ተከትሎ መንግስት ፈተናውን ለመሰረዝ የተገደደ ሲሆን፣ በተማሪዎች በኩል የተለያዩ አስተያየቶች እየተስተናገዱ ነው። በወላይታ ሶዶ ፈተናው መሰረዙን የሰሙ ተማሪዎች ተቃውሞ አድርገው የነበረ ቢሆንም፣ የፌደራል ፖሊሶች በትነዋቸዋል። ከተለያዩ የገጠር ከተማዎች የመጡ ተማሪዎች፣ ከእንግዲህ ወዲያ ወደ ቤተሰቦቻችን የምንሄድበትም ሆነ ከተማ የምንቆይበት ገንዘብ ስለሌለን መንግስት አንድ ...

Read More »

በዩጋንዳ ኢትዮጵያ ሬስቶራንት ላይ ጥቃት የፈጸሙ ግለሰቦች የእድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸው

ኢሳት (ግንቦት 19 ፥ 2008) ዩጋንዳ መዲና ካምፓላ በሚገኘው የኢትዮጵያ ሬስቶራንት (ምግብ ቤት) ላይ ከስድስት አመት በፊት በተፈፀመው የሽብር ጥቃት ሃሙስ የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈባቸው አምስት ተከሳሾች የእድሜ ልክ የእስር ፍርድ ተላለፈባቸው። በተመሳሳይ ክስ ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ሁለት ተከሳሾች ደግሞ የ50 አመት የእስር ቅጣት እንደ ተበየነባቸው ቢቢሲ የዩጋንዳን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔን ዋቢ በማድረግ አርብ ዘግቧል። የሽብር ጥቃቱን በዋነኛነት አቀናብሯል የተባለው ...

Read More »

ወደ አውሮፓ የሚፈልሱትን የአፍሪካ ስደተኞች ለማስቆም የአውሮፓ ህብረት ለአፍሪካ አምባገነን መሪዎች የገንዘብ ስጦታ መደበ

ኢሳት (ግንቦት 19 ፥ 2008) ከአፍሪካ ወደ አውሮፓ የሚጎርፉ ሰደተኞችን ለመግታት የአውሮፓ ህብረት ስደተኞቹ ለሚመነጩባቸው ሃገራት መሪዎች ከፍተኛ ገንዘብ ለመስጠት በሚስጥር እየመከረ መሆኑ ተገለጸ። በዚህም የሱዳኑን አልበሽርን ጨምሮ ማንነታቸው ላልተገለጸ ስምንት የአፍሪካ አምባገነን መሪዎች 46 ሚሊዮን ዩሮ ወይም ከ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሰጥ ሲወያዩ እንደነበር ዴይሊ ሜይል የተባለ በእንግሊዝ የሚታተመው ጋዜጣ የጀርመንን መገናኛ ብዙሃንን ዋቢ በማድረግ በዛሬው ሃሙስ ኣጋልጧል። ...

Read More »

ከጋምቤላ ክልል በሙርሌ ጎሳ አባላት የተጠለፉ ህጻናት ጉዳይ አነጋጋሪ መሆኑን የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ

ኢሳት (ግንቦት 19 ፥ 2008) ባለፈው ወር በጋምቤላ ክልል በሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የተፈጸመው ጥቃት ወደ 2ሺ በሚሆኑ ታጣቂዎች መፈጸሙንና በድርድር ያልተለቀቁ ህጻናት ጉዳይ አነጋጋሪ ሆነ መቀጠሉን አልጀዚራ የቴለቪዥን ጣቢያ አርብ ዘገበ። የደቡብ ሱዳን መንግስት ከጎሳ አባላቱ ተወካዮች ጋር ሲያካሄድ የቆየውን ድርድር ተከትሎ ወደ 53 የሚጠጉ ህጻናት የተለቀቁ ሲሆን የተቀሩ ህጻናት ህልውና ግን ለአካባቢው ነዋሪዎች ስጋት መፍጠሩን የቴለቪዥን ጣቢያው ከነዋሪዎቹ ጋር ...

Read More »

“ህዝቡ ከኢህአዴግ መሪዎች ይልቅ በውጭ ለሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች እውቅና እየሰጠ ነው” ሲል የደህንነት መስሪያ ቤቱ አስታወቀ

ግንቦት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ 25ኛ አመት በአሉን እያከበረ በሚገኝበት ወቅት እያደረገ ባለው ግምገማ የደህንነት መስሪያ ቤቱ ለስርአቱ አደጋ ሊፈጥሩ ይችላሉ ያላቸውን ጉዳዮች ለውይይት ከማቅረብ ባሻገር ፣ ህዝቡ በአገር ውስጥ ላሉ የኢህአዴግ ባለስልጣናት ከሚሰጠው እውቅና ይልቅ በውጭ አገር ለሚገኙ የተቃዋሚ መሪዎች እየሰጠ በመምጣቱ የስደት መሪዎችን እስከመሾም ተደርሷል ብሎአል ። የደህንነት እና መረጃ ክፍል ባቀረበው ...

Read More »

ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛል ተብሎ የታቀደው የቆዳ እና ሌጦ ኢንዱስትሪ ውጤታማ አልሆነም

ግንቦት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አምና ኢትዮጵያ ወደ ውጭ አገር እቃዎችን በመላክ ያገኘችው ገቢ ማሽቆልቆሉ ያስደነገጣቸው የመንግስት ባለስልጣናት በዚህ እና በመጪዎቹ አመታት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የማግኘት እቅድ ነድፈው ነበር። ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ያስገኛሉ ተብሎ ተስፋ ከተጣለባቸው ምርቶች አንዱ ቆዳና ሌጦ ቢሆንም ፣ ባለፉት 9 ወራት የተገኘው ውጤት ከአምናው ጋር ሲተያይ ከ20 በመቶ በላይ አሽቆልቁሏል። በእቅዱ ...

Read More »

የአቶ አንዳርጋቸው የ9 ዓመት ልጅ በእንግሊዝ መንግስት ላይ ክስ አቀረበች

ግንቦት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአሜሪካና የእንግሊዝ ዜግነትን አጣምራ የያዘችው ምናቤ አንዳርጋቸው የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ በሚከታተሉ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰራተኞች ላይ በጠበቃዎቹዋ አማካኝነት ክስ መስርታለች። ላለፉት 2 ዓመታት በእስር ላይ የሚገኘው አቶ አንዳርጋቸው ከሁለት አመት በፊት በጣም ለአጭር ጊዜ ካደረገው የስክል ጥሪ በስተቀር ከቤተሰቡ ጋር እንዲገናኝ አልተፈቀደለትም ሲል ጉዳዩን የሚከታተለው ሪፕሪቭ የተባለው የህግ ባለሙያዎች ...

Read More »

ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በማላዊ እስር ቤትና በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በስቃይ ላይ ናቸው

ግንቦት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አገር አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ሲሞክሩ በማላዊ መግቢያና መውጫ ድንበሮች አካባቢ የተያዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእስር ቤትና በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በስቃይ ላይ እንደሚገኙ ተዘገበ። ማላዊ በሚገኘው ዲዛካ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UNHCR) ስር ባሉት የመጠለያ ጣቢያዎች ካሉ 24 ሽህ ስደተኞች ሲኖሩ፣ ከእነዚህ መካከል በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ...

Read More »

በአዲስ አበባ ወረገኑ ቤት የማፍረስ ዘመቻ ቀጥሎ በግጭቱ የአንድ ሰው ህይወት ጠፋ

ኢሳት (ግንቦት 18 ፥ 2008) ሰሞኑን በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ወረገኑ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ህገወጥ ናቸው የተባሉ የመኖሪያ ቤቶችን የማፍረሱ እርምጃ ሃሙስም ለሁለተኛ ሳምንት ጊዜ ቀጥሎ ተጨማሪ አንድ ሰው መሞቱን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መናገር ያልፈለጉት ነዋሪዎች የጸጥታ ሃይሎች አሁንም ድረስ በአካባቢው በመስፈር በነዋሪዎች ላይ እርምጃን እየወሰዱ መሆኑን አስታውቀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወረገኑ ተብሎ ...

Read More »