ሰኔ ፲(አሥር) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዋጅ ቁጥር 47/67 ትርፍ ቤትን ለመንግስት ባደረገው አዋጅ የተወረሱ የቀበሌ ቤቶችን አመራሩ ለራሱ ጥቅም ቅድሚያ በመስጠት በመኖሪያነትና በንግድ ቤትነት የሚገለገልበት አካሄድ አግባብ አለመሆኑን ሰሞኑን የባህርዳር ከተማ አስተዳደር አገልግሎት አቅርቦትና አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፋሲል ሙሉ ተናግረዋል። “ድሃ ይቅደም!” የሚሉት የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር ፣ ህብረተሰቡ በዚህ አሰራር መማረሩን ገልጸው፤ የከተማ አስተዳደሩ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ባለፉት 4 ወራት 7 የደህንነት አባላት ተገደሉ
ኢሳት (ሰኔ 9 ፥ 2008) ባለፉት 4 ወራት 7 የኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት ሰራተኞችንና አስተባባሪዎች በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በአልሞ ተኳሾች መገደላቸውን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ዘውዱ ተከለማሪያም፣ ሲሳይ እና ኤሊያስ የተባሉትን የደህንነት አስተባባሪዎችን ጨምሮ 7 የደህንነት ሰራተኞች በሃረር፣ አዳማና ደብረዘይት ተገለዋል። በተለይም በሶማሊ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት ደህንነት መዋቅር አስተባባሪ ወይንም ኢንተለጀንስ ኦፕሬሽን ኮኦርዲኔተር የሆኑት ሶስቱ የህወሃት አባላት መገደል በሶማሊያ ከአልሻባብ ጋር በሚደረገው ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል በመንግስታዊ ድርጅቶች የተካሄደውን ግምገማ ተከትሎ 12 ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
ኢሳት ዜና (ሰኔ 9 ፥ 2008) በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ መንግስታዊ ድርጅቶች ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ግምገማ ተከትሎ 12 ሃላፊዎች ሃሙስ በቁጥጥር ስር ዋሉ። የቀድሞ የገላን ከተማ ከንቲባ አቶ ሙሉጌታ ከበደን ጨምሮ በተለያዩ የስራ ሃላፊነት ላይ የነበሩ 12 የክልሉ አመራሮች ለእስር የተዳረጉ ሲሆን ግለሰቦቹ አርብ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሏል። በቁጥጥር ስር የዋሉት የክልሉ ሃላፊዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክትትል ሲካሄድባቸው መቆየቱን የኦሮሚያ ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት ተጠያቂነትና ግልጽነት እንዲኖረው ጠየቀ
ኢሳት ዜና (ሰኔ 9 ፥ 2008) የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ሃላፊዎች የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስርዓት ተጠያቂነትና ግልጽነት የሚታይበት እንዲሆን አሳሰቡ። የህብረቱ የሰብዓዊ መብት ምክትል ፕሬዚደንት የሆኑት ፊዴሪካ ሞግሪኒ በቤልጅየም ብራሰልስ ጉብኝት እንያደረጉ ካሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጋር በኦሮሚያ ክልል ስለተካሄደው ተቃውሞና ተያያዥ ፖለቲካዊ ጉዳዮች መምከራቸውን የአውሮፓ ህብረት አስታውቋል። ህብረቱ እያካሄደ ካለው የልማት ፕሮግራም ጎን ለጎን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ...
Read More »በአዲስ አባባ በአስር ክፍለ-ከተሞች አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ተስፋፋ
ኢሳት ዜና (ሰኔ 9 ፥ 2008) ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ የተቀሰቀሰው የአጣዳፊ ተቅማትና ትውከት በሽታ በአስሩም ክፍለ ከተሞች ተሰራጨ። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን በመግለጽ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲያደርጉ ሃሙስ በድጋሚ ጥሪ አቅርቧል። ወደ 15 የሚደርሱ ሰዎች በበሽታው ተይዘው በህክምና ላይ ሲሆኑ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እስካሁን ድረስ የደረሰ የሞት አደጋ አለመኖሩን ገልጿል። የበሽታው መሰራጨት ተከትሎ ...
Read More »በአዲስ አበባ የተቋቋሙ ወደ አራት ሺ የሚሆኑ አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች የገቡበት አለመታወቁ ተነገረ
ኢሳት ዜና (ሰኔ 9 ፥ 2008) በአዲስ አበባ ከተማ ድህነትን ለመቅረፍ ይረዳሉ ተብለው ከተቋቋሙ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች መካከል ወደ አራት ሺ የሚጠጉት የገቡበት አለመታወቁን መንግስት ሃሙስ አስታወቀ። ከእነዚሁ አራት ሺ ተቋማት በተጨማሪ 1ሺ 600 አካባቢ ኢንተርፕራይዞች ባለቤታቸውና አባሎቻቸውን ማግኘት ሳይቻል መቅረቱን በድርጅቶቹ ላይ ቆጠራን ሲያካሄድ የቆየው መንግስታዊ ድርጅት ገልጿል። ድርጅቱ ወደ አራት ሚሊዮን ብር አካባቢ ወጪን በማድረግ ቆጠራን ሲያካሄድ ቢቆይም ...
Read More »በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ለመቀልበስ መንግስት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መውሰዱን አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አስታወቀ
ኢሳት ዜና (ሰኔ 9 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰውና ከመንፈቅ በላይ በዘለቀው ተቃውሞ የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 400 ያህል መሆኑን እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን ፣በአስር ሺዎች መታሰራቸውን ሂዩማን ራይትስ ዎች (Human Rights Watch) ሃሙስ ይፋ አደረገ። የ314ቱን ሰለባዎች ስም ዝርዝር በቀን እና በአድራሻ በ 86 ገጽ ሪፖርቱ አስፍሯል። የHuman Rights Watch ሪፖርት ከ125 በላይ የሚሆኑ ምስክሮች፣ የጥቃቱ ሰለባዎች፣ እና የመንግስት ...
Read More »ኤርትራ ከ200 በላይ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገድላ ከ300 በላይ ማቁሰሏን አስታወቀች
ሰኔ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የህወሃት መንግስት ሰኔ 5 ቀን 2008ዓም በጾረና ግንባር ጥቃት መጀመሩንና ሰኞ ሰኔ 6 ጠዋት ላይ ለማጥቃት የተንቀሳቀሰው ጦር ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት ወደ ሁዋላ ማፈግፈጉን ገልጿል። በዚህ አላማው ግልጽ ባልሆነ የግድየለሽ ጥቃት 200 የኢትዮጵያ ወታደሮች ሲገደሉ 300 የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል ብሎአል። የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊልቅ ይቻላል ሲል በመግለጫው ...
Read More »የተለያዩ የጸጥታ ሃይሎችን ሙሉ መረጃዎች የሚያሳዩ ሰነዶች ኢሳት ውስጥ ገቡ
ሰኔ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ በአገሪቱ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የጸጥታና የደህነት ሃይሎች ሙሉ ስም ዝርዝር፣ የመታወቂ ቁጥር፣ የመኖሪያና የስራ አድራሻ እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች ኢሳት እጅ ገብተዋል። የጸጥታ ሃይሎች ያደረጉዋቸውን ስብሰባዎች የሚያሳዩ ቃለ ጉባኤዎች እንዲሁም በሚስጢር እንዲያዙ የተደረጉ የምርምራ ዘገባዎችም ኢሳት እጅ ገብተዋል። ኢሳት የደህንነት ምንጮቹን አደጋ ውስጥ በማይጥል መልኩ ሁኔታዎች ሲመቻቹ ዋና ዋና መረጃዎችን እየመረጠ ...
Read More »የመንግስት ወታደሮች 400 የኦሮሞ ተወላጆችን መግደላቸውን ሂውማን ራይትስ ዎች አስታወቀ
ሰኔ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሚያ ክልል ተካሂዶ በነበረው ሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞ ወቅት በገዥው መንግስት ታጣቂዎች ከ400 በላይ የሚሆኑ ሰላሚዊ ዜጎች በግፍ መገደላቸውንና ከአስር ሺ በላይ መታሰራቸውን ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው ሪፓርት ገልጿል። ሂውማን ራይትስ ወች ለተወሰደው ኢሰብዓዊ ጨፍጨፋ የኢትዮጵያ መንግስት በአፋጣኝ ኃላፊነቱን መውሰድ አለበት ብሏል። ገለልተኛ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ በዜጎች ...
Read More »