.የኢሳት አማርኛ ዜና

ከ202 ሚሊዮን ብር በላይ የወጣበት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና መሰረዙን ተከትሎ ተማሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ነው

ግንቦት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከፍተኛ ወጪ የወጣበት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና መሰረዙ በተለዩ አካባቢዎች ተማሪዎች ተቃውሞ እንዲያነሱ እያደረጋቸው ሲሆን፣ መንግስት ለደረሰባቸው ኪሳራ ተገቢውን ካሳ እንዲሰጥ ይጠይቃሉ። በምእራብ ጎጃም ዞን ደጋ ዳሞት ወረዳ የሚገኙ ተማሪዎች ባካሄዱት ተቃውሞ ፣ “የፈተናው ወረቀት ለእኛም ይሰጠንና እንዘጋጅበት፣ ይህ ካልሆነ ፍትሃዊ ውድድር እንዳልተደረገ ይቆጠራል” የሚል ጥያቄ አንስተው ተቀባይነት ባለማግነቱ ፣ ተማሪዎቹ ...

Read More »

የፌደራል ፖሊስ አባላት በብዛት ስራቸውን እየለቀቁ ነው

ግንቦት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ለስርዓቱ መቀጠል ዋስትና ይሆናሉ ተብለው ከሚታመንባቸው የጸጥታ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የፌደራል ፖሊስ በሰው ሃይል ድርቅ እየተመታ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። የፖሊስ አባላቱ ከሚደርስባቸው አስተዳደራዊ ጭቆና፣ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የተስፋፋው ፍጹም ዘረኝነት እንዲሁም የኢኮኖሚ ችግርና በአጠቃላይ በስርዓቱ ላይ ተስፋ በማጣት ስራቸውን እየለቀቁ በመጥፋት ላይ ናቸው። የወታደሮቹ መጥፋት ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ የጣለው መንግስት፣ ...

Read More »

በደሴ  የተጠራው የግንቦት 20 ድጋፍ ሰልፍ ከሸፈ

ግንቦት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወኪላችን እንደገለጸው መንግስት በከተማዋ ግንቦት19 ጠርቶት የነበረው የድጋፍ ሰልፍ ህዝቡ በሰልፉ ለመገኘት  ፈቃደኛ ባለመሆኑ ከከሸፈ በሁዋላ፣ በድጋሜ በማግስቱ ህዝቡ የስኳርና የዘይት ኩፖን ይዞ እንዲወጣ ጥሪ ቢደረግለትም ለመውጣት ፈቃደና ባለመሆኑ የተወሰኑትን በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁትን ሰዎች ብቻ በመያዝ በአሉን አክብሮአል። ዛሬ ግንቦት  24 ደግሞ ህዝቡ ነገ በሰልፍ ለኢህአዴግ ድጋፉን እንዲገልጽ ለማድረግ ካድሬዎቹ ቤት ለቤት  ...

Read More »

ፊሊፕ ሃሞንድ ስለ አቶ አንዳርጋቸው መጠየቅ አለባቸው ተባለ

ግንቦት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊሊፕ ሃሞንድ ለሁለት ቀናት በኢትዮጵያ በሚያደርጉት ጉብኝታቸው ከየመን ታፍነው የተወሰዱትን የሶስት ልጆች አባትና የዴሞክራሲ አቀንቃኝ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ ጥያቄ እንዲያቀርቡ የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚከታተለው ሪፕሪቭ የተባለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ጥያቄ አቅርቧል። አቶ አንዳርጋቸው ሰብዓዊ መብታቸው ተጥሶ በሞት ፍርድ የሚያስቀጣ ወንጀል ተከሰው በኢትዮጵያ ወህኒ ቤት ...

Read More »

የአዲስአበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በወቅቱ ፍቃድ አላሳደሱም ያላቸውን 65 የሀገር ውስጥ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ድርጅቶች መዝጋቱን አስታወቀ።

ግንቦት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከግንቦት 1 ቀን 2008 ጀምሮ ፈቃዳቸው ከተሰረዘባቸው ድርጅቶች መካከል ከ 1997 ዓም ጀምሮ በስራ ላይ የነበሩ ይገኙበታል። እነዚህ ድርጅቶች ፈቃዳቸውን ለማሳደስ ፈቃደኛ ያልሆኑበት ምክንያት ምን እንደሆነ ቢሮው አልጠቀሰም። ፈቃዳቸው ከተሰረዘባቸው ድርጅቶች አንዳንዶቹ ፈቃዳቸው የሀገር ውስጥ ስራና ሰራተኛን ማገናኘት ቢሆንም በገሀድ ወደአረብ አገራት ሰራተኞች የሚልኩ እንደነበሩና የውጪ ስራ ስምሪት መታገድ ጋር ተያይዞ ...

Read More »

64 ስደተኛ ኢትዮጵያውያን በሱዳን መታሰራቸውን ሂውማን ራይትስ ዎች ገለጸ

ኢሳት ( ግንቦት 23 ፥ 2008) የሱዳን መንግስት 64 ኢትዮጵያውን አስሮ እንደሚገኝና ወደ ኢትዮጵያ በግዳጅ ሊመልስ ይችላል ሲል ሂውማን ራይትስ ዎች የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽንም የታሰሩትን ኢትዮጵያውያንን እንዳይጎበኝ ተከልክሏል ሲል ለሰብዓዊ ሰብዓዊ መብት ጉዳይ የሚከራከረው ይኸው አለም አቀፍ ድርጅት ሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ሱዳን በግንቦት 2008 ዓም ብቻ ከ 64 ኢትዮጵያውያን በተጨማሪም 442 ኤርትራውያንን በግዳጅ ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ አድርጋለች ሲል ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የሚደረገው ጫና ተጠናክሮ ቀጥሏል

ኢሳት ( ግንቦት 23 ፥ 2008) በቃሊቲ ወህኒ ቤት በሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ በእስር ቤቱ ሃላፊዎች የሚደረገው ጫና ተጠናክሮ መቀጠሉ ታወቀ። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የ18 አመት እስራት ተፈርዶበት በወህኒ ቤት የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ ከቤተሰብ እንዳይገናኝ ተከልክሏል፣ ስንቅ እንዳይገባለትም ዕገዳ ተጥሎበታል። መስከረም 2003 ዓም ጀምሮ ላለፉት 5 አመታት ያህል በአሸባሪነት ተከሶና ተፈርዶበት በወህኒ ቤት የሚገኘው ...

Read More »

ከ100 በላይ የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን በማላዊ ታስረው እየተሰቃዩ ነው ተባለ

ኢሳት ( ግንቦት 23 ፥ 2008) የማላዊ መንግስት ክ100 የሚበልጡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን የሰብዓዊ መብ በጎደለው ሁኔታ አስሮ ይገኛል ያሉ የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ድርጊት በመቃወም ሃገር አቀፍ የተቃውሞ ዘመቻን ጀመሩ። በኢትዮጵያውያን ስደተኞች የእስር ቤት አያያዝ ቅሬታቸውን እየገለፁ ያሉት እነዚሁ ድርጅቶች 119 የሚሆኑና ወደማላዊ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በሶስት እስር ቤቶች ለመከራ ተዳርገው እንደሚገኙ ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያን ስደተኞቹ የእስር ...

Read More »

በሱዳን አብዬ ግዛት የሞቱ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ቁጥር 16 ደረሰ

ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2008) ሁለቱ ሱዳኖች የይገባኛል ጥያቄን አንስተው በሚገኙባት የአብዬ ግዛት በሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው ከሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች መካከል በተለያዩ ጊዜያት የሞቱ ወታደሮች ቁጥር 16 መድረሱን የተባበሩት መንግስታት የልዑካን ቡድን ገለጠ። የሰላም አስከባሪ ቡድኑ ሰላም ማስከበር ስራ ላይ ተሰማርተው ህይወታቸው ላጡ ወታደሮች ቤተሰቦች የክብር የሜዳሊያ ስጦታን ሰሞኑን በአብዬ ግዛት ማበርከቱን የሱዳን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ሁለቱ ሱዳኖች በነዳጅ ...

Read More »

ግብፅ ከሃያ በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በግዳጅ ወደ ኢትዮጵያ መለሰች

ኢሳት (ግንቦት 23 ፥ 2008) የግብፅ መንግስት በሃገሪቱ በኩል ወደ ሌላ ሃገር በህገወጥ መንገድ ለመጓዝ ሙከራን አድርገዋል ያላቸውን ከ20 በላይ ኢትዮጵያውያን፣ የሱዳን እንዲሁም የናይጀሪያን ተወላጆችን በግዳጅ ወደ ሃገራቸው መመለሱ ታውቋል። መቀመጫቸውን በካይሮ ያደረጉ የየሃገራቱ የኤምባሲ ተወካዮች ስደተኞቹን ወደሃገራቸው ለመመለስ ትብብር ያደረጉ ሲሆን፣ 24 የሚሆኑት ስደተኞች በአራት እስር ቤቶች መቆየታቸውን ካይሮ ፖስት ጋዜጣ ማክሰኞ ዘግቧል። የግብፅ መከላከያ ሰራዊት በበኩሉ ባለፉት 10 ...

Read More »