.የኢሳት አማርኛ ዜና

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የህግ ምክር እንዲያገኙ ስምምነት መደረሱ ተነገረ

ኢሳት (ግንቦት 25 ፥ 2008) የብሪታኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግስት በእስር ላይ የሚገኙ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ነጻ የሆነ የህግ ምክርን አግኝተው የሃገሪቱ የህግ-ስርዓት የሚፈቅደውን አማራጭ እንዲመለከቱ ስምምነት መደረሱን ሃሙስ ይፋ ተደረገ። ይኸው ስምምነት በኢትዮጵያ ጉብኝት ባደረጉ የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፊሊፕ ሃሞንድና በኢትዮጵያ ባለስልጣናት በኩል መደረሱን የብሪታኒያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከምክክክሩ በኋላ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ለሁለት ቀን በአዲስ አበባ ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት ጸረሽብር ህጉን እንዲሰርዝ ጥሪ ቀረበ

ኢሳት (ግንቦት 25 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት  የጸረሽብር ህግን በመጠበቀም በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ በግል መገናኛ ብዙሃን፣ በሰላማዊ ተቃዋሚዎች እንዲሁም በፖለቲካ ድርጅቶች ላይ እያደረሰ ያለውን ወከባና እንግልት እንዲያቆም የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጥሪ አቀረቡ። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ማህበር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ያሬድ ሃይለማሪያም መንግስት እየወሰደ ያለው አፈና በኦሮሚያ ተቃውሞ እንዲስፋፋ አስተዋጽዖ አድርጓል ሲሉ ዲፌንድ ዲፌንደርስ ለተባለው በምስራቅና በአፍሪካ  ቀንድ ለሚሰራው ተቋም ...

Read More »

ጄኔራል ሳሞራ የኑስ ትልቅ የገበያ ማእከል ገንብተው እያከራዩ ነው

ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ መከላከያ ከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች በአዲስ አበባ ዘመናዊ የንግድ እና የመኖሪያ ቤቶችን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እያወጡ መገንባታቸውን የሚያሳዩ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በኢሳት ሲለቀቁ ቆይተዋል። በአሁኑ ሰአት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የሚገነቡ ዋና ዋና የሚባሉ የህንጻ ግንባታዎች በህወሃት የፖለቲካ መሪዎች፣ በህወሃት ነባር ታጋይና አሁን ከፍተኛ የጦር ኣዛዦች በሆኑ ግልሰቦች እንዲሁም ከእነርሱ ጋር ...

Read More »

ሰመጉ በወልቃይት እና በሌሎችም አካባቢ የተገደሉና የጠፉ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረገ

ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ( ኢሰመጉ) የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ( ሰመጉ) በ141ኛው ልዩ ሪፖርቱ በወልቃይት፣ በቅማንት፣ በቁጫና በኮንቶማ አካባቢዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገደሉ፣ የጠፉ፣ የታሰሩ እንዲሁም የተሰደዱ ሰዎችን እና በአጠቃላይ የደረሰባቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፋ አድርጓል። ሰመጉ ከወልቃይት የአማራ ማንነት ጋር በተያያዘ የተገደሉ የ34 ሰዎችን ፣ ታፍነው የተወሰዱ የ47 ...

Read More »

የፌደራል ፖሊስ አባላት ስራቸውን የሚለቁት በደሞዝ ማነስና የአላማ ጽናት ጉድለት አኳያ ነው ሲል ኮሚሽኑ አስታወቀ

ግንቦት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአምስት አመት እቅዱ ላይ መስሪያ ቤቱን የሚለቁ ወታደሮች መበራከታቸውን እና  አዳዲስ አባላትን ለማሰልጠን የተደረገው ጥረትም አለመሳካቱን ገልጿል። መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ዝርዝር ሪፖርት ላይ ለፍልሰቱ የሰጠው ምክንያት ኢኮኖሚያዊና የአቋም መላላት የሚል ነው። በሃገራችን ይላል ሰነዱ “ ካለው አጠቃላይ እድገት የሚመነጭ የስራ አማራጭ በማየትና አንዳንድ የአላማ ጽናት የሚጎድላቸው አባላትም በኩብለላም ...

Read More »

ለህገመንግስት ታማኝ አይደሉም ተብለው ከዳኝነት ስራቸው የታገዱት የህግ ባለሙያ ለጥብቅና ያመለከቱት ፈቃድ ውድቅ ተደረገ

ኢሳት (ግንቦት 24 ፥ 2008) በቅርቡ ለህገ-መንግስቱ ታማኝ ሆነው አልተገኙም” ተብለው ከዳኝነት ስራቸው የታገዱት የህግ ባለሙያ የጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደረገ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወደ አምስት የሚጠጉ ከፍተኛ ዳኞች በተለያዩ መድረኮች ህገመንግስቱን የሚጻረር ንግግርን አድርገዋል ሲል ከዳኝነት ስራቸው እንዲታገዱ ከወራት በፊት ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል። ከዳኝነት ስራቸው እንዲነሱ ከተደረጉት መከከል አንደኛው የሆኑት አቶ ግዛቸው ምትኩ የጥብቅና ፈቃድ ለማግኘት ...

Read More »

የዞን 9 አባላት ወደ ውጭ አገር እንዳይጓዙ የጉዞ ሰነዳቸውን መነጠቃቸው ተነገረ

ኢሳት (ግንቦት 24 ፥ 2008) በሽብር ወንጀል ተከሰው ለአንድ አመት ያህል በወህኒ ቤት ታስረው የተፈቱት የዞን 9 ጦማሪያን አባላት ከተለቀቁበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ተለያዩ የአለም ክፍሎች እንዳይጓዙ በኢትዮጵያ መንግስት የመጓጓዣ ሰነድ መቀማታቸው ተነገረ። የህግ መምህርና ጦማሪ ዘላለም ክብረት የዞን 9 ጦማሪያን አባላት ባለፈው አመት ያለፍርድ ሂደት ከእስር የመለቀቃቸው ጉዳይ ለፕሬዚደንት ኦባማ የተሰጠ ገጸ-በረከት ነው ካለ በኋላ፣ “በጊዜው ለምን እንደተለቀቅን ስንጠይቅ፣ ...

Read More »

በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የመንግስት ተወካይ እንዲገኝ ተወሰነ

ኢሳት (ግንቦት 24 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ የመንግስት ተወካይ እንዲገኝ አባቶች ወሰኑ። በዚህ ትልቅ መንፈሳዊ ጉባዔ ላይ ዕምነቱ የማይታወቅ የመንግስት ተወካይ እንዲሳተፍ ጥሪ መቅረቡን በመቃወም ታዋቂ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮች የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለፓትሪያርክ እንደራሴ ለመሾም በሚደረገው ውይይት፣ የመንግስት ተወካይ እንዲገኝ ሃሳቡን ያቀረቡት ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ...

Read More »

ሩሲያ ከ160 ሚሊዮን ዶላር በላይ እዳ እንድትሰርዝላት ኢትዮጵያ ጠየቀች

ኢሳት (ግንቦት 24 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ከሩሲያ መንግስት ያለበትን ከ160 ሚሊዮን ዶላር በላይ እዳ “የልማት ፕሮጄክቶች” ለማካሄድ በሚል እዳው የሚሰረዝበትን መንገድ እያግባባ መሆኑን የሩሲያ መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘገቡ። ሃገሪቱ ከኢትዮጵያ መንግስት የሚቀርቡላትን የልማት ፕሮጄክቶች ዝርዝር በመመርመር በቅርቡ ውሳኔን እንደምታስተላለፍ ስፐትኒክ ኒውስ የተሰኘ የሩሲያ ጋዜጣ የሁለቱ ሃገራት ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ አስነብቧል። እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ1998 አም ጀምሮ ሩሲያ ወደ አምስት ...

Read More »

 ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በዋሽንተን ዲሲና ሲያትል ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ

ኢሳት (ግንቦት 24 ፥ 2008) የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰት ብርሃኑ ነጋ በአሜሪካ ዋሽንግተን እንዲሁም በሲያትል ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር ተወያዩ። ለዲፕሎማሲያዊ ስራዎችና ድርጅታዊ ተግባሮች በአውሮፓና በአሜሪካ ቆይታ ማድረጋቸው የተገለጸው ፕሮፌሰት ብርሃኑ ነጋ በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ከገንዘብ ድጋፍ ባሻገር በዲፕሎማሲያዊ ስራዎች ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ከኤርትራ ወደ አውሮፓ ከዚያም ወደ አሜሪካ የተሻገሩት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ በጥር ወር 2008 ዋሽንግተን ...

Read More »