ኢሳት (ሰኔ 2 ፥ 2008) የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ሃሙስ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንትና ምክትል ፕሬዚደንቱ ከሃላፊነት አነሳ። የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት የነበሩት አቶ ደሞዜ ማሜ እና ምክትላቸው አቶ ቦጀ ታደሰ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከአመታት ካገለገሉበት ስልጣን እንዲነሱ መደረጉ ታውቋል። ሃሙስ በአዳማ ከተማ የተካሄደው የዳኞቹን ከሃላፊነት መነሳትን ተከትሎ አቶ አዲሱ ቀበኔሳ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የኢትዮጵያ መንግስት “ተቃዋሚዎች እግር ሲያወጡ መቁረጥ” የሚል ስትራቴጂ እንደሚከተል ዶ/ር መረራ ተናገሩ
ኢሳት (ሰኔ 2 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ የመቻቻል ፖለቲካ የሚከተል በማስመሰል በአገር ውስጥ ግን ተቃዋሚዎችን መፈናፈኛ አሳጥቶ እንደሚገኝ ዶ/ር መረራ ገለጹ። የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ወህኒ ቤት መውረዳቸውንና ቢሮዎቻቸው ባዶ መሆናቸውን ዶ/ር መረራ ጉዲና አሜሪካ አገር ለሚገኘው ኤን ፒ አር ለተባለ የሬዲዮ ጣቢያ ተናግረዋል። በቁም እስር ከሚገኙት የፓርቲው ጸሃፊ በተጨማሪ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ምክትል ሊቀመንበር፣ ረዳት ጸሃፊ፣ እና ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት ቦንድ በመሸጥ የሰበሰበውን ከእነወለዱ 6.5 ሚሊዮን ዶላር እንዲመልስ ተወሰነ
ኢሳት (ሰኔ 2 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መብራት ሃይል ባለስልጣን በአሜሪካን ህገወጥ የቦንድ ሽያጭ በማድረግ የሰበሰበውን 5.8 ሚሊዮን ድላር ለባለድርሻዎቹ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከእነወለዱ እንዲመልስላቸው ተወሰነበት። የአሜሪካን የቦንድ ሽያጭና ግዥን የሚቆጣጠረው The Securities and Exchange Commission የተባለው ኮሚሽን ባቀረበው ክስ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በአሜሪካን ባልተመዘገበ የቦንድ ሽያጭ የሰበሰበውን 5.8 ሚሊዮን ዶላር ጨምሮ በድምሩ 6.5 ሚሊዮን ዶላር እንዲከፍል መስማማቱን ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ይህም ...
Read More »አልሸባብ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ጥቃት ፈጽሞ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ
ሰኔ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሶማሊያው ታጣቂ ሃይል አልሸባብ በማእከላዊ የሶማሊያ ግዛት በ አልገን ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ ጦር ላይ በድንገት ባደረሰው ጥቃት 60 ወታደሮች መገደላቸውን የአለማቀፍ መገናኛ ብዙሃን አልሸባብን በመጥቀስ ሲዘግቡ ፣ የመንግስት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው መረጃው ሃሰት ነው ብለዋል። የአፍሪካ ህብረት ዘግይቶ ባወጣው መግለጫ ግን ጉዳት መድረሱን አምኖ፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሃዘኑን ገልጿል።
Read More »የአሜሪካ የግብይት ደህንነት ኮሚሽን በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ አገሪቱን በጥቁር መዝገብ ላይ ያስቀምጣታል ተባለ
ሰኔ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአሜሪካ መንግስት የግብይት ደህነት ኮሚሽን ( securities and exchange commission) ባወጣው መግለጫ ፣ የኢትዮጵያ መብራት ሃይል ለአባይ ግድብ ግንባታ በሚል ከኢትዮጵያውያን ሲሰበስብው የነበረው የቦንድ ሽያጭ ህገወጥ መሆኑን በመጥቀስ አገሪቱ 6 ሚሊዮን 500 ሺ ዶላር እንድትከፍል መስማማቱን ተከትሎ፣ ውሳኔው የኢትዮጵያን ክብር የሚነካ ብቻ ሳይሆን ፣አገሪቱን በጥቁር መዝገብ ውስጥ blacklist ውስጥ የሚያስገባት መሆኑን በዴንቨር ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ዞን ድርቅ ባጠቃቸው ቀበሌዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ዓመቱን በሙሉ በመምህራን እጥረት እንደተቸገሩ ተነገረ፡፡
ሰኔ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አብዛኛው መምህራን ከድርቁ ጋር ተያይዞ በነበረው የውሃ እጥረት ስጋት ምክንያት በየጊዜው ስራቸውን እየለቀቁ መሄዳቸውን የተናገሩት የትምህርት ባለሙያ በሚለቁ መምህራን ትክ የሚመጡትም ብዙ ሳይሰሩ በመልቀቃቸው የመማር ማስተማሩ ሂደት ተስተጓጉሎ የትምህርቱ ጥራት እየወደቀ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ ሰው ከድርቁ ስጋት የተነሳ አካባቢውን በመልቀቁ መምህራንም እንደ ነዋሪው ቀየውን እየለቀቁ ለመሄድ መገደዳቸውን ተናግረው፤ በዚህ ምክንያት የትምህርቱ ስራ እየወደቀ ...
Read More »ኢትዮጵያ ያጸደቀችው የኢንተርኔት አጠቃቀም ህግ ተቃውሞ ገጠመው
ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2008) የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት አጠቃቀም ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል በሚል ማክሰኞ የጸደቀውን አዋጅ ተከትሎ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት በህጉ ላይ ቅሬታ ማቅረብ መጀመራቸውን አለም አቀፉ መገናኛ ብዙሃን ረቡዕ ዘገቡ። እስከ 10 አመት የሚደርስ ቅጣትን ያስተላልፋል የተባለው ይኸው አዲስ ህግ፣ በሃገሪቱ ሃሳብን ለመግለጽ በሚደረገው ጥረት ላይ ተጨማሪ ቁጥጥርን እንደሚያጠናክር የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አካላት በመግለጽ ላይ መሆናቸው ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ዳባት ግጭት ተቀሰቀሰ
ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2008) በሰሜን ጎንደር ዳባት ከተማ ላይ በቀድሞ መንግስት የተተከለ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመር ወደ ትግራይ ክልል ለመውሰድ የተደረገ ሙከራ በህዝቡና በታጠቁ የመንግስት ሃይሎች መካከል ግጭት መቀስቀሱን እማኞች ለኢሳት ገለጹ። የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሩን ለመውሰድ የመጡ ሁለት ከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት የሰነዘረው የዳባት ነዋሪ ህዝብ ከመንግስት ታጣቂዎች ጋር ግጭት ውስጥ በመግባት ሲታኮሱ እንደነበር ከስፍራው ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። አንድ የአካባቢው ነዋሪ ...
Read More »በድርቁ ምክንያት ስድስት ሚሊዮን ህጻናት ትምህርታቸው ሊስተጓጎል እንደሚችል ተመድ ገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2008) በኢትዮጵያ በስድስት ክልሎች ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ በትምህርት ላይ የሚገኙ የሚገኙ ወደ ስድስት ሚሊዮን ህጻናት ትምህርታቸውን ሊስተጓጎል እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። በወቅታዊ የሃገሪቱ የድርቅ አደጋ ዙሪያ ሪፖርትን ያወጣው ድርጅቱ በድርቁ መባባስ የተነሳ ተማሪዎች ለምግብና ለውሃ ችግር ተጋልጠው እንደሚገኙ ገልጿል። እነዚሁ ለከፋ የድርቅ አደጋ ተጋልጠው የሚገኙትና ቁጥራቸው ወደ ስድስት ሚሊዮን አካባቢ የሚደርሱ ህጻናት ...
Read More »ሊሰበሰብ ከታቀደው የውጭ ንግድ ገቢ ግማሽ ያህሉ ብቻ መገኘቱ ተገለጸ
ኢሳት (ሰኔ 1 ፥ 2008) በመገባደድ ላይ ባለው የ2008 በጀት አመት ከውጭ ንግድ ገቢ ሊገኝ ከታቀደው አራት ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ባለፉት ዘጠኝ ወራቶች 51 በመቶ የሚሆነው ብቻ መገኘቱን የንግድ ሚኒስቴር ገለጸ። የውጭ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆል የሃገሪቱ የንግድ ሚዛን ከ16 ቢሊዮን ዶላር በላይ ልዩነት እንዲያሳይ ምክንያት መሆኑም ታውቋል። ባለፉት ዘጠኝ ወራቶች የተገኘው የውጭ ንግድ ገቢ ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጻር በ 6.5 ...
Read More »